በየመን የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤደንን ለመያዝ በሃውቲ ሚሊሺያዎችና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሃዲ መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን፣ 80 ሲቪሎች በጦርነቱ መሃል መገደላቸው ተዘግቧል።

የሃውቲ ሚሊሺያዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ታማኞችና በአረብ አገራት ጥምረት የአየር ሃይል ጥቃት የተነሳ እስካሁን የኤደንን ከተማ ለመያዝ አልቻሉም።የከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።