የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት ይቅርታ እንድትጠይቅ ተጠየቀች

ጥቅምት (አንድ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለጸላት።

እስከዳር”  አስቂኝም፤አስገራሚም ነገር”በሚል ርዕስ  በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው፦ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልጻለች።

“ሰብዐዊ ጥሰት የተፈፀመብን ፣ የተጉላላን ፣ የተሰደብን ፣ የተዛተንብ፣የተደበደብን . . . እኛ፡፡ ይሄ ሆኖ ሳለ ነዉ እንግዲህ በእህትሽ ጉዳይ የማረሚያ ቤቱን ስም በየመፅሔቱ አጥፍተሻል  የተባልኩት። ስም ማጥፋት የተባለውም ስለርዕዮት የረሃብ አድማንና ስለ ተፈፀመባት የሰብአዊ መብት ጥሰት መግለጼ ነው”ብላለች-እስከዳር ዓለሙ።

” ስለዚህ ነው ይቅርታ ጠይቂ የተባልኩት” ያለችው እስከዳር፤  “እኔ የምለዉ እነዚህ ሰዎች ይህንን ይቅርታ እንዴት ነዉ የሚወዱት?!!”በማለት  ጠይቃለች።