Amsterdam

የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ፖሊስ አዛዥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ፖሊስ አዛዥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ኮሎኔል ጉዕሽ ከባቢሌ ወደ ሃረር ሲጓዙ ዳካታ በሚባል ቦታ ላይ ሃምሌ 28 ቀን 2010 ዓም ባልታወቁ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል። አዛዡ ወደ ባቢሌ ብቻቸውን ተጉዘው እንደነበር የሚገለጹት ምንጮች፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ከመኪናቸው አውርደው ገድለዋቸዋል። አስከሬናቸው ሃምሌ 29 ቀን 2010 በምስራቅ እዝ አባላት ...

Read More »

የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከጉጂ ዞን የተፈናቀሉ የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላትን ወደ ቦታቸው ለመመለስ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና የጌዲዮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሃይለማርያም ተስፋዬ ህዝቡን ያነጋገሩ ቢሆንም፣ ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ህዝቡ ተቃውሞውን በሰልፍ ገልጿል። ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው ከመመለሳቸው በፊት የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው፣ ለወደመባቸው ንብረትም አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸው ...

Read More »

በኮምቦልቻ የባቡር ሃዲድ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

በኮምቦልቻ የባቡር ሃዲድ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ያፒ መርከዚ በተባለ የቱርክ ኩባንያ ከ አዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ በሚሰራው የባቡር መንገድ ዝርጋታ ስራ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ትናንት ወደ አደባባይ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ ከደቡብ ወሎ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ከኩባንያው መሪዎች ጋር ለመነጋጋር ቀጠሮ የያዙ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱ ለጥያቄያቸው ...

Read More »

በመስቀል ዓደባባይ የቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ቀጠሮው ተራዘመ

በመስቀል ዓደባባይ የቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ቀጠሮው ተራዘመ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገቡት የለውጥ ጅምሮችን በመደገፍ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም የምስጋና እና የድጋፍ ሰልፍ ላይ የቦንብ ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል። በወቅቱ የደረሰውን ጥቃት አቀናብረዋል፣ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ...

Read More »

በጅግጅጋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

በጅግጅጋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ከተቆጣጠረ ከትናንት ጀምሮ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ቤቶቻቸው የተዘረፉባቸው እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት የወደሙባቸው ዜጎች በብስጭት ተቃውሞ ለማድረግ ቢያስቡም፣ የአገር ሽማግሌዎች በቀልን በበቀል መመለስ ትክክል አይደለም በማለት እንዳረጋጉዋቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ ከስልጣን የተነሱ ሲሆን ፣ በዛሬው እለት በቁጥጥር ...

Read More »

በተርጫ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው።

በተርጫ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ትናንት የተጀመረው ተቃውሞ በመከለከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብነት ቢበርድም ፣ ዛሬም ከፍተኛ ውጥረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በከተማው ለደረሰው ጥፋት ባለስልጣናቱን ተጠያቄ የደርጋሉ። ችግሩ እንዴት እንደተነሳ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑትን መመህር ፍሰሃ ተስፋዬን አነጋግረናቸዋል።

Read More »

“ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በየትኛውም መንገድ ተቀባይነት የሌለው የሕዝብ ጠላትነት ተግባር ነው” ሲል ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ

“ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በየትኛውም መንገድ ተቀባይነት የሌለው የሕዝብ ጠላትነት ተግባር ነው” ሲል ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በከፈሉት መራር መስዋዕትነት ባለፉት አራት ወራት አገራዊ አንድነት እና መግባባት፤ እንዲሁም የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በአንፃራዊነት መከበራቸውን፤ ...

Read More »

በጅግጅጋ የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን መቆጣጠሩን እንዲሁም በሶማሊ ክልል የነበረውን ሁኔታ ሳፋ አድርገን እንዘግባለን።

(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)በጅግጅጋ የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ተቆጣጠረ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የአብዲ ኢሌ ልዩ ሃይል አባላት እና እርሱ ያደራጃቸው ወጣቶች በክልሉ በሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት በመፈጸም፣ የበርካታ ዜጎች ህይወት እንዲጠፋ አድርገዋል። ከ7 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። የሌሎች ብሄሮች እና አብዲ ኢሌን ይቃወማሉ የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ንብረት ተዘርፏል፤ ከፍተኛ ሃብትና ንብረትም ወድሟል። በርካታ ዜጎች ሚካኤል ቤተከርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ያለፉትን 2 ...

Read More »

(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)የሶማሌ ክልል ተወካዮች የጋራ የምክክር መድረክ ላለፉት ሦስት ቀናት በድሬዳዋ ሲያካሂዱ የቆዩትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ባወጡት መግለጫ ክልሉን እየመሩ ያሉ ሰዎች ከሥልጣናቸው እንዲነሱና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። ዛሬም ሰዎች እየተገደሉ ነው።

Read More »

በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ላይ በተነሳ ተቃውሞ ከፍተኛ ውድመት ደረሰ

(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)ተቃውሞው የክልሉ መንግስት ከመንገድ ስራ ጋር በተያያዘ በሰጠው የተሳሳተ መረጃ ነው። ይህን ተከትሎ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሎአል። ይህንን ተከትሎ የከተማው ህዝብ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን አቃጥሏል። በዛሬው ተቃውሞ የተርጫ ከተማ ከንቲባ የአቶ አንበሰ ኡርካ ንግድቤትና መኖሪያ ቤት፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አንድነት አሸናፊ መኖሪያ ቤት፣ የገቢዎችና ማዘጋጃ ቤቶች ተቃጥለዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች የዞኑ አስተዳዳሪና የድርጅት ጽ/ቤትን ተጠያቂ ...

Read More »