ግንቦት 7 የመለስ መንግስት በኤርትራ ላይ የሰነዘረውን ጥቃት አወገዘ

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ንቅናቄው ባወጣው መግለጫ የመለስ ሠራዊት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚደረገዉን የ ሰላም ጥረት በማደናቅፍና የአለም አቀፉን ህግ በመጣስ የኤርትራን ግዛት ወርሮ ማን አለብኝነት የተሞላበት ወታደራዊ ጥፋት መፈጸሙን አስታውሶ፣  ወታደራዊ ትንኮሳውና ጥቃቱ የአፍሪካን ቀንድ ከዚህ ቀደም ታይቶ ወደ ማይታወቅ ትልቅ የጦርነት እሳት ዉስጥ ሊከት የሚችል የጀብደኝነት ተግባር ነዉ ብሎታል። የወያኔ አገዛዝ ይህንን የምስራቅ አፍሪካን ...

Read More »

ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን በእስረኞች ላይ ጉዳት እንደተፈፀመባቸው ገለፀ

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ታህሳስ  ወር በሳዑዲ አረቢያ  የገናን በዓል ለማክበር በመሰባሰባቸው ለእስር የተዳረጉት 35 ኢትዮጵያውያን አብረዋቸው በታሰሩ ሌሎች እስረኞች ከፍ ያለ ጉዳት እየተፈፀመባቸው መሆኑን ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን ገለጸ። ጂዳ ውስጥ በብሪማን እስር ቤት ውስጥ  በከባድ ወንጀል ከተከሰሱ እስረኞች ጋር  ከታሰሩት ኢትዮጵያውያን አንዱ፦”ያሰሩን  በነፍስ ግድያ ከታሰሩ ወንጀለኞች ጋር ነው።እነዚህ እስረኞች አንድ ቀን በእኛ ላይ ጉዳት ...

Read More »

በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ አድማው ለሁለት ቀናት ይቆያል

መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሃሙስ መጋቢት 13 ቀን 2004 ዓ.ም  ለዓመታት ስንታገልለት በነበረው የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ላይ ሰሞኑን የኢህአዴግ መንግሥት አሳፋሪ ዝቅተኛ ጭማሪ በማድረግ አሹፎብናል ያሉ መምህራን የሁለት ቀን አስቸኳይ የሥራ ማቆም አድማ መቱ፡፡ በአዲስ አበባ ዳርቻዎች የሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች እና በመሐል ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የሁለት ቀን የሥራ ማቆም አድማ ...

Read More »

አቶ አንዷለም አራጌ ደብዳቤ 1 ሺህ ዶላር ተሸጠ

መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ አንዷለም አራጌ ከ እስር ቤት ሆነው የፃፉት ደብዳቤ  የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች ሰሞኑን በ አትላንታ ባዘጋጁት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ፤ 1 ሺህ ዶላር ተሸጠ። የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አንዷለም አራጌ ፤በእስር ቤት ውስጥ በመንግስት አቀነባባሪነት የተደረገበትን ድብደባና የግድያ ሙከራ በስፋት  በዘረዘረበት በዚሁ ደብዳቤ፤ “ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ እኔም ለመሞት ዝግጁ ነኝ”| ማለቱ ይታወሳል። ...

Read More »

በጥንታዊ ና ታሪካዊ ገዳማት ላይ እየተከሰተ ያለው ተከታታይ አደጋ ቁጣ እየቀሰቀሰ ነው

መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርብ ጊዜ ብቻ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይዞታ ስር ባሉ በሦስት ታሪካዊና ጥንታዊ ገዳማት ላይ ከአስር ጊዜ በላይ  የቃጠሎ አደጋ ተከስቷል። በጣና ሀይቅ ዳርቻ በምትገኘው በ ኡራ ኪዳነ-ምህረት፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኘው አሰቦት እና በደብረዘይት አቅራቢያ በሚገኘው በዝቋላ ገዳማት። በተለይ ሰሞኑን በዝቋላ የተነሳው ቃጠሎ በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ ቢደረግበትም  እነሆ ሳይጠፋ ሰባተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። የእምነቱ ...

Read More »

ለሚድሮክ ኩባንያ ሲባል በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና ጉጂ ዞን ቀበሌዎች ተፈናቀሉ

መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለሚድሮክ ኩባንያ ሲባል በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና ጉጂ ዞን ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች፤ ያለ ምንም ካሳ ከቦታቸው እንዲፈናቀሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገለፁ፡፡ ነዋሪዎቹ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት፤ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ፤አካባቢው በወርቅ ማዕድን የበለፀገ በመሆኑ የሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ንብረት ለሆነው ለሚድሮክ ወርቅና ማዕድን ኩባንያ  ለመስጠት  መንግስት በመወሰኑ ነው፡፡ ቀደም ሲል በተመሣሳይ ...

Read More »

የድምጸ-ወያነ ጋዜጠኞች የአረና አባል ሆነው ተገኙ

መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከትጥቅ ትግሉ ጊዜ አንስተው የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ድምፅ የሆነው የድምጸ-ወያነ ራዲዮ አዘጋጆች የነበሩት ጋዜጠኛ ስልጣኑ ህሽ እና ጋዜጠኛ አንዶም ገብረሥላሴ የ አረና ለትግራይ ፓርቲ አባል ሆነው ተገኙ። በዚህም ምክንያት ከሀያ ዓመታት በላይ ከሠሩበት ድምጸ ወያነ ራዲዮ ጣቢያ መባረራቸውን  ፓርቲያቸው አረና ለትግራይ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። የፓርቲውን መግለጫ በመጥቀስ ሳምንታዊው ሰንደቅ እንደዘገበው፤ ከሁለቱ ...

Read More »

ሰበር ዜና * ከሰዓት በኋላ አብዛኛው የአዲስ አበባ ት/ቤቶች መምህራን አድማውን ተቀላቅለዋል

የመምህራኑ አድማ እንደቀጠለ ነው ከሰዓት በኋላ አብዛኛው የአዲስ አበባ   ት/ቤቶች መምህራን አድማውን ተቀላቅለዋል በአንዳንድ ት/ቤቶች መምህራን ያለ ስራ  በጊቢው ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ የኢሀዴግ የፀጥታ  ሀይሎች መምህራኑን ለማስገደድ እየተንቀሳቀሱ ነው

Read More »

ሰበር ዜና * በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ሰበር ዜና በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ *** አድማው ለሁለት ቀናት ይቆያል ከፍተኛ  ውጥረት አለ *** የኢሀዴግ አባላት መምህራንም አድማውን ተቀላቅለዋል *** አድማው ከአወልያ  ጋርተያይዞ  ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ ይችላል ተብሎ  ተፈርቷል::

Read More »

የመንግስት የ5 አመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ የኑሮ ውድነቱን እንዳባባሰው ተገለጠ

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚታየው የኑሮ ውድነት የታችኛውና መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው የመንግስት ሰራተኛው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ ነው። ጤፍ በአዲስ አበባ በኩንታል እስከ 1700 ብር በመሸጥ ላይ ነው። ዘይትና ስኳር ደግሞ ጭራሽ ከገበያ ጠፍተዋል። ለአንዳንድ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በየወሩ ስኳርና ዘይት ለማከፋፋል ሙከራ እየተደረገ ነው። እስከዛሬም መንግስት ስንዴ ከውጭ እያስመጣና ገበያውን እየደጎመ ...

Read More »