.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሸህ መሀመድ ሁሴን አል ዓሙዲ ቤቶችን ተነጠቁ

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት ጋር ባላቸው ከመጠን ያለፈ ወዳጅነትና ቅርበት የሚታወቁት ሼህ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ለእግዶች ማረፊያ የተከራዩዋቸውን  ቤቶች እንደተነጠቁ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ሼሁ፤ ከውጪ አገራት ለሚመጡባቸው እንግዶች በአያት ሲ.ኤም. ሲ   25 መኖሪያ ቤቶችን ለውጪ አገር ጎብኝዎች በተሰላ ሂሳብ ተከራይተው +በዶላር ምንዛሬ እየከፈሉ ሲገለገሉባቸው መቆየታቸውን የጠቀሱት እነዚሁ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ  ምንጮች፤ መንግስት ባልተገለጸ ምክንያትና የኪራይ ውሉን በማፍረስ  ...

Read More »

የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት ይቅርታ እንድትጠይቅ ተጠየቀች

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለጸላት። እስከዳር”  አስቂኝም፤አስገራሚም ነገር”በሚል ርዕስ  በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው፦ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልጻለች። “ሰብዐዊ ጥሰት የተፈፀመብን ፣ የተጉላላን ፣ የተሰደብን ፣ የተዛተንብ፣የተደበደብን . . . እኛ፡፡ ይሄ ሆኖ ሳለ ነዉ እንግዲህ ...

Read More »

በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውና መኪና የሚያሸልመው የ ኢሳት ልዩ ቶምቦላ ፤ ወጣ

ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውና መኪና የሚያሸልመው የ ኢሳት ልዩ ቶምቦላ ፤  ታዛቢዎች በተገኙበትና ለሚዲያ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት አምስተርዳም በሚገኘው የ ኢሳት ስቱዲዮ በይፋ ወጥቷል። በመሆኑም መኪና የሚያሸልመው አሸናፊ ቁጥር፦  2657  ሆኗል። የዕጣው አሸናፊ በአስር ቀናት ውስጥ አምስተርዳም፣ ወይም ዋሽንግተን ዲሲ፣ ወይም ለንደን ከሚገኙት ስቱዲዮዎች ለአንድኛቸው በስልክ ወይም በኢሜይል ...

Read More »

ፍጥጫ በሞላበት የብአዴን አባላት ግምገማ ከ 1 መቶ 70 በላይ ሰዎች በአንድ ጊዜ መልቀቂያ አስገቡ

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ2005 ዓም የስራ ክንውንና በ2006 ዓም የስራ እቅድ በሚል ርእስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የኢህአዴግ አባላት ግምገማዎች እየተካሄዱ ነው። በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የሚከተለውን ፖሊሲ መተቸታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግምገማ ደግሞ በርካታ የብአዴን አባላት በፓርቲውና በስርአቱ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ኪራይ ...

Read More »

በቁጫ ወረዳ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች እየተባረሩ ነው

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል። እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ ታስረዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ...

Read More »

የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ታስሮ ወደ ደቡብ ክልል ተወሰደ

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው እንደዘገበው  መላኩ ደምሴ  ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰዷል፡፡ ጋዜጠኛው ለጥያቄ የተወሰደው ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ...

Read More »

ቻልሰ ቴለር ወደ እንግሊዝ ተዛውረው ይታሰራሉ

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ሊቢያው አምባገነን መሪ ቻርለስ ቴለር በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው ዘ ሄግ በሚገኘው አለማፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የ50 አመታት እስር ከተፈረደባቸው በሁዋላ፣ የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ እንደሚፈጽሙ ታውቋል። ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን ጦርነት ወቅት በተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ደግፈዋል በሚል ነበር ጥፋተኛ የተባሉት። የ65 አመቱ ቴለር ቀሪ ህይወታቸውን በእንግሊዝ እስር ቤት እንደሚያጠናቅቁ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

Read More »

የአፍሪካ መሪዎች በአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዙሪያ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ፊታውራሪነት የአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን አሰራር ለመቃወም አፍሪካ መንግስታት በአዲስ አበባ ለአስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸው ታውቋል። ጠ/ሚ ሀይለማርያም ሰሞኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቀርበው የወንጀል ፍርድ ቤቱን ተችተው ነበር። ይህን ተከትሎ በሚመስል ሁኔታ የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር መሪዎችን ከጥቅምት 1 እስከ 2 በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል። የኬንያው ፕሬዚዳንት ...

Read More »

4 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሥራ ዝውውር ሊያደርጉ ነው

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት እንደሚያደርግ ሪፖርተር ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር  በሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር በሆኑት  ዶ/ር ካሱ ኢላላና በፈረንሳይ ...

Read More »

መንግስት ከ9 አመታት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ11 በመቶ በታች እድገት ማስመዝገቡን ገለጸ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 በጀት ዓመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 ነጥብ 7 በመቶ ማደጉን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ በበርካታ ፈተናዎች ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት እድገት መመዝገቡን አወድሰዋል። የግብርና ዘርፍ በ2005 በጀት ዓመት የ7 ነጥብ 1 በመቶ የአገልግሎት ዘርፉ  ደግሞ የ4 ነጥብ 9 በመቶ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል። ዶክተር አብርሃም ኢኮኖሚያዊ እድገቱ የሃገሪቱን ...

Read More »