የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ መንግስት ከሙስሊም ጥያቄ አቅራቢዎች ተወካዮች ጋር ሲወያይ ከቆየ በሁዋላ አብዛኞቹን በሽብረተኝነት ከሶ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ ማድረጉንና ክሳቸውም እየታየ ባለበት ወቅት በህገ መንግስቱ የተደነገገውን ማንም ሰው ወንጀለኛነቱ በፍርድ ቤት እስኪረጋገጥ ድረስ እንደንጹህ የመቆጠር መብትን በመታገስና ተከሳሾች ራሳቸው ጥፋተኞች መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ በሚያስገድድ ሁኔታ የዞጎችን ስእብና የሚያራክስ ዘጋቢ ማሳየቱን ገልጿል። ፓርቲው ፣ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
መንግስት 850 ሺ ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ እየገባ ነው አለ
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 21 አመታት ኢትዮጵያን በምግብ እራሱዋን እንደሚያስችል ቃል ሲገባ የነበረው የኢህአዴግ መንግስት በቅርቡ ከውጭ የተገዛውን 850 ሺ ኩንታል ስንዴ እንደሚያስገባ የእህል ንግድ ድርጅት አስታውቋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ አስገብቶ ማከፋፈሉን የገለጠ ሲሆን፣ የስንዴው መግባትም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የእህል ዋጋ ንረት ለማለዘብ እንደረዳ ድርጅቱ አስታውቋል። መንግስት በአሁኑ ጊዜ በግብርናው ዘርፍ ...
Read More »ከአርቲስት ታምራት ሞላ ቀብር ጋር በተያያዘ ቅሬታ ቀረበ
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ እንደ ቅርስ ከሚታወቁት አንጋፋ ድምፃውያን አንዱ የሆነው አርቲስት ታምራት ሞላ የምድር ጦር ሰራዊት ኦኬስትራ ማርሽ ሊዘጋጅለት ይገባ ነበር ሲል ሌላው አንጋፋ አርቲስት ዳምጠው አየለ ቅሬታውን ገለጠ። አርቲስት ዳምጠው እርሱ በሚቀጠርበት ጊዜ የሙያ ገምጋሚው አርቲስት ታምራት እንደነበር ገልጾ፣ ለ30 አመታት ያክል ሳይለያዩ በምድር ጦር አገልግሎት መስጠታቸውን አውስቷል። እኛ የምንሰራው ለአገር፣ ለሙያ ...
Read More »የመንግስት ሰራተኞች ምርጫ ካርድ መውሰድ አለመውሰዳቸውን እየተጠየቁ ነው
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በሚያዝያ ወር ለሚካሄደው የአካባቢና የአ/አ አስተዳደር ምርጫ ካርድ መውሰድና አለመውሰዳቸውን በቀጥታ እየተጠየቁ መሆኑን እንዲሁም አንዳንድ አባል ያልሆኑ ነዋሪዎች በካድሬዎችና በደህንነት ሰዎች የኢህአዴግ ዕጩ ሆነው በምርጫው እንዲቀርቡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለአንድ ወር ተካሄዶ ጥር 21 ቀን 2005 ዓ.ም የመራጮች መደበኛ ምዝገባ ቢጠናቀቅም በተለይ በአዲስ አበባ ...
Read More »ኢሳት በስዊድንና በኖርዌይ የተሳካ ዝግጅት አደረገ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብርዋሪ 9፣ 2013 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተካሄድው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰባቢያ ዝግጅት ላይ ከጨረታ ከመቶ ሰላሳ ሺህ የስዊድን ክሮነር ወይም ከሃያ ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ። ይህንን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ የተገኘው በዝግጅቱ ላይ የታላቁ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትሪያክ እና የጸረ ፋሽስት ታጋይ ...
Read More »እውቁና አንጋፋው ድምፃዊ፤ አርቲስ ታምራት ሞላ አረፈ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ እንደ ቅርስ ከሚታወቁት አንጋፋ ድምፃውያን አንዱ የሆነው አርቲስት ታምራት ሞላ አረፈ። ታምራት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ከ 50 ዓመታት በላይ ያገለገለ ስመ-ጥር አርቲስት ነው። ከዓመታት በፊት በሉኪሚያ (የደም ካንሰር) የተጠቃው ተወዳጁ የባህል ቅርስ፤ከህመሙ ጋር ግብ ግብ ሲያደርግ ከቆዬ በሁዋላ ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ ህይወቱ አልፏል። በጎንደር ከተማ የተወለደው እና ገና በወጣትነት በሠራዊቱ ...
Read More »የጸጥታ ሹሙ የኦሮሚያን መሬት ለሶማሊ ክልል አሳልፈን አንሰጥም አሉ
የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 4 ቀናት በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው በክልሉና በሶማሊ ክልል መካከል ያለው የብሄር ግጭት ነው። ከህመማቸው በመጠኑም ቢሆን አገግመው በስብሰባውላይ የተገኙት የክልሉ ፕሬዚዳንት፣ አቶ አለማየሁ አቶምሳ እና የክልሉ የጸጥታ ሹም ፍቃዱ ሰቦቃ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ መልስ ለመስጠተ ሞክረዋል። ከምስራቅ ኦሮሚያ እና ከቦረና ዞን የመጡ የምክር ቤት ...
Read More »በትላንት አርብ የጁማ ጸሎት ተሳትፈዋል የተባሉ ሙስሊሞች ታሰሩ
የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት እንዳመለከተው ከፍተኛ ቁጥር ባስተናገደው የትናንት የጁማ ተቃውሞ በአስተባባሪነት የተጠረጠሩ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ናቸው። በመርካቶ፣ ፒያሳ ፣ ጉለሌ፣ ሰባተኛ እና በሌሎችም አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ተይዘው ታስረዋል። ከታሰሩት መካከል አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ፣ አንዳንዶች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ሌሎች ደግሞ በየአካባቢያቸው ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ተወስደዋል። ...
Read More »ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለስራ የተቀመጡ 18 አምባሳደሮችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጠራ
የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሚኒስቴሩ ይህን እርምጃ የወሰደው ባለፈው ሀሙስ የፓርላማ አባላት ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ጥያቄ ካቀረበ በሁዋላ ነው። የፓርላማ አባላት “በአንድ አገር ውስጥ ሁለት አምባሳደሮችና ሁለት ምክትሎች ይመደባሉ፣ ስራቸው ምንድነው?” በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሚኒስትሩም ” ምን እንደሚሰሩ አላውቅም” የሚል መልስ መስጠታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በአጠቃላይ 30 አምባሳደሮችና ምክትሎች ያለምንም ስራ ደሞዝ እየተከፈላቸው ...
Read More »”የዘንድሮው ምርጫ፤ ምርጫም፣ቅርጫም አይደለም”ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ
የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መራጮች ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት ለዘንድሮው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ዜጐች ቤታቸው በራፍ እየተንኳኳ አስጨናቂ በሆኑ የማግባባት ሂደቶች፤ ሕጉ እና መመሪያው የሚጠይቀው አንዱም መስፈርት መሟላቱ ሳይረጋገጥ ‹‹ሰው›› መሆኑ ብቻ እየታየ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ሲገደዱ ነበር። በምርጫ 97 ወቅት በመራጭነት ለመመዝገብ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግባቸው የነበሩት መስፈርቶች በዘንድሮው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ በቸልተኝነት መታለፋቸውን የጠቆሙ መራጮችና የፖለቲካ ...
Read More »