(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀል ግድያ ላይ ያወጣው መግለጫ ጉዳዮን አቅጣጫ ለማሳት የታለመ በመሆኑ እንደሚያወግዘው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ገለፀ:: የኮሚኒቲው ሰብሳቢ አቶ ታምሩ አበበ ለኢሳት እንደገለፁት የኤምባሲው መግለጫ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ እንደመጮህ የሚቆጠር ነው:: ኮሚኒቲው ይህን ያለው የአክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀልን ግድያ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ተገቢ አይደልም በሚል በፕሪቶሪያ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣውን መግለጫ ...
Read More »በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተጠርጣሪዎችን በነጻ ያሰናበቱት ዳኛ ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኮማንድ ፖስት የተያዙ ተጠርጣሪዎችን በነጻ አሰናብተዋል የተባሉ ዳኛ መታሰራቸው ተሰማ። ዳኛው በሰጡት ውሳኔ ላይ የለመታሰር መብታቸው ተጥሶ ወደ ወህኒ መውረዳቸውም ታውቋል። ዳኛው ለሚመሩት ችሎት ተጠርጣሪዎቹን አቅርበዋል የተባሉት አቃቤ ሕግም ለአንድ ቀን ታስረው መለቀቃቸው ተሰምቷል። ግዳዩ የተፈጸመው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ደኖ ወረዳ ነው።ቀኑ ደግሞ ሚያዚያ 12/2010። የወረዳው ኮማንድ ፖስትም ሶስት ተጠርጣሪዎችን ያስራል።ተጠርጣሪዎቹም ችሎት ይቀርባሉ። ነገር ...
Read More »ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ረገድ 150ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ረገድ ከአለም 180 ሀገራት ጋር ስትነጻጸር በ150ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ድንበር የለሽ የሪፖርተሮች ቡድን አመለከተ። ድንበር የለሽ የሪፖርተሮች ቡድን የተባለ አለም አቀፍ ተቋም የየሃገራቱን የጋዜጠኞች መብት አከባበር አስመልክቶ ባወጣው የግምገማ ሪፖርት እንደገለጸው ኢትዮጵያ በአሸባሪነት ሰበብ ጋዜጠኞችን በማሳደድ የከፋ ርምጃ ትወስዳለች። ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን መብት አከባበር በተመለከተ ከአመት አመት ሁኔታውን ከማሻሻል ይልቅ የባሰ ርምጃ እየወሰደች ...
Read More »የአብዲ ዒሌና የሽንሌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ድርድር ያለውጤት ተበተነ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) የአብዲ ዒሌና የሽንሌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ድርድር ያለውጤት ተበተነ:: አንድ ሳምንት የሞላውን ተቃውሞ ለማስቆም በአብዲ ዒሌ በኩል ግፊት የተደረገበት ድርድር የከሸፈው በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች እንደማይፈቱ በመገለፁ ነው:: የክልሉን ምክትል ፕሬዝዳንት የላከው አብዲ ዒሌ በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ በመሆናቸው ልንፈታቸው አንችልም የሚል መልስ ለሽማግሌዎቹ ተነግሯቸል :: ይህ በእንዲህ እንዳለም በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የተጀመረው ተቃውሞ መቀጠሉ ታውቋል:: ድርድሩ ...
Read More »የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ
የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችና ጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል። ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ዙሪያ እና አገሪቱ መውሰድ ስለሚገባት እርምጃ አስተያቶችን ሰብስበዋል። በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ወደ ...
Read More »በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው
በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በረባራት እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች በአቶ አብዲ ኢሌ አገዛዝ በመማረር የጀመሩትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። በርካታ ወጣቶች በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮች፣ የእስር ዘመቻው ተጠናክሮ በመቀጠሉ አካባቢው በውጥረት እንደሚሞላ አድርጎታል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በአካባባቢው በማሰማራት ተቃውሞውን ለማፈን ጥረት መደረጉን የአካባቢው ...
Read More »“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ
“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ይህን የተናገሩት በቤተመንግስት የመሸኛ ዝግጅት በተደረገላቸው ወቅት ነው። አቶ ሃይለማርያም ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያላቸውን አድናቆት ከገለጹ በሁዋላ በአገሪቱ እየነፈሰ ያለው የለውጥ ንፋስ ህዝቡ በሚፈልገው መሰረት እንዲከናወን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው፡፡ ለውጡ የሁላችንንም ፍላጎት ያማከለ እንዲሆን ልንረባረብ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝርፊያ እየተፈጸመባቸው ነው
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝርፊያ እየተፈጸመባቸው ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢትዮጵያኑ እንዳሉት የአገሪቱ ዜጎች የፖለቲካ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ከወጡ በሁዋላ የስደተኞችን ንብረቶች በመዝረፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት፣ በዝርፊያው በርካታ ኢትዮጵያውያን ሃብትና ንብረታቸውን አጥተዋል። በሌላ በኩል ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሞዛንቢክ ውስጥ ተያዙ በሕገወጥ መንገድ ሞዛምቢክን አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ...
Read More »በካናዳ ቶሮንቶ አንድ እቃ ጫኝ መለስተኛ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 10 አካል ጉዳተኞች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010) በካናዳ ቶሮንቶ አንድ እቃ ጫኝ መለስተኛ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 10 አካል ጉዳተኞችን ሲገድል 15 ማቁሰሉ ተሰማ። የካናዳ ፖሊስ አደጋው ሆን ተብሎ ነው የተፈጸመው ቢልም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግን ማወቅ አልተቻለም ሲል ገልጿል። የአደጋው ፈጻሚ የ25 አመቱ አሌክ ሚናሲያ አደጋውን ካደረሰ በኋላ ለመሸሽ ቢሞክርም ብዙም ሳይርቅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። በካናዳ ቶሮንቶ ዮንጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ...
Read More »አቶ ጌታቸው አምባዬ ከስልጣን የተነሱት በሙስናና እስረኞችን አልፈታም በማለታቸው ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2010)በኢትዮጵያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሆነው የሰሩት አቶ ጌታቸው አምባዬ ከስልጣን የተነሱት ከሙስናና ከሕወሃት ጋር ባላቸው ቅርበት እስረኞችን አልፈታም እያሉ በማስቸገራቸው መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። አቶ ጌታቸው አምባዬ በተለይም የዋልድባ መነኮሳትን ላለመልቀቅ በማቅማማታቸው ከእስር ሳይፈቱ እንዲዘገዩ አድርገዋል ተብሏል። የቀድሞው አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ በነባሩም ይሁን በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መነኮሳቱን እንዲፈቱ ተጠይቀው እምቢተኛ ሆነው መቆየታቸውንም ለማወቅ ...
Read More »