በዱባይ አንድ ኢትዮጵያዊት በአሰሪዋ ተገድላ በጊቢው ውስጥ ተቀብራለች

መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዱባይ አንድ ኢትዮጵያዊት በአሰሪዋ ተገድላ በጊቢው ውስጥ ተቀብራለች የኢትዮጵያ ቆንስላ ዜናው እንዳይወጣ እያባበለ ነበር ተብሎአል:: ታሪኩ የተፈጸመው የዛሬ ሁለት ወር ገዳማ ነው ዱባይ ውስጥ ነው። በአንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ 3 ኢትዮጵያውያውያን እና ሁለት የፊሊፒንስ ዜጋ ተቀጥረው ሲሰሩ ከቆዩ በሁዋላ አንደኛዋ የፈሊፒንስ ዜጋና ኢትዮጵያዊቷ ቤቱን ለቀው ጠፍተው ሲሄዱ ሁለት አትዮጵያውያንና አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ ...

Read More »

መድረክ የፖለቲካ ተጽእኖው በረታብኝ አለ

መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ  ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አዳራሽ ቅዳሜ መጋቢት 22 ቀን 2004 ዓም ስብሰባ ቢጠራም፣ አዳራሹን ያከራየው ድርጅት በመጨረሻ አዳራሹን እንደማያከራይ በመግለጡ በኑሮ ውድነቱና በአዲሱ የሊዝ አዋጅ ዙሪያ ሊካሄድ የነበረውን ስብሰባ ለመሰረዝ ተገዷል። የመድረክ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ መድረክ ስብሰባ ለማካሄድ ከመንግስት ፈቃድ ማግኘቱን እና አስፈላጊውን ...

Read More »

የአፋር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተፋጧል ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ታስረዋል

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመለስ መንግስት በአፋር አካባ ቢ የጀመረው የስኳር ልማት ፕሮጀክት ከተወላጆች ከፍተኛ ተቃውሞ ስለገጠመው ልዩ ሀይሉን እና የመከላከያ ሰራዊት አባላቱን በአካባቢው አሰማርቶ ተወላጆችን በማሰር፣ በመድብደብና በማሰቃየት ላይ ነው። የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ሳይፈቅዱ አካባቢውን ማረስ መጀመሩን የአካባቢው ሰዎች መቃወም በመጀመራቸው ሁለት ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ 8 ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ...

Read More »

በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊቱ አባለት በነዋሪዎች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰዱ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በጋምቤላ በቅርቡ 19 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ ገዳዮችን ለማደን ከፍተኛ ዘመቻ ሲያካሂድ ቢቆይም እስካሁን ድረስ አልተሳካለትም። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዘመቻው አንድም ሽፍታ ያልተያዘ በመሆኑ ሰራዊቱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሽፍቶቹን አውጡ በማለት እያሰቃዩ ነው። የመከላከያ ሰራዊት በጋምቤላ ጸጥታ የማስከበሩን ሀላፊነት ከክልሉ መንግስት ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ በህዝቡ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ከፍተኛ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን በሚሰጠው የትምህርት አይነት ከዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ጋር ሲወዛገቡ የቆዩት ከ1ኛ እስከ 5ኛ አመት የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርት ያቆሙት አሁን ባለው የትምህርት አሰጣጥ ተምረንም ኮብል ድንጋይ ከማንጠፍ ሌላ የሚጠብቀን የለንም በሚል ነው። ዝርዝር ሁኔታውን ለማጣራት ኢሳት ተደጋጋሚ ሙከራ በማድረግ ላይ ነው። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate ...

Read More »

በእግር ኳስ ግጥሚያው አምባሳደሮቹ አለመጫዎታቸው እያነጋገረ ነው

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዳሴውን ግድብ ግንባታ አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መመቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የውጪ አገር ዲፕሎማቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት ጋር የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ብዙሀን መገናኛ ሲዘግቡ ቢሰነብቱም፤አምባሳደሮቹ አለመጫዎታቸው እያነጋገረ ነው። ኢቲቪ ከቀናት በፊት ፤የመንግስት ባለሥልጣናት ከውጪ አምባሳደሮች ጋር የ እግር ኳስ ጨዋታ እንደሚያካሂዱ በማሣወቅና   የአምባሰደሮቹን ቡድን ለመግጠም ባለሥልጣናቱ  ስላደረጉት ዝግጁነት ...

Read More »

ብአዴን ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉትን የአማራ ተወላጆች ካምፕ ውስጥ እንዲገቡ አደረገ

መጋቢት ፳፪ (ሃይ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ጉዳይ አስፈጻሚ እየተባለ ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ብአዴን፣ ከደቡብ ክልል በቤንች ማጅ ዞን በጉራ ፋርዳ ወረዳ በግፍ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የመጡ ወደ 200 የሚጠጉ የአማራ ተወላጆችን ተጠልለው ይገኙበት ከነበረው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲወጡ በማድረግ በሁለት ማጎሪያ ካምፖች እንዲቀመጡ አድርጓል። ተፈናቃዮቹ ወደ አዲስ ...

Read More »

በጋምቤላ አሁንም ትምህርት አልተጀመረም

መጋቢት ፳፪ (ሃይ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ የተጀመረው የመምህራን የስራ ማቆም አድማ በመቀጠሉ እስከ ትናንት ድረስ ትምህርት አልተጀመረም። ኢሳት የክልሉ መምህራን ላለፉት ሁለት ወራት ባጀት የለም በሚል ምክንያት ደሞዝ ሊከፈላቸው ባለመቻሉ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን መዘገቡ ይታወሳል። የጋምቤላ ወኪላችን እንዳለው እስከ ትናንት ድረስ በወረዳው የሚገኙ ዋና ዋና ትምህርት ቤቶች ስራ ያልጀመሩ ሲሆን በቶሎ ስራ ይጀምራሉ ተብሎም አይታሰብም። የጋምቤላ ...

Read More »

የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ተሰግቷል

መጋቢት ፳፪ (ሃይ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የእህል ዋጋ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው። በአዲስ አበባ ጤፍ እስከ 1700 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም ጤፍ በኩንታል እስከ 1500 ብር እየተሸጠ ነው። የእህል ዋጋ መጨመር ብቻ ሳይሆን ስኳርና ዘይትም ከገበያ ጠፍተዋል። ችግሮቹ ተደራርበው ህብረተሰቡን እያስጨነቁ ባለበት ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ደርቅ እንደገና ይከሰታል የሚል ሪፖርት ...

Read More »

መንግስት ከጋምቤላ ክልል ወደ ግማሽ የሚሆነውን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ደግሞ 1/5 ኛውን መሬት ሊሸጠው ነው

መጋቢት ፳፪ (ሃይ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ አገዛዝ የእርሻ መሬቶችን ለባለ ሀብቶች በሊዝ የመሸጡን ሂደት አቋርጣለሁ ባለ በሳምንቱ ፈጣን የመሬት ሽያጭ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ። እንደ ኢትዮጵያ ዛሬ ዘገባ ፤በተለይም በሱዳን አዋሳኝ በሆኑት በጋምቤላና በቤንሻንጉል ክልሎች አንድ ሄክታር መሬት በአመት በ1ዶላር ከ15 ሣንቲም ሂሳብ እየተቸበቸበ የአካባቢው ነዋሪዎቹ ግን መላ ህይወታቸውን ከሚገፉበት ቀዬ በግዳጅ መፈናቀላቸው ከፍተኛ ውግዘት በማስከተሉ ...

Read More »