(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011) በብሪታኒያ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሞት ባለፉት 5 አመታት እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ። ባለፈውአመት ብቻ 600 ያህል የጎዳና ተዳዳሪዎች በእንግሊዝና በዌልስ ግዛት መሞታቸውን የብሪታኒያ መንግስት መረጃዎች አመልክተዋል። ባለፉት ሁለት አመታት የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ሞት በ24 በመቶ መጨመሩም ታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 ጀምሮ የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ቁጥር በ169 በመቶ መጨመሩን የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘገባውን አቅርቧል። ይፋዊ ...
Read More »አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የተደረገላቸው አቀባበል ከጠበቁት በላይ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011) በጎንደርና በዳባት የተደረገላቸው አቀባበል ከጠበቁት በላይ እንደሆነባቸው አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ገለጹ። አርበኛ መሳፍንት ከኢሳትጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የህዝብ ስሜት የከፈሉት መስዋዕትነት ዋጋ እንዳለው ያሳየ ሆኗል። ከ250 ጦራቸው ጋር ከጎንደር በኋላ ወደ ባህርዳር የገቡት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ነጻነትና ፍትህ እስኪረጋገጥ በትግላቸው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ የደረሱባቸውን ጉዳዮች ወደፊት በዝርዝር እንደሚገልጹና አሁን ባለው ለውጥ ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ...
Read More »ለንደን ላይ ከ27 ዓመታት በፊት የተጠራው ድርድር ሳይጀመር መጠናቀቁ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011)ለንደን ላይ ከ27 ዓመታት በፊት በአምባሳደር ኸርማንኮኸን የተጠራው ድርድር ከሻዕቢያና ሕዉሃት መሪዎች ጋር ሳይተያዩና ሳይጀመር መጠናቀቁን የመንግስት ተደራዳሪ የነበሩት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ተናገሩ። ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ስለድርድሩዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል። ከአማጽያን ጋር የተደረጉት ድርድሮች ሁሉ የቀድሞው መንግስት ዋና ተደራዳሪ የነበሩት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ከኤርትራ ጋር ችግሩን ለመፍታት የፌደሬሽን አማራጭ ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል። በህወሃት በኩል ...
Read More »ኢትዮጵያ ለሁሉም የተመቸች ሃገር እንድትሆን እንሰራለን ተብሏል
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ/2011) ኢትዮጵያ ለሁሉም የተመቸች ሀገር እንድትሆንና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የለውጥ ሃይሉ ጠንክሮ እንደሚሰራ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለኢሳት ገለጹ። በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሰሜን አሜሪካ ያካሄደውን ጉብኝት አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል። በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት የሰሜን አሜሪካ የጉዞ ዓላማ ክልሉን በልማት፣በኢንቨስትመንት እና ...
Read More »የኦነግ ወታደሮች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ተሰቷቸዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወታደሮች ጥቃት ከተፈጸመባቸው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ሰጥተናል ሲሉ አቶ ዳውድ ኢብሳ ገለጹ። በትላንትናው ዕለት ኦዴፓ ያወጣውን መግለጫምየጦርነት አዋጅ ነው ያሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ የመንግስት ሰራዊት በዛሬው እለት ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው ሲሉምተናግረዋል። አዲስ አበባ በሚገኘውና በቅርቡ በመንግስት በተሰጣቸው ጽሕፈት ቤት መግለጫ የሰጡት አቶ ዳውድ ኢብሳ በዛሬው ዕለት ዶክተር ገዳን ጨምሮ ...
Read More »በሱዳን የገዢው ፖርቲ ጽሕፈት ቤት ተቃጠለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011)ሱዳን ውስጥ ለተቃውሞ አደባባይየወጡ ወጣቶች የገዢውን ፖርቲ ጽሕፈት ቤት አቃጠሉ። የተቃውሞው መነሻ በነዳጅ እና በዳቦ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ተቃውሞው የተነሳውና የተቀጣጠለው ከርዕሰ መዲናዋ ካርቱም 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አትባራ በተባለው ከተማ ሲሆን በተቃውሞው የሱዳኑ ገዢ ፓርቲ ናሽናል ኮንግረስ ጽሕፈት ቤት ከመቃጠሉ ባሻገር በጎዳናዎችም ላይ እሳት እያነደደ መገኘቱን አልጀዚራ ዘግቧል። አንድ የሱዳን ፓውንድ ...
Read More »ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገቡ። የደርግንመንግስት በመቃወም ስርአቱን ከከዱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመጀምሪያው የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ1981 በኮለኔል መንግስቱሃይለማርያም ላይ የተካሄደው የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ላይ ከውጭ ሆነው ተሳታፊ እንደነበሩም መረዳት ተችሏል። ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ትላንት ከናሚቢያ ዊንዲሆክ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንደተቀበሏቸው ...
Read More »የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ጸደቀ
(ኢሳትዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በኢትዮጵያ ከወሰንና ከማንነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚል የተዘጋጀው ረቂቃአዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ። በ33 ተቃውሞ የጸደቀው ይህ አዋጅ እንዳይጸድቅ 10 የሕወሃት የፓርላማ አባላት በፊርማ አስቀድመው ጥያቄ አቅርበዋል። ጥያቄያቸውም አዋጁ ሕገ መንግስቱን ይጻረራል የሚል ሲሆን የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ኮሚሽኑ የማማከር እንጂ የመወሰን ስልጣን ስለሌለው ሕገ መንግስት አይጻረርም በማለት ሞግተዋል። “የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ለማቋቋም ...
Read More »በተለያዩ የትግራይ እስር ቤቶች የራያ ተወላጆች ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በተለያዩ የትግራይ እስር ቤቶች ከ750 በላይ የራያ ተወላጆች ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። የራያ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ለኢሳትእንደገለጸው ተቃውሞ ከተነሳበት ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ በተወሰደ የጅምላ እስር 761 የራያ ተወላጆች ታስረውበአራት የትግራይ እስር ቤቶች ውስጥ ታጉረዋል። ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ የሚገልጸው ኮሚቴው አንድ ሰው በድብደባ ምክንያት ህይወቱ ማለፉን አስታውቋል። ከታሰሩት በተጨማሪ በርካታ የራያ ተወላጆች ...
Read More »በአማሮ ኬሌ በተከሰተ ግጭት በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ11/2011) ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦነግ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎችና በአማሮ ኬሌ ነዋሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት በሰውናንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስር በሚገኘውየአማሮ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ለሁለት ዓመት የዘለቀው ግጭት ሰሞኑን እንደ አዲስ ማገርሸቱን የአካባቢውነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የአንድ አርሶ አደር ህይወት የጠፋበት ግጭት ከትላንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን ጃሎ የተሰኘ ቀበሌ በእሳት መውደሙንም ...
Read More »