ግንቦት ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በሃረር የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የንግድ ድርጅታቸው የተቃጠለባቸው 22 ነጋዴዎች ሁከት በማስነሳት የተከፈተባቸው ክስ ወደ ወደ ሽብርተኝነት በመለወጡ፣ ዋስትና ተከልክለው በሃረሪ እስር ቤት እንዲቆዩ መደረጉን የኢሳት ዘጋቢ ገልጿል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነጋዴዎች በዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ አሳልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስና አቃቢ ህግ ክሱን ወደ አሸባሪነት በመለወጣቸው ነጋዴዎቹ ከእስር ቤት እንዳይወጡ ተደርጓል። ከእስረኞቹ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የደቡብ ሱዳን መሪ በሚቀጥለው አመት ምርጫ እንደማይደረግ አስታወቁ
ግንቦት ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳልቫ ኪር ይህን የተናገሩት አዲስ አበባውን የሰላም ስምምነት ፈርመው ከተመለሱ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ በሚቀጥለው አመት ሊካሄድ የታሰበው ምርጫ ለሁለት አመታት የተራዘመው ለሰላም ስምምነቱ እድል ለመስጠት ነው ብለዋል። የሰላም ስምምነቱን የፈረምኩት ተገድጄ ነው ያሉት ኪር፣ ተገደው የፈረሙትን የሰላም ስምምነት ለማክበር ቃል ገብተዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ “ይህን ስምምነት የማትፈርሙ ከሆነ አስራችሁዋለሁ እንዳሏቸው” የገለጹት ሳልቫ ኪር፣ ...
Read More »በጊምቢ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የዘር ፍጅት ሊነሳ እንደሚችል አስጠነቀቁ
ግንቦት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ወለጋ በጊምቢ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ተወላጆች፣ ከአካባቢው እንዲወጡ በሚፈልጉ ወጣቶች ቤታቸው እየተደበደበ መሆኑንና ህይወታቸውም አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል። አንድ ከወሎ አካባቢ የመጡ የመንግስት ሰራተኛ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ባለቤታቸውን አግብተው ለዘመናት ከኖሩ በሁዋላ፣ ሰሞኑን ወደ መጣህበት ሂድ ተብለው በባለቤታቸው ልመና ከሞት እንደተረፉና የቤታቸው ጣሪያም ወንፊት እንደሆነባቸው እያለቀሱ ተናግረዋል። ባለቤታቸውም በከተማዋ ...
Read More »የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ታዘዙ
ግንቦት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር ዩኒቨርስቲው ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ አንዳንድ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት መጀመራቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች እንደገለጹት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወደ ዘመዶቻቸው የተመለሱ በመሆኑ በግቢው ውስጥ የሚታዩት ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው። ተማሪዎች እንደሚሉት በግቢው ውስጥ የሚታየው ሁኔታ አሁንም አስፈሪ ነው። ወደ ...
Read More »ጋዜጠኛ አበበ ገላው ፕሬዚዳንት ኦባማ ለኢትዮጵያ ትኩረት እንዲሰጡ ጠየቀ
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ኦባማ ለዲሞክራቲክ ፓርቲያቸው ገንዘብ ለማሰባሰብ በተገኙበት አንድ ስብሰባ ላይ ነው፣ አበበ ንግግራቸውን አቋርጦ ስለኢትዮጵያ ነጻነት ጥያቄ ያቀረበው። ጋዜጠኛ አበበ ” ፕሬዚዳንት ኦባማ እንወድዎታለን፣ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ነጻነት እንፈልጋለን” ሲል በንግግራቸው ጣልቃ ገብቶ መልእክቱን አስተላልፏል። “ሰምቼሃለሁ፣ ንግግሬን ልጨርስና በሁዋላ እንወያያለን” በማለት ፕሬዚዳንቱ ቢመልሱም፣ አበበ ንግግሩን በመቀጠል ” ኦባማ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ይቁሙ” ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር ሰብአዊ መብት ድርጅት ከኢትዮጵያ ታስክ ፎርስ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን በኦሮሞ፣ በአፋር፣ በጎንደር እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸሙት ግድያዎች በጽኑ አውግዘዋል። ከአስተባባሪዎች አንዱ ሆኑት ዶ/ር ኮንቴ የኢትዮጵያውያኑን ጥያቄ ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ማቅረባቸውንና በሚቀጥለው ሳምንትም ከህብረቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ካተሪና አሽተን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዙን ገልጸዋል። የአውሮፓ ህብረት ...
Read More »የሜሪሲ የውሃ ፕሮጀክት በሙስና ምክንያት ቆመ
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ የትውልድ ከተማ ላይ 62 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የውሃ ፕሮጀክት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ በመክሸፉ የፕሮጀክቱ ማናጀርና የገንዘብ ቤት ሃላፊው በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዚህ ፕሮጀክት ዋና ተጠያቄ የውሃ ቢሮ ሃላፊዋና ፕሮጀክቱን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው የልዩ ፖሊስ አዛዥና ፕሬዚዳንቱ የጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄኔራል አብዲ አደም መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ...
Read More »በሞያሌ በኦነግና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱ ታወቀ
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ በሞያሌ ገጠራማ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በኦነግ ወታደሮች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 2 የኦነግ ወታደሮች ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የመንግስት ወታደሮችም መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ሁለቱ የኦነግ ወታደሮች ቀኑን ሙሉ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተጥለው ይታዩ እንደነበር የአይን እማኖች ገልጸዋል። 4 የመንግስት ወታደሮች በጽኑ ቆስለው ህክምና ሲደረግላቸው እንደነበር የአይን እማኞች አክለው ተናግረዋል። የመንግስት ...
Read More »በቦዴዎችና ኮንሶዎች ማካከል ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትንናት ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በጊዮ ሰፈራ ጠባያ ቦዲዎች ባደረሱት ጥቃት አንድ የኮንሶ ተወላጅ ሲገደል በሰላማጎ ወረዳ ዋና ከተማ ሃና ላይ ደግሞ 2 ሴቶች ቆስለው በጅንካ ሆስፒታል እየታከሙ ነው። አሰበች ጠጉ የተባለች የ4 ልጆች እናት ክፉኛ የቆሰለች ሲሆን፣ ባለቤቷ በእስር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ልጆቿ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል። ሌላዋ ቁስለኛ የስራ ...
Read More »ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር ድፍረቱ እንደሌላቸው አስታወቁ
ሚያዚያ ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድሬዳዋና በሃረር አብያተ ክርስቲያናትና በግለሰቦች ቤት ተጠግተው የሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚታየው ድባብ አስፈሪ መሆን ትምህርት በቶሎ ይጀመራል የሚለውን ተስፋ አጨልሞታል። መንግስት ውጥረቱ መርገቡን በመግለጽ ከግቢ የወጡ ተማሪዎች ተመልሰው እንዲገቡና ትምህርት እንዲጀምሩ ጥሪ ቢያቀርብም፣ አንዳንድ ግቢውን ጎብኝተው የተመለሱ ተማሪዎች ግን ሁኔታው አሁንም አስፈሪ በመሆኑ ትምህርት ለመጀመር ፍላጎት የለንም ብለዋል። አንድ ተማሪ ...
Read More »