የኢህአዴግ መንግስት በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የሚያደርገውን አፈና ቀጥሎአል

  መጋቢት ፳፪ (ሃይ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባሳለፍነው ሳምንት ከፍተኛ ተነባቢነትን ያለውን የፍትህ ጋዜጣ ድህረ ገጽ  መዘጋቱን ተከትሎ በዚህ ሳምንት ደግሞ  የተለያዩ ብሎጎች እና ድህረ ገጾች  ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል።  ከቻይና መንግስት የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመተባበር  ዌብሳይቶችን እንዲዘጋ ያደረገው  የኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ ደረጃ የሚዲያን ሃያልነት እና ልዩ ጠቀሜታን ጠንቅቆ እንደተረዳው ያስገነዝባል ። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግስት በአሁን ሰአት ...

Read More »

ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በደቡብ ክልል በርካታ አርሶአደሮች መታሰራቸውን ገለጠ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቀድሞ አጠራሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ከገዢው ፓርቲ በደረሰበት አፈና ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የሚል ስያሜ አገኘው ኢሰመጉ በ118ኛ እና 119ኛ  በከፋ ዞን በገዋታ ወረዳና ዙሪያ ከ1950 ዓም ጀምሮ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና በማህበር እንዲደራጁ እንዲፈቀድላቸው በመጠየቃቸው ከ20 የማያንሱ  ሰዎች ታስረዋል። በዚሁ ጥያቄ የተነሳም 33 ሰዎች ቤት ንበረታቸው ...

Read More »

ሂውማን ራይተስ ወች ታጣቂዎች በንጹሀን ዜጎች ላይ ጅምላ ግድያ እየፈጸሙ ነው አለ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና የሽግግሩ መንግስት ደጋፊ ታጣቂዎች ፣ የአልሸባብ ደጋፊዎች ይሆናሉ ብለው የጠረጡዋቸውን ሰዎች በጅምላ ይገድላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያስራሉ ሲሉ ጠቅሷል። ሂውማን ራይተስ ወች እንደሚለው በባይደዋና በበለተወይም መምህራን ሳይቀሩ ተገድለው ተገኝተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልሸባብ በደፈጣ ውጊያ ወይም ፈንጆችን በማጥመድ በኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትና በሶማሊያ መንግስት ደጋፊ ታጣቂዎች ላይ ...

Read More »

”ዋልድባ በትግራይ ክልል የሚገኝ በመሆኑ፤በልማታችን ላይ ጥያቄ ማንሳት አትችሉም” በማለት አንድ የትግራይ ክልል የደህንነት መኮንን ተናገረ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመኮንኑ ንግግር የተበሳጩት ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ ፦”ዋልድባ የትግሬው ወይም የአማራው ብቻ አይደለም።ዓለማቀፍ ገዳማችን ነው”ሲሉ ገስፀውታል። ብአዴን/ኢህአዴግ በዋልድባ ጉዳይ ከመነኮሳቱና ከ አካባቢው ነዋሪ ጋር ለመነጋገር ሰሞኑን በጎንደር ከተማ በጠራውና በሥኳር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጁ በ አቶ ዓባይ ፀሀዬ በተመራው ስብሳባ ላይ በርካታ ተቃውሞ ከመንፀባረቃቸውም ባሻገር ውይይቱ ያለስምምነት መቋጨቱ ታውቋል። በተለይ የስብሰባው መሪ አቶ አባይ ...

Read More »

ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የአርበኞች ግንባር አባላት ላይ የቅጣት ውሳኔ ሰጠ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔውን ያሳለፈው በ6 የአርበኞች ግንባር አባላት ላይ ሲሆን፣ በአንደኛ ተከሳሽ ሲሳይ ብርሌ የ13 አመት ጽኑ እስራት፣ ከ2ኛ እስከ 6ኛ በተዘረዘሩት ተከሳሾች ቢራራ አለሙ፣ ማንደፍሮ አካልነው፣ ዘመድየ አገዘ፣ መሰለ ድንቁና ቴዎድሮስ አያሌው ላይ ደግሞ የ10 አመት እስራት ፈርዷል። በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾች የአርበኞች ግንባር አባላት በመሆን ...

Read More »

49 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የንጹህ ውሀ ተጠቃሚዎች አይደሉም ተባለ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-49 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የንጹህ ውሀና  ተጠቃሚዎች አይደሉም ፣ 75 ሚሊዮኑ ደግሞ ለንጽና መስጠበቂያ የሚሆን በቆ ውሀ አያገኙም የሚሊኒየም የልማት ግቦችን አሳካለሁ በማለት ሌት ተቀን የሚናገረው የመለስ መንግስት ፣ ከ20 አመታት ከፍተኛ የውጭ እርዳታ በሁዋላ እንኳን የአገሪቱን የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋንን ለማሻሻል አልቻለም። ዘ ግሪን የተባለ ዌይባሳይት በፎቶ ግራፍ አስደግፎ ባቀረበው ዘገባ 82 ...

Read More »

ፕሬዚዳንት ኦቦንግ ኦሞድ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቀ መምህራንም የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፕሬዚዳንቱ ኦቦንግ ኦሞድ ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ መምህራንም የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።   ባለፉት ሳምንታት የመንግስትን ፖሊሲ ይቃወማሉ የተባሉ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሲቪሎች መገደላቸውን ተከትሎ ጋምቤላ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ መዘገባችን ይታወሳል። ከሳምንታት በሁዋላም ውጥረቱ በነበረበት መቀጠሉን ነው ዘጋቢያችን የገለጠው። ሰሞኑን የኑዌርና የመዠንገር ተወላጆች የመሩት ስብሰባ በሶስት የተለያዩ አቅጣጫዎች ...

Read More »

ድህነት መቀነሱን የሚያሳይ በገልለልተኛ ወገን እስካልተሰራ ድረስ ተቀባይነት የለውም ተባለ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት በተገኙበት አንድ ጉባኤ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ያስጠናው የድህነት ቅነሳ ሪፖርት ይፋ መሆኑ ይታወሳል። ጥናቱ ድህነት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መሄዱን የሚያመለክት ሲሆን፣ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀንም ዜናውን ተፈላጊው ህዝብ ዘነድ ለማዳረስ ሲደክሙ ሰንብተዋል። ይሁን እንጅ ገለልተኛ ባለሙያዎች የጥናቱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሀሳቦችን በመሰንዘር ላይ ናቸው። አንድ ስማቸው ...

Read More »

የአለማችን ቱጃር ቢልጌትስ ኢትዮጵያን ጎበኙ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማይክሮሶፍት ባለቤትና ለበርካታ አመታት አለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነው የቆዩት አሜሪካዊው ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል እና ማሊንዳ ፋውዴሽን የተባለው ድረጅታቸው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመጎብኘት ነው። ቢል ጌትስ ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ያስመዘገበችውን ስራ የሚመሰገን ቢሆንም፣ ብዙ መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቢል ጌትስ የአውሮፓ መንግስትታት ለታዳጊ አገሮች የሚሰጡትን እርዳታ እንዳይቀንሱ እየተማጸኑ ...

Read More »

“አርቲስቶች በዓባይ ግድብ ግንባታ ላይ አንድም ነገር መሥራት አልቻልንም” አሉ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስቶችን በመወከል  በህዳሴው ግድብ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ሆኖ  እንዲሳተፍ የተደረገው ሠራዊት ፍቅሬ ይህን ያለው፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ  አርቲስቶች ለዓባይ ግድብ ግንባታ ህብረተሰቡ ያለማቋረጥ እንዲረባረብ በማድረግ በኩል ስለሠሩትና እየሠሩት ስላለው ሥራ ያብራራ ዘንድ በተጠየቀበት ጊዜ ነው። ሠራዊት ለጥያቄው በሰጠው መልስ፦”አርቲስቶች በ ዓባይ ልማት ዙሪያ የተለያየ አስተዋጽኦ ለማበርከት ወንዙ ድረስ ሄደን ቃል ገብተን ...

Read More »