(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በአውሮፓ የሚኖሩ ከ20ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያንን የሚያነጋግሩበት መድረክ በፍራንክፈርት ከተማ መዘጋጀቱ ታወቀ። ከነገ በስቲያ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያውያን ጋር በሚያደርጉት ውይይት ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ኢትዮጵያውያን ወደ ስፍራው መጓዛቸው ተመልክቷል። ዛሬ ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፓሪስ ሲደርሱ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ፍቅሩ ኪዳኔን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ተቀብለዋቸዋል። በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ...
Read More »ጄይል ኦጋዴን እስር ቤት ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) የሰው ልጅ የስቃይ ማዕከል በሚል የሚታወቀው ጄይል ኦጋዴን እስር ቤት ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑ ተገለጸ። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ዑመር ለኢሳት እንደገለጹት በቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ የተከፈተውና የፖለቲካ ተቀናቃኞች የሚሰቃዩበት፡ ቶርች የሚደረጉበትና የሚገደሉበት ጄይል ኦጋዴን በይፋ ከተዘጋ በኋላ ሙዚየም እንዲሆን ተደርጓል። በሌላ በኩል አቶ ሙስጠፋ ኢትዮጵያዊነትን በሶማሌ ክልል ማጠናከር የቅድሚያ ተግባራቸው መሆኑን ገልጸዋል። ጎጠኝነት መጨረሻው ...
Read More »በአፋር ክልል የተጀመረው ተቃውሞ መቀጠሉ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) በአፋር ክልል የተጀመረው ተቃውሞ ቀጥሎ ዛሬ በዳሎልና ኤረብቲ አፋሮች ድምጻቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ። ትላንት ሰመራና በራሂሌ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ሰዎች በልዩ ሃይል ድብደባ መጎዳታቸው ታውቋል። በመሰንጠቅ አደጋ ውስጥ የሚገኘው የክልሉ ገዢ ፓርቲ አብዴፓ ያባረርኳቸውን አመራሮች እመልሳለሁ ሲል አስታውቋል። ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ፕሬዝዳንቱ አቶ ስዩም አወል ስልጣን እለቃለሁ ቢሉም ለዘመዳቸው አውርሰው ለመልቀቅ ማቀዳቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአፋር ...
Read More »በመከላከያ ሰራዊትና በኦነግ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) በመከላከያ ሰራዊትና በኦነግ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀስቀሱ ተገለጸ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የመንግስት ሃይል ጋር ለመዋጋት ወጣቶች ወደ ጫካ መግባታቸው ትክክለኛ ርምጃ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። ለኢሳት በደረሰው መረጃም ከአርብ ጀምሮ በጉጂ ዞን ውጊያ ተከስቷል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተበላሸ መምጣቱን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ በኦነግ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመሩም ...
Read More »አማራና ኦሮሚያ የሚባሉ ክልሎችን የፈጠረው ኢህአዴግ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 16/2011)አማራና ኦሮሚያ የሚባሉ ክልሎችን የፈጠረው ኢህአዴግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ። ከማንነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ የሚደረግ ሙከራ ነው ሲሉም የህወሃት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ከድምጸ ወያኔ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ እንደገለጹት የወልቃይትና ራያ የማንነት ጥያቄዎች የቀድሞውን የጠቅላይ ግዛት መዋቅር ለመመለስ የሚደርግ እንቅስቃሴ ነው ። በሌላ በኩል ...
Read More »ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ሰመራ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 16/2011)የአፋር ክልል ገዢ ፖርቲ አብዴፓ ውስጥ የተፈጠረውን መሰንጠቅ ተከትሎ ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ሰመራ መግባታቸው ተገለጸ። ለውጡን በሚደግፉና በሚቃወሙ የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አብዴፓ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ፓርቲውን ለሁለት መክፈሉ ታውቋል። የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ስዩም አወል ምክትላቸውን ጨምሮ የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ኢስማዔል አሊሴሮንና ሌሎች 18 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ትላንት አግደዋል። በፕሬዝዳንቱ የታገዱት አመራሮችም በፊናቸው ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ...
Read More »የትግራይ ልዩ ሃይል ከወልቃይትና ራያ እንዲወጣ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 16/2011) የትግራይ ልዩ ሃይል ከወልቃይትና ራያ ወጥቶ በምትኩ የፌደራል ፖሊስ እንዲገባ ተጠየቀ። ልሳነ ግፉአን የተሰኘው የወልቃይት ጠለምት ጠገዴ መብት ተሟጋች ድርጅት በራያ እየተካሄደ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ወገንተኛ የሆነው የትግራይ ልዩ ሃይል ሰላም የሚያስከብር ባለመሆኑ ገለልተኛ የሆነ አካል በአካባቢው መስፈር ይገባዋል። ከራያ ተወላጆች ጎን እንቆማለን ያለው ልሳነ ግፉአን ህወሃት በቀረጸው ህገመንግስትም ሆነ በህወሃት በተዋቀረው ፌደራል ስርዓቱ የማንነት ...
Read More »በነጭ ሳር ፓርክ ታጣቂዎች ተጣቂዎች ቢያንስ 4 ሰዎችን ገደሉ
በነጭ ሳር ፓርክ ታጣቂዎች ተጣቂዎች ቢያንስ 4 ሰዎችን ገደሉ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአርባምንጭ ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የነጭ ሳር ፓርክ ውስጥ የመሸጉ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ 4 ሰዎች ሲገደሉ 3 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ጥቃቱን የኦነግ ታጣቂዎች እንዳደረሱት ይናገራሉ ኢሳት የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረገው ...
Read More »በዱራሜ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ
በዱራሜ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ ያጡ ወጣቶች ወደ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ማምራታቸውን ተከትሎ በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ተማሪዎቹ ቀደም ብለው ጥያቄያቸውን ለመስተዳድሩ አቅርበው ለዛሬ አርብ ተቀጥረው የነበረ ቢሆንም፣ በቀጠሮአቸው መሰረት ወደ መስተዳድሩ ሲሄዱ ያጋጣማቸው የፖሊስ ...
Read More »በታንዛኒያ ውቂያኖስ ዳርቻ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ ሰባት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገልብጠው ህይወታቸውን አጡ።
በታንዛኒያ ውቂያኖስ ዳርቻ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ ሰባት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገልብጠው ህይወታቸውን አጡ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) መነሻቸውን ከኬኒያ በማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ ከነበሩት 13 ተጓዦች ውስጥ ባጋጠማቸው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ሰባቱ መሞታቸውን ማክሰኞ ዕለት የታንዛኒያ ፖሊስ አስታውቋል። ጀልባዋ ሰኞ ማለዳ ላይ ህንድ ውቅያኖስ የኬኒያ እና የታንዛኒያ የባህር ዳርቻ በጀልባ ጉዞዋቸውን በማድረግ ላይ እያሉ ...
Read More »