የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደቡብ ሱዳንና ኤርትራን ሊጎበኙ ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳሚ ሹክሪ ወደ ጁባ በማቅናት ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የሚመክሩ ሲሆን፣ ወደ ኤርትራም በማቅናት በሽበርተኝነት፣ እና በአካባቢው ባሉ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ የግብጹ አል ሃራም ዘግቧል።

ጉብኝቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ መንግስት ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመራቸውን ባስታውቁ ማግስት እንዲሁም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የአባይን ግድብ በተመለከተ አዲስ የትብብር ማእቀፍ በተፈራረሙ ማግስት የሚደረግ ነው።