ለንደን ላይ ከ27 ዓመታት በፊት የተጠራው ድርድር ሳይጀመር መጠናቀቁ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011)ለንደን ላይ ከ27 ዓመታት በፊት በአምባሳደር ኸርማንኮኸን የተጠራው ድርድር ከሻዕቢያና ሕዉሃት መሪዎች ጋር ሳይተያዩና ሳይጀመር መጠናቀቁን የመንግስት ተደራዳሪ የነበሩት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ተናገሩ።

ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ስለድርድሩዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል።

ከአማጽያን ጋር የተደረጉት ድርድሮች ሁሉ የቀድሞው መንግስት ዋና ተደራዳሪ የነበሩት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ከኤርትራ ጋር ችግሩን ለመፍታት የፌደሬሽን አማራጭ ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል።

በህወሃት በኩል የድርድር ሃሳብ ሲመጣ የቀድሞው መንግስት አንገራግሮ እንደነበርና በኋላም እንደተቀበለው የገለጹት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ሕዉሃትም ሆነ ኢህአዲግን ወክለው የሚመጡት ተደራዳሪዎች የሕዉሃት ሰዎች ብቻ እንደነሩም አስታውሰዋል።

          በቀድሞው መንግስት በአምባሳደርነትና በሚኒስትርነት በተለያዩ ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች ያገለገሉት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከአማጽያኑ ጋር በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ከተሞች በሚስጥርና በይፋ የተደረጉትን ድርድሮች በዝርዝር ተመልክተዋል።

የኢህአዴግ ጦር አዲስ አበባ እንዲገባ ስለተወሰነው ውሳኔና ስለ ኮሎኔል መንግስቱ አወጣጥ በርሳቸው በኩል ያለውን መረጃ ይፋ አድርገዋል።

የደርግ መንግስት ሊወድቅ አንድ ቀን ሲቀረው ለንደን ላይ የተካሄደውን ድርድር በተመለከተም አደራዳሪው ሚስተር ኸርማንኮኸን ከጄኔራል ተስፋዬ ገብረኪዳን ጋር እያደረጉት ስላሉት ስምምነትና እነርሱ ጄኔራል ተስፋዬን ለማግኘት ስላደረጉት ሙከራ እንዲሁም ከለንደን ወደ አሜሪካ ስለተደረጉት ጉዞዎች በዝርዝር ገልጸዋል።

ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ከአማጽያን ጋር የተደረጉት ድርድሮች ሁሉ የቀድሞው መንግስት ዋና ተደራዳሪ እንደነበሩ ይናገራሉ።

በወቅቱ ከኤርትራ ጋር ችግሩን ለመፍታት የፌደሬሽን አማራጭ ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል።

በህወሃት በኩል የድርድር ሃሳብ ሲመጣ የቀድሞው መንግስት አንገራግሮ እንደነበርና በኋላም እንደተቀበለው የገለጹት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ሕዉሃትም ሆነ ኢህአዲግን ወክለው የሚመጡት ተደራዳሪዎች የሕዉሃት ሰዎች ብቻ እንደነሩም ሳይገልጹ አላለፉም።

ላለፉት 27 ዓመታት ድምጻቸው ያልተሰማውና በአሜሪካ ሉዚያና ግዛት ሳውዘርን ዩንቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር በመሆን በማስተማርና በአስተዳደር ስራ ላይ ከሚገኙት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ሰሞኑን ይዘን እንቀርባለን።