አቶ አንዷለም አራጌ ደብዳቤ 1 ሺህ ዶላር ተሸጠ

መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ አንዷለም አራጌ ከ እስር ቤት ሆነው የፃፉት ደብዳቤ  የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች ሰሞኑን በ አትላንታ ባዘጋጁት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ፤ 1 ሺህ ዶላር ተሸጠ።

የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አንዷለም አራጌ ፤በእስር ቤት ውስጥ በመንግስት አቀነባባሪነት የተደረገበትን ድብደባና የግድያ ሙከራ በስፋት  በዘረዘረበት በዚሁ ደብዳቤ፤ “ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ እኔም ለመሞት ዝግጁ ነኝ”| ማለቱ ይታወሳል።

የደብዳቤው ሙሉ ቃል ለተሰብሳቢዎቹ  ከተነበበ በሁዋላ ፤ለጨረታ ቀርቦ አንድ ሺ ዶላር ተሸጧል፡፡” በጨረታ የተገኘው ገቢም፤ ፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣን ለማጠናከር እንደሚውል ተገልጿል።

“በኢህአዴግ አስተዳደር በአገር ቤት ውስጥ ሕይወታቸው ላለፉት ዜጐች የሕሊና ፀሎት በማድረግ በተጀመረው በዚሁ ስብሰባ ላይ፤ የአንድነት የአትላንታ ድጋፍ ሰጪ አካል ሊቀመንበር አቶ ግርማዬ ግዛውና የስብሰባው የክብር እንግዳ የሆኑት የፓርቲው ከፍተኛ

አመራር አቶ ስየ አብርሃ ንግግር አድርገዋል፡  አቶ ስየ በንግግራቸው፦ “በኢትዮጵያ ውስጥ ሙስና መስፋፋቱን  በመጥቀስ፤ሕወሓት የአቶ መለስና የወ/ሮ አዜብ መስፍን ንብረት ሆኗል ብለዋል።

“በኢትዮጵያ  አሁን ያለው የፌዴራል ፖሊስ፤  ተቃዋሚዎችን በኃይል ለመደምሰስ የተቋቋመ ፓራ ሚሊተሪ ነው” ያሉት አቶ ስዬ፤  “አረቦች ፍርሃትን አሸንፈዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኖች በመከራ ውስጥ ስለቆዩ ፍርሃት ውስጥ ናቸው፡፡የታመቀ ቁጣ ‘በቃ!’ ብሎ ሲነሳ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መልክ ይቀየራል”ብለዋል።

ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ ፓርቲ እንዳልሆነም፤ አቶ ስዬ አብራርተዋል። በፖለቲካ ውስጥ ተለዋዋጭ ክስተቶች ብዙ ጊዜ ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ሲናገሩም፦”ለምሳሌ እኔና አቶ ግርማዬ በአንድ ግንባር ላይ እርስ በእርስ ተዋግተናል፡፡

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide