ኢሳት አዲሱ ስርጭቱ መቋረጡን ተከትሎ የችግሩን ምንጭ ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በቅርቡ በዩቴልሳት ስርጭቱን በአዲስ መልክ ማሰራጨት ቢጀምርም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምክንያቱ በውል ባልተወቀ ሁኔታ ስርጭቱ ተቋርጧል።

እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቱ እንዲገለጽላቸው  ለሚያቀርቡት ጥያቄ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቓል።

የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የኢሳትን ስርጭት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው በማለት መገምገሙን መዘገባችን ይታወሳል። ኢሳት ካለፉት 5 አመታት ጀምሮ ከገዢው ፓርቲ የሚደርስበትን ከፍተኛ የአፈናና የዲፕሎማሲ ጫና ተቋቁሞ ስርጭቱን በውጭ

በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም በአገር ውስጥ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የመረጃና የሞራል ድጋፍ ዝግጅቱን በማቅረብ ላይ ነው።