ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እየተካሄደ ባለው የለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያዊቷ ሶፊያ አሰፋ በ3000 ሜትር የሴቶች መሰናክል የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን፦ የመንፈስ አባቷን የአትሌት እሸቱ ቱራን ድል ደግማለች። አትሌት እሸቱ ቱራ በ1980 በተካሄደው የሞስኮ ኦሎምፒክ በ 3000 መሰናክል የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ በመሆን፤ በኦሎምፒክ የመሰናክል ውድድር ለራሱና ለአገሩ የመጀመሪያ የሆነውን አንጸባራቂ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል። ቆፍጣናዋ ጀፍና ሶፊያ አሰፋ ከ 33 ...
Read More »ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የፍትህ ስርአቱን ብሉሽነት የሚያሳይ ነው ተባለ
ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ያሳለፈውን የቅጣት ውሳኔ ተከትሎ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባወጣቸው መግለጫዎች ላይ ነው ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን የሰጠው። አንድነት ፓርቲ ሰኔ 24 እና ሀምሌ 8 በእነአቶ አንዱአለም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ በጽኑ ማው ገዙ ይታወቃል። የፓርቲው መግለጫ የፍርድ ቤቱን ነጻነት የሚጋፉ ብሎም አደጋ ...
Read More »በኢትዮጵያ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ተከሰተ
ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውጭ ባለሀብቶች የውጭ አገር የንግድ ስራዎችን ለመስራት ኤልሲ ( ሌተር ኦፍ ክሬዲት) ለመክፈት በሚሄዱበት ጊዜም ይሁን ሌሎች ለትምህርት ወይም ለህክምና ወደ ውጭ አገር ለመሄድ የሚፈልጉ ሰዎች ዶላር ለመግዛት ወደ ባንኮች ሲሄዱ፣ ዶላር የለም በሚል እንደሚመለሱ ታውቋል። አቶ መለስ ከ6 ወራት በፊትበቂ የሆነ የዶላር ክምችት መኖሩን ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ አሁን የታየውን የዶላር እጥረት ምን ...
Read More »የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በዕፅ ማዘዋወር ተይዘው ስለተቀጡት ዲፕሎማት የማውቀው ነገር የለም አለ
ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በለንደን- ሔትሮ አውሮፕላን ማረፊያ 56 ኪሎ ግራም ካናቢስ ሲያዘዋውሩ ስለተያዙት ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ጉዳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንም አላውቅም አለ። በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቪዛ ክፍል ውስጥ ሠራተኛ የነበሩት ወይዘሮ አመለወርቅ ወንድማገኝ 160 ሺሕ ፓውንድ ዋጋ ያለው የካናቢስ ዕፅ ሲያዘዋውሩ ተይዘው፣ ባለፈው ሳምንት የ 33 ወር እስራት እንደተፈረደባቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ...
Read More »በሳዑዲ-አረቢያ 35 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ተጠርዘው ከአገር ተባረሩ
ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ከ7ወራት በላይ በእስር ቤት ሲያሰቃያቸው የነበሩ 35 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ባሳለፍነው ሳምንት ከአገሪቱ ማባረሩ ተገለፀ። እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ተይዘው የታሰሩት፣ ባለፈው ታህሳስ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በጅዳ ከተማ በአንደኛው ጓደኛቸው ቤት ተሰባስበው በመፀለይ ላይ ሳሉ ሲሆን፣ በእስር ላይ ሳሉ ሃይማኖታቸውን በግዴታ እንዲቀይሩ ከፍተኛ ማስፈራሪያና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ዓለም አቀፍ የክርስቲያኖች ድርጅት አስታውቋል። ...
Read More »በሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘር ቋንቋና ሃይማኖት ያለየው በሜልበርን የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየፈጸመ ያለው ኢ.ሰባዊና ኢ.ፍትሃዊ ተግባር እንዳስቆጣው ቅዳሜ ኦገስት 4 ቀን ባደረገው ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ገለጸ። በመቶዎች የሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ በሜልበርን ፓርላሜንት ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሞውን ማሰማት የጀመረው ከረፋዱ 4 ሰአት ጀምሮ ነበር። በዚሁ የተቃውሞ ሰልፍ በሜልበርን የምስራቅ አፍሪካ ሙስሊም ማህበረሰብ ተወካይና ...
Read More »አትሌት ቲኪ ገላና የኦሎምፒክ ክብረ-ወሰን ሰበረች
ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የበለንደን ኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶን ውድድር በአትሌት ተኪ ገላና የተወከለችው ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነች። ኢትዮጵያ በ ኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሸነፈችው፤ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1996 ዓመተ ምህረት አትላንታ ላይ በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር በፋጡማ ሮባ አማካይነት ነው። በጠይሟ እንስት አንበሳ በቲኪ ገላና የተገኘው የለንደኑ ማራቶን ውጤት፤ ኢትዮጵያ ከ 16 ዓመት በሁዋላ በኦሎምፒክ ...
Read More »ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገር ውስጥ እና በውጭ አገር በሚያደርገውን ትግል አጋር መሆኑን አስታወቀ።
6 August 2012 [ESAT] የኢትዮጵያ ህዝቦች በአገር ውስጥና በውጭ ሃገር በመደራጀት እየታገሉ መሆናቸውን ተገንዝቤያለው ያለው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ ከዚህ የህዝብ አብራክ የወጣ የመከላከያ ሰራዊትም በህቡዕ ተደራጅቶ የትግል አካል ለመሆን መዘጋጀቱን በመግለጫው አስታውቋል:: የንቅናቄው ቃል አቀባይ ሻምበል ኤፍሬም ተካ ከኢሳት ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መከላከያ የፖሊስና የደህንነት ኃይል በህቡዕ ሲደራጅ መቆየቱን አመልክተው ለትግል ለተዘጋጀው የኢትዮጵያ ህዝብ መከታ ሆኖ ከጎኑ ...
Read More »የአቶ መለስ ዜናዊ መጨረሻ አሁንም የኢትዮጵያውያን ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኗል
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እጅግ ውስብስብ የሆኑ ሚስጢሮችን በማውጣት የሚታወቁት አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የአቶ መለስን የደህንነት ሁኔታ ለማወቅ አለመቻላቸው ብዙዎችን አነጋግሯል። አንዳንድ ወገኖች የምእራባዊያን የመገናኛ ብዙሀን ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ መንግስታት የ”ይለፍ መብራት” ካልበራላቸው፣ ዜናዎችን ለማውጣት ፈቃደኛ አይሆኑም በማለት ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ኢትዮጵያ የምእራባዊያን የመገናኛ ብዙሀን የምትስብ አገር ባለመሆኑዋ የመገናኛ ብዙሀኑ ትኩረት እንደነፈጉዋት ይገልጣሉ። በመሀሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »በደቡብ ክልል በፕሬዚዳንቱና በአፈ ጉባኤዋ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክር ቤቱ ለሁለት ተከፈለ
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ማክሰኞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው “የሲዳማ ጥያቄ ፣ ወቅታዊ አለመሆኑንና አብዛኛውን ህዝብ የማይወክል መሆኑን” ተናገሩ በማለት ለማግባባት ሞክረው እንደከሸፈባቸው መዘገባችን ይታወሳል። ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ከሌሎች የመገናኛ ብዙሀን የተወከሉ ጋዜጠኞች በስፍራው ተገኝተው “የሲዳማ ጥያቄ የጸረ ሰላም ሀይሎች ጥያቄ ነው” በማለት ይዘግባሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ...
Read More »