መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ባሰባሰቡት መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቁጥር አንድ ችግር ብሎ የሚያነሳው የኑሮው ውድነቱን ነው። የኑሮ ውድነቱ ከዛሬ ነገ ይቀንሳል በማለት ህዝቡ ተስፋ ቢያደርግም፣ ውድነቱ ግን ከመጨመር ውጭ ሊቀንስ አልቻለም። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ መምህር ፣ ሶስት ልጆቻቸውን ለማስተማር ቀርቶ አብልተው ለማኖር እንደተቸገሩ ገልጠዋል። በኑሮ ውድነቱ የተነሳ አመታዊ በአላትን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአልሸባብ ተዋጊዮች ኪስማዮን ለቀው ወጡ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶማሊያ መንግስትና በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ስም የዘመተው የኬንያ ጦር በጋር በመሆን በአልሸባብ ላይ የከፈቱት ዘመቻ ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አልሸባብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ የሚያስገኝለትን የወደብ ከተማ የሆነችውን ኪስማዩን ለመልቀቅ መገደዱ፣ የድርጅቱን ፍጻሜ ሊያቃርበው እንደሚችል ነው ዘገባዎች የሚያመለክቱት። የሶማሊያ ጦር አዛዥ እንደተናገሩት አልሸባብ ኪስማዩን ለቆ ቢወጣም ፣ የአፍሪካ ህብረት ጦር ...
Read More »በመተማ ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ ከ120 በላይ ሰዎች ታሰሩ
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት እንዳረጋገጠው በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ደስታችሁን ገልጣችሁዋል የተባሉ ከ120 በላይ ሰዎች ታስረው ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። የመተማ አካባቢ ነዋሪዎች እንደገለጡት አቶ መለስ ዜናዊ ሞታቸው እንደተሰማ ” መለስ እንኳንም ሞተ፣ ተገላገልን” በማለት በመጠጥ ቤቶች ውስጥም ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ደስታቸውን ገልጠዋል የተባሉ ከ120 በላይ ሰዎች ታስረዋል። ግለሰቦቹ ...
Read More »በመንግስት እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል ድርድር ቢጀመርም፡ ጦርነቱም እንደ ቀጠለ ነው
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመንግስት እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል ድርድር ቢጀመርም፡ ጦርነቱም እንደ ቀጠለ ነው ሲሉ የግንባሩ ቃል አቀባይ ገለጡ የኦብነግ ቃል አቀባይ አቶ ሀሰን አብዱላሂ በኬንያ አደራዳሪነት ተከታታይ የሆኑ ድርድሮችን ለማካሄድ ስምምነት ላይ ቢደረስም ፣ ጦርነቱ ግን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል። “እናንተ ከመንግስት ጋር ድርድር ውስጥ የገባችሁት ሀይላችሁ እየተዳከመ በመምጣቱ ነውን?” በሚል ...
Read More »በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ሲሉ ተናገሩ
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ከወላይታ ብሄረሰብ የተገኙ መሆናቸው በክልሉ ነዋሪዎች ዘንድ ምን ስሜት ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ኢሳት ከተለያዩ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር ቃለምልልስ አድርጓል። አንዳንድ ነዋሪዎች የእርሳቸው መመረጥ ደስታ የፈጠረላቸው መሆኑን ቢናገሩም፤ አብዛኞቹ ግን ሹመቱ የይስሙላ በመሆኑ ምንም ስሜት እንዳልሰጣቸው ይናገራሉ። አቶ ኦታራ ኦሼ የጋሞጎፋ ዞን ተወላጅ ናቸው። የአቶ ሀይለማርያም ሹመት ” ...
Read More »የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሙከራ ስርጭት ጀመረ
መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በገዢው ፓርቲ አፈና ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ታፍኖ ቆየው ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የሙከራ ስርጭት ጀምሯል። ከኒው ሆርን ቴሌቪዥን የአየር ስርጭት በመግዛት በሚቀጥሉት ቀናት ሙሉ ስርጭቱን የሚጀምረው ኢሳት፣ በቅርቡ ተጨማሪ የራሱ ሙሉ የስርጭት ጊዜ ይኖረዋል። አዲሱ ስርጭት በኤ ቢ 7 በ7 ዲግሪ ዌስት ላይ በ 10815 ሜጋ ሀርዝ፣ በ27 ሺ 500 ...
Read More »የደመራ በአል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ
መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላላቅ ሀይማኖታዊ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የደመራ በአል በዛሬው እለት በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። የደመራ በአል ንግስት ኢሌኒ እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ለመፈለግ የተጠቀመችበትን ደመራ እና የእጣን ጭስ ለመዘከር የሚደረግ ሀይማኖታዊ በአል ነው። የቤተክርስቲያኑዋ መጽሀፍት እንደሚያመለክቱት ግማደ መስቀሉ በአጼ ዳዊትና በልጃቸው ባአጼ ዘርአያቆብ በአስራ አምስተኛም ምእተ አመት መግቢያ ላይ ...
Read More »በደቡብ ክልል ” መለስ ዜናዊ እንኳን ሞተ” ብለው ተናግረዋል የተባሉ 80 ሰዎች ታሰሩ
መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ አርሶአደሮች፣ ” መለስ ዜናዊ እንኳንም ሞተ፣ አናዝንም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል በሚል ነው የወረዳው አቃቢ ህግ ክስ ያቀረበባቸው። የክስ መዝገቡ እንደሚያመለክተው አርሶ አደሮቹ በኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 4 /86 ሀ ላይ የተደነገገውን ተላልፈዋ ል። በመዝገብ ቁጥር 4103/30/2004 ፣ በ ቀን ጻጉሜ 1፣ 2004 በተጻፈው የክስ ቻርጅ ...
Read More »የኦሮሚያ ቴሌቪዥን በኢቲቪ ምክንያት ከዓረብ ሳተላይት ተባረረ
መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮምኛ ቋንቋ የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሰራጨት ውል ገብቶ ሥራ የጀመረው በኦሮሚያ ክልል መንግስት የሚተዳደረው የኦሮሚያ ቴሌቪዥን የኢትዮጽያ ቴሌቪዥንን(ኢቲቪ) ፕሮግራሞች በአማርኛ ቋንቋ ማስተላለፍ ከመጀመሩ ጋር ተያይዞ ከውል ውጪ ተንቀሳቅሰሃል በሚል ከዓረብ ሳት መባረሩ ተጠቆመ፡፡ ቀደም ብሎ ከዓረብ ሳት ጋር ውል የገቡ ጣቢያዎችን ጃም በማድረግ ወይም በማፈን ክስ ቀርቦበት ከዓረብ ሳት የተባረረው ...
Read More »የኦህዴድ ካድሬዎች የአቶ ሀይለማርያምን ሹመት በመቃወማቸው በኦነግነት እየተከሰሱ ነው
መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ካድሬዎች፣ ኦህዴድ ተገቢውን የስልጣን ቦታ አለገኘም በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን መቀጠላቸውን ተከትሎ በርካታ ካድሬዎች በኦነግነት እየተወነጀሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙት የኦህዴድ መሪዎች ሹመቱን ከመቀበል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም በማለት አቋማቸውን ግልጽ በማድረግ ካድሬዎቻቸውን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም፣ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ እና ተራ አባላቱ ...
Read More »