የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከጉጂ ዞን የተፈናቀሉ የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላትን ወደ ቦታቸው ለመመለስ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና የጌዲዮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሃይለማርያም ተስፋዬ ህዝቡን ያነጋገሩ ቢሆንም፣ ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ህዝቡ ተቃውሞውን በሰልፍ ገልጿል። ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው ከመመለሳቸው በፊት የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው፣ ለወደመባቸው ንብረትም አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።
ህዝቡ ተቃውሞውን በሰልፍ ሲገልጽ፣ ወታደሮች ጥይት በመተኮስ ለመቆጣጠር ባደረጉት ሙከራ ሰዎች መጎዳታቸውም ታውቋል። የክልሉ ፕሬዚዳንትና የዞኑ አስተዳዳሪም በወታደሮች ታጅበው ወደ ዲላ ተወስደዋል።