የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ አለማቀፍ የሀይማኖት ነጻነት አስጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ የሳውዲ አረቢያ መንግስት እስረኞችን ያሰረበትን ትክክለኛ ምክንያት ይፋ እስካላደረገ ድረስ፣ መልቀቅ አለበት ብሎአል። እስረኞቹ በእስር ቤት ውስጥ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን፣ የእስልምና ሀይማኖትን እንዲቀበሉ እየተገደዱ መሆኑን ድርጅቱ አክሎ ገልጧል። 35 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የታሰሩት ሴቶችና ወንዶች በአንድ ላይ በመሆን አምልከዋል በሚል ምክንያት ነው። ሳውዲአረቢያ የቤተሰብ አባል ያልሆኑ ሴቶችና ...
Read More »የሰበታ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሽመልስ ሀሰኖ በ10 አመት እና በ40 ሺ ብር ተቀጡ
የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሙስና ጋር በተያያዘ በእስር ላይ በሚገኙት በርካታ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱን ዘጋቢአችን ገልጧል። ከአቶ አባዱላ ገመደ እና ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሲነገርላቸው በቆዩት በከንቲባ ሽመልስ ላይ የ10 አመት ፍርድ ሲያስተላልፍ፣ ከእርሳቸው ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ግበረ አበሮች ላይ ደግሞ ከ8 አመት እስከ 9 ወር በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ወስኗል ...
Read More »መለስ በመድረክ ውስጥ ያልታሰሩ የሽብርተኛ ድርጅቶች አባላት አሉ ብለው የተናገሩትን የመድረኩ መሪ አጣጣሉት
የካቲት 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ 99 ነጥብ ስድስት በመቶ በራሳቸው የፓርቲ አባላት በተያዘው ፓርላማ ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር በመድረክ ውስጥ ለፍርድ ቤት በቂ የሆነ ማስረጃ ያላገኘንባቸው የአሸባሪ ድርጅቶች አባላት አሉ በማለት መናገራቸው ይታወቃል። የመድረኩ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ በበኩላቸው አቶ መለስ ዜናዊ በሰው ህሊና ውስጥ ያለውን ነገር እንዴት እንደሚያውቁ አላውቅም ሲሉ መልሰዋል:: አቶ መለስ ዜናዊ ...
Read More »የጋምቤላውን ከፍተኛ ባለስልጣን አስገድለዋል የተባሉ ተያዙ፤ ሶስት ባለስልጣናትን ለመግደል እቅድ ነበራቸው
የካቲት 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጋምቤላውን ከፍተኛ ባለስልጣን አስገድለዋል የተባሉ አንዳንድ ባለስልጣናት መያዛቸው ተሰማ፣ ሶስት ባለስልጣናትን ለመግደል እቅድ ነበራቸው ተብሎአል የኢሳት የጋምቤላ ወኪል እንደገለጠው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ በስውር የደህንነት አባል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ጌታቸው አንኮሬን ያስገደሉት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። ግለሰቡ የከምባታ ተወላጅ ሆነው የህወሀት ሰላይ በመሆን የክልሉ ነዋሪዎችን ሲያሰቃዩ፣ እርስ በርስ ለመከፋፈል ሲሞክሩ መቆየታቸውን መረጃዎች ...
Read More »ዜጎች ሀሳባቸውን በመግለጣቸው አሸባሪ እየተባሉ በመታሰር ላይ ናቸው ሲሉ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ተናገሩ
ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-99 በመቶ የአንድ ፓርቲ ሰዎች በታጨቁበት ፓርላማ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ዛሬ የአቶ መለስ ዜናዊን የስድስት ወራት ሪፖርት ካደመጡ በሁዋላ በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ማቅረባቸውን ዘጋቢያችን ገልጧል። ዜጎች ሀሳባቸውን በገለጡ አሸባሪ ይባላሉ በዚህም የተነሳ የፖለቲካ መህዳሩ እየጠበበ መምጣቱን አቶ ግርማ ተናግረዋል። አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ህግ በዓለም ላይ ምርጥ ከተባሉት ...
Read More »የ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር የፃፉት ደብዳቤ ይፋ ሆነ
ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ተከሰው የ 17 ዓመት እስራት የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገብረ-እግዚአብሔር የፃፉት ደብዳቤ ይፋ ሆነ። አቶ ዘሪሁን ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት በወረዱበት ቀን ለፍኖተ-ነፃነት አንድ ደብዳቤ ጽፈው እንደነበር ያወሳው የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል፤ ጉዳያቸው ገና በፍርድ ቤት እየታየ ስለነበር በወቅቱ ደብዳቤውን ሊያወጣው እንዳልቻለ በመጥቀስ፤በትናንትናው ዕትሙ ይፋ አድርጎታል። አቶ ...
Read More »ካናዳ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለሚፈጽመው የግዳጅ ሰፈራ እርዳታ በመስጠቷ ተቃውሞ ቀረበባት
ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሂዩማን ራይትስ ዎች ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፤ብዙዎችን ለችግርና ለመከራ ህይወት ለዳረገውና ኢትዮጵያ እየፈፀመች ላለው የግዳጅ ሰፈራ የገንዘብ እርዳታ አድርጋለች ያላትን ካናዳን መውቀሱ ይታወሳል። የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ይፋ መሆን ፤ግብር ከፋዩን የካናዳ ህዝብ እያነጋገረ እንደሆነ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት፤ የአገሪቱ ታላቁ ራዲዮ የሆነው “ራዲዮ ካናዳ ኢንተርናሽናል” በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጡ ዘንድ፤ የድርጅቱን አንድ መርማሪ በመጋበዝ ...
Read More »በባለስልጣናትና በህዝቡ አለመግባባት ሳቢያ፤ በሀዲያ የተጀመረው ስብሰባ ተቋረጠ
ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ፍኖት ዘገባ፤በመልካም አስተዳደር እጦትና በመሬት ወረራ ዙሪያ በሀዲያ ዞን የተጀመረው ስብሰባ የተቋረጠው፤ መድረክ ሲመሩ በነበሩት ባለስልጣናትና በተሰብሳቢው ህዝብ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፤ ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ በመውጣቱ ነው። የክልሉ እና የዞኑ አመራሮች በተገኙበት በሆሣዕና ከተማ ባለፈው እሁድ ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም በሀዲያ የባህል አዳራሽ የተጠራው ይህ ስብሰባ፤ በዞኑ ስላለው የመልካም አስተዳደር እጦትና የመሬት ወረራ ...
Read More »የታሰሩ ወጣቶች ቁጥር መንግስት ይፋ ካደረገው እንደሚበልጥ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት አጋለጠ
ጥር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፉት አራት ወራት የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች የህዝብ አመጽ ለማስነሳት ይቀሰቀሳሉ ብለው የሰሩዋቸው ወጣቶች ቁጥር መንግስት ይፋ ካደረገው አሀዝ በእጅጉ እንደሚበልጥ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት አጋለጠ ለደህንነቱ ሲባል ስሙን ለመግለጥ የማንፈልገው ወጣት ባለፈው ሳምንት ታስሮበት ከነበረው የታጠቅ እስር ቤት አምልጦ እንዲወጣ በተለያዩ ወገኖች ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ነበር። ወጣቱ ከእስር ቤት አምልጦ እንደወጣ ወዲያውኑ ከኢሳት ...
Read More »የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ዘመዶች መሰጠታቸው ቅሬታ አስነሳ
ጥር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ልደታ አካባቢ የሚገኙ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ዘመዶች መሰጠታቸው ቅሬታ አስነሳ በልደታ አካባቢ በመገንባት ላይ ያሉት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ፣ ከተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ዘግይተው ቢጠናቀቁም ሰሞኑን እየተሰራ ያለው ድራማ ግን ህዝቡን ያሳዘነ ሆኗል። የኢሳት ምንጮች እንዳሉት ኮንዶሚኒየም ቤቶቹ አስቀድመው ለገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና የባለስልጣናት ዘመዶች ተሰጥተዋል። የአካባቢው ነዋሪ ይህን ቢያውቅም፣ የመንግስትን ይፋዊ መልስ ለመስማት በመፈለግ ...
Read More »