መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ800 ሺ ያላነሱ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበትን 20ኛ አመት ለማክበር በርካታ ህዝብ በስታዲየሞች ተገንቶ ስነስርአቱን የተከተታለ ሲሆን፣ አንዳንድ ዜጎች በጊዜው ስለነበረው ሁኔታ ሲገለጽ ራሳቸውን ለመቆጣጠር ተስኖአቸው ታይቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባንኪሙን ጭፍጨፋውን ለማስቆም ደርጅታቸው በቂ የሆነ እገዛ ባለማድረጉ ይቅርታ ጠይቀዋል። የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዎሪ ሙሰቬኒ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአንድነት ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ መተላለፉን ፓርቲው አስታወቀ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የጠየቀባቸው ቦታዎች የተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ትላልቅ የመንግስት ተቋማት የሚገኙባቸው በመሆኑ እንዲሁም በእለቱ ሌሎች ተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስለአሉ እውቅና እንደማይሰጥ ማሳወቁን ተከትሎ፣ አንድነት ፓርቲ የሰልፉን ቀን በአንድ ሳምንት አስተላልፏል። ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የፓርቲው የአዲስ አበባ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ...
Read More »በጎንደር ከተማ በህገወጥ መንገድ ቤት ሰርታችሁዋል የተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲያፈርሱ ተጠየቁ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ 15 ሺ በላይ ህዝብ ይኖርበታል ተብሎ በሚገመተው ቀበሌ 18 በገንፎ ቁጭ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን በአስቸኳይ እንዲያፈርሱ የታዘዘው ፣ ቤቱቹ በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል በሚል ነው። ቤቱቹ የተገነቡት ከ10 አመታት በፊት መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች መንግስት ቤቶቹ ሲሰሩ ማስቀም እየቻለ ዛሬ በአካባቢው አስፈላጊው ልማት ከተካሄደ በሁዋላ አፍርሱ ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለዋል። በዛሬው ...
Read More »በሀረር ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዳንዶች ተለቀቁ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀረር ከተከሰተው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ታስረው ከነበሩት ሰዎች መከካል አንዳንዶች ተለቀዋል። ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ ካስተላለፈባቸው 7 ሰዎች መካከል ለአሜሪካ ድምጽ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ተብለው የታሰሩት አቶ ገብረመድህን ገብረ መስቀል እንዲሁም 4ቱ የመብራት ሀይል ሰራተኞችም ተለቀዋል። ይሁን እንጅ በሀረሪ የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኛ የነበረው ጋዜጠኛ ጀማል ዳውድ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝና ...
Read More »በአዋሳ ታቦር ትምህርት ቤት የተነሳውን ግጭት ክልሉ ሆን ብሎ ያቀነባበረው እንደነበር አንድ የደኢዴግ አባል ገለጹ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ግለሰብ እንደገለጹት መድረክ የተባለው የተቃዋሚዎች ስብስብ በአዋሳ ከተማ በርካታ ህዝብ በተገኘበት ስብሰባ ማድረጉን ተከትሎ የተበሳጩት የገዢው ፓርቲ ሰዎች ግጭቱን ተቃዋሚዎች ያስነሱት ነው ለማለት ከውጭ የኒፎርም ለብሰው ወደ ትምህርት ቤቱ የገቡ 45 ተማሪዎች 500 ብር ተከፍሎአቸው እንዲነሳ ማድረጉን ገልጸዋል እቅዱ ሲዘግጀ ነበርኩ ያሉት ግለሰብ፣ ሁኔታው አበሳጭቷቸው ለመናገር እንደተገደዱ ...
Read More »የመከላከያ ሰራዊት በቦዲዮች ላይ ተኩስ ከፍቶ በርካታ ሰዎችን ማቁሰሉን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 24 ቀን በቦዲዎችና በኮንሶዎች መካከል ለአንድ ወር ያክል የቆየውን ግጭት ለማብረድ በሚል ወደ አካባቢው የተጓዘው የመከላከያ ሰራዊት በቦዲዎች ላይ በመትረጊስ የታገዘ ተኩስ በመክፈቱ በርካታ ነዋሪዎች መቁሰላቸውን ከእነዚህም ውስጥ 17 አሮጊቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች በሃና ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ጂንካ የሚገኘው የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ጽ/ቤት ለኢሳት ገልጿል። የመከላከያ ሰራዊቱ የወሰደውን ...
Read More »በመጪው እሁድ በሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት ታሰሩ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳደር የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ ሆኑት አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት እንደገለጹት ምንም እንኳ የተወሰኑ ሰዎች የታሰሩ ቢሆንም፣ ቅስቀሳው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ሀብታሙ ታምሩ፣ አሸናፊ ጨመረዳ እና ደራሲ መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን የቅስቀሳ ወረቀቶችን ሲበትኑ ተይዘው የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል። ለገሃር ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ደግሞ አክሊሉ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ውይይት አደረገ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-” ኢትዮጵያ መረጃ የሚያወጡትና ጋዜጠኞችን ስሚ” በሚል ርእስ የአውሮፓ ህብረት ሶሻሊስቶችና ዲሞክራቶች ከአለም የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ከሆነው ሲፒጄ ጋር በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ በቃሊቲ እስር ቤት ከአንድ አመት በላይ ታስሮ የተለቀቀው ስዊድናዊው ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብየና በኦጋዴን የተካሄደውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያጋልጥ መረጃ ይዞ የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን፣ የአውሮፓ ህብረት ...
Read More »አንድ የአሜሪካ ወታደር 3 ባልደረቦቹን ግደሎ 16ቱን አቆሰለ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢቫን ሎፔዝ የተባለው የ34 አመት ተጠርጣሪ ወታደር ቴክሳስ ውስጥ በሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ነው። ገዳዩ በኢራቅ ሲያገለግል የነበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በድርጊቱ በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ገዳዩ ራሱን ማጥፋቱም ታውቋል።
Read More »በአዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተነሳ ግጭት ተማሪዎች ተጎዱ
መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በተነሳው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚወጡ ተማሪዎችን ሲደበድቡ የታዩ ሲሆን፣ በውስጥ ያሉ ተማሪዎችም እንዲሁ ድንጋይ ሲወረወሩ መታየታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ግጭቱ ተባብሶ በመሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይቶችን በተደጋጋሚ ተኩሰዋል። ታቦር ትምህርት ቤት መዘጋቱንም ለማወቅ ...
Read More »