በቁጫ ወረዳ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች እየተባረሩ ነው

መስከረም (ላሳ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል።

እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ ታስረዋል።

ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ችግር በ48 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሽፋን 45 በመቶ መቀነሱም ታውቋል።

ተቃውሞውን አስተባብሮአል የተባሉት መአቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።