ቻልሰ ቴለር ወደ እንግሊዝ ተዛውረው ይታሰራሉ

መስከረም (ላሳ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ሊቢያው አምባገነን መሪ ቻርለስ ቴለር በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው ዘ ሄግ በሚገኘው አለማፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የ50 አመታት እስር ከተፈረደባቸው በሁዋላ፣ የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ እንደሚፈጽሙ ታውቋል።

ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን ጦርነት ወቅት በተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ደግፈዋል በሚል ነበር ጥፋተኛ የተባሉት።

የ65 አመቱ ቴለር ቀሪ ህይወታቸውን በእንግሊዝ እስር ቤት እንደሚያጠናቅቁ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።