በዱባይ አንድ ኢትዮጵያዊት በአሰሪዋ ተገድላ በጊቢው ውስጥ ተቀብራለች

መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በዱባይ አንድ ኢትዮጵያዊት በአሰሪዋ ተገድላ በጊቢው ውስጥ ተቀብራለች የኢትዮጵያ ቆንስላ ዜናው እንዳይወጣ እያባበለ ነበር ተብሎአል::

ታሪኩ የተፈጸመው የዛሬ ሁለት ወር ገዳማ ነው ዱባይ ውስጥ ነው። በአንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ 3 ኢትዮጵያውያውያን እና ሁለት የፊሊፒንስ ዜጋ ተቀጥረው ሲሰሩ ከቆዩ በሁዋላ አንደኛዋ የፈሊፒንስ ዜጋና ኢትዮጵያዊቷ ቤቱን ለቀው ጠፍተው ሲሄዱ ሁለት አትዮጵያውያንና አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ ቀርተው ነበር። ከቀሩት መካከል አንደኛዋ ኢትዮጵያዊት እና የፊሊፒንሱ ወንድ ሰራተኛ በአሰሪዎቹ ከታረዱ በሁዋላ በግቢው ውስጥ እንዲቀበሩ ተደርጓል። የኢትዮጵያዊቷ ን እና የፊሊፒንሱን ተወላጆች ደም እንድታጸዳ የተጠራቸው ኢትዮጵያዊት ባየችው ነገር በመደንገጥ እንደምንም ከግቢ በመውጣት ሁኔታውን ዱባይ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ አሳውቃለች። የኢትዮጵያ ቆንስላም ዜናው ለማንም እንዳይነገር ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን፣ በሁኔታው እእምሮዋ የታወከችውን ወጣት ሰራተኛ ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ዜናው ይፋ እንዳይወጣ ሲከላከል መቆየቱን በዱባይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አጋልጠዋል።

አእምሮዋ የተጎዳችው ወጣት በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለች ለማወቅ ያልተቻለ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ ቆንስላ ስትማለለስ መሰንበቷ ታውቋል።

በሌላ ዜና ደግሞ በሊባኖስ ኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሰልፍ አደርገዋል

በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ማህበረሰባቸዉ ትኩረት የተነፈገዉ መሆኑ እንዳስቆጣቸው በመግለፅ በባዳሮ የኢትዮጵያ ቆንሱላ ደጃፍ ፊት ለፊት ነው የተቃዉሞ ሰልፍ ያደረጉት።

የእሁድ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን ፍፃሜ ተከትሎ የተቃዉሞ ሰልፈኞቹ ወደ ቆንሱላዉ  በማምራት የሚገጥማቸዉን ችግር ለማዳመጥ ጽ/ቤቱ ፈቃደኛ እንደማይሆንና ስልክም ቢደዉሉ እንደሚዘጋባቸዉ በመግለፅ በዜግነታቸዉ የሚገባቸዉ መብት እንደማይጠበቅላቸዉ አመልክተዋል። 

በህገወጥ መንገድ መግባቱ የተገለፀ ዜጋ በሚገጥመዉ ችግር ሃላፊነት በመፍራት ቆንሱላዉ ትብብር የሚነፍገዉ ሲሆን የዚህን ዜጋ ፓስፖርት ለማደስ ግን ገንዘብ ስለሚያስገኝ ይፈፅምለታል በማለት የተሰማቸዉን ቅሬታ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያዉያኑ በቆንሱላዉ ፊት ለፊት ላደረጉት የተቃዉሞ ሰልፍ ዋናዉ ምክንያት በቅርቡ አሊ ማህፉዝ በተባለ ሊባኖሳዊ አማካይነት በቆንሱላዉ ደጃፍ ላይ ህገወጥ ወከባና እንግልት ተፈፅሞባት ሆስፒታል ከገባች በሁዋላ እራስዋን ማጥፋቷ በተገለፀዉ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ አለም ደቻሳ ደሲሳን የቆንሱላዉ ጽ/ቤት ሊደርስላት አለመቻሉ ያሳደረባቸዉ ቁጭት እንደሆነ ታዉቋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙት ኢትዮጵያዉያን ቁጥራቸዉ እጅግ አነስተኛ የሆነበት ምክንያት ከሰልፈኞቹ መካከል በቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ የተገኙ የቆንሱላዉ ሰራተኞች በሰላማዊ ሰልፉ ቢሳተፉ ፖሊስ ተጠርቶ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ማስፈራሪያ በመሰጠታቸዉ እንደሆነ የሊባኖስ ዴይሊ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እያዉለበለቡና መፈክሮችን እያሰሙ ቁጣቸዉን ከገለፁ በሁዋላ ተቃዉሟቸዉን በፀሎት ማጠናቀቃቸዉን የዜና ምንጩ በተጨማሪ ገልጿል።

በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ኢትዮጵያውያን ከሚደርስባቸው እንግልትና በደል ሊታደጉዋቸው ባለመቻላቸው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። ኢምባሲዎቹ ገንዘብ ከመሰብሰብ እና የድህንነት ስራ ከመስራት ያለፈ ስራ አይሰሩም እየተባሉ ይተቻሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ራፖርተር በአለም ደቻሳ ግድያ ዙሪያ ሙሉ ምርምራ እንዲካሄድ ጠይቋል።

የተመድ የዘመናዊ ባርነት ተከላካይ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ጉልናራ ሻህኒን  የሊባኖስ መንግስት ራሷን ያጠፋቸውን ኢትዮጵያዊቷን የቤት ሰራተኛ የአለም ደቻሳን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተል ጠይቀዋል።

ጉልናራ እንዳሉት በአለም ደቻሳ ላይ የተፈጸመው ድርጊት በአረብ አገራት በሚገኙ በብዙ የቤት ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል የሚያስታውስ ነው።

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide