.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኦሞ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ህይወታቸው አሣሳቢ አደጋ ውስጥ ወድቋል ተባለ

የካቲት 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በታችኛው ኦሞ ሸለቆ  አካባቢ የሚኖሩ 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሬታቸው ለህንድ ኩባንያዎች በመሰጠቱ ህይወታቸው አሣሳቢ አደጋ ውስጥ መውደቁን አልጀዚራ ዘገበ። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የ አካባቢው ነዋሪዎች  መሬታቸው “ለልማት ይፈለጋል”ተብለው በግዳጅ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ሲሆን፤ ቤታችንን እና ይዞታችንን አንለቅም ያሉ ደግሞ እየታሰሩ ነው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት እነዚህ ዜጎች እየተፈናቀሉ ያሉት፤ የኢትዮጵያ መንግስት በህንድ ...

Read More »

አቶ አንዱዓለም አራጌ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጸመበት

 የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ስም በእስር ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው  አቶ አንዱአለም አራጌ ቃሊቲ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በተቀመጠበት የካቲት 7 ቀን 2004ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ተደብድቧል፡፡ ከድብደባ በሁዋላ ፊቱ ላይ ጠባሳ የሚታይ ሲሆን ጭንቅላቱ አካባቢም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ አቶ አንዱአለም ለወንድሙ አቶ አብርሀም አራጌ በብስጭት እንደነገሩት በማረሚያ ቤቱ የተቀነባበረና ...

Read More »

በጋምቤላ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደሉ

የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት ጥቂት ቀናት መረጋጋት የሰፈነበት ይመስል የነበረው የጋምቤላ ክልል ከትናንት ሁሙስ የካቲት ስምንት ቀን ከሰአት ጀምሮ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ ምንጮች ገልጠዋል። ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላትና አንድ ሲቪል ሰራተኛ በላንድ ክሩዘር መኪና ከዋና ከተማዋ ጋምቤላ ተነስተው 70 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ሚገኘው የ አበቦ ወረዳ በማምራት ላይ ሳሉ ሁለት የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ ...

Read More »

አወልያ መስጊድ ታህሪር አደባባይ ሆኖ መዋሉ ተዘገበ

የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው በዛሬው እለት በአወልያ መስጊድና በዙሪያው ባሉ ቦታዎች ከ100 ሺ ያላነሰ ህዝብ ተገኝቷል ከሙስሊሙ የተወከሉ ሰዎች ባለፈው ሰኞ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት ሪፖርት ለመስማማት ህዝቡ አሰፍስፎ ይጠብቅ ነበር፡፡ ተወካዮቹ የህዝቡን ስሜት በመረዳት የመንግስት ባለስልጣናት ጥያቄያቸውን እንደተቀበሉዋቸው እና የመጨረሻ መልስ ለመስጠት ለየካቲት 26 ቀነ ቀጠሮ እንደሰጧቸው ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች ተወካዮች በሰጡት መልስ ...

Read More »

የአቤ ቶኪቻው ወንድም የሆነው ወንደሰን ጌታነህ አንድ ሆቴል ውስጥ ሞቶ ተገኘ

የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጸሀፊና ሀያሲ አቤ ቶኪቻው የሶስት ጊዜ ታናሽ ወንድም የሆነው ወንደሰን ጌታነህ ሰሜን መዘጋጃ አካባቢ ከሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ሞቶ ተገኘ፡፡ ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡኩ ላይ ባስቀመጠው ዘገባ እንዲህ ብሎአል “ይህ ልጅ ገና ታዳጊ ነው፡፡ በአንድ ገራዥ ውስጥም በብየዳ ሙያ ተሰማረቶ ይሰራል፡፡ ገነት ሆቴል አካባቢም ብቻውን ተከራይቶ ይኖር ነበር፡፡ ስለድንገተኛ አሟሟቱ ፖሊስ መረጃ ለመስጠት ጊዜው ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በኦጋዴን 16 ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸዉ ተገለፀ

የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ምስራቅ ኦጋዴን በደገሃቡር ጉነ-ጋዶ አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሰት ወታደሮች በመንገድ ዳር ሰብሰብ ብለዉ ይነጋገሩ በነበሩ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ 16 ሰዎች መግደላቸዉን የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር መግለፁን ብሉምበርግ የዜና ወኪል ገልጿል። በወቅቱ ነዋሪዎቹ በመነጋገር ላይ የነበሩት ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በአካባቢዉ ነዋሪ በሆኑ አንድ አረጋዊና አንድ የፖሊስ ኮሚሽነር ላይ ስለተፈፀመዉ ግድያ እንደነበር የዜና ...

Read More »

የአዉሮፓ ህብረት ሁለቱ ስዊድናዉያን እንዲለቀቁ ጠንካራ ጫና በማድረግ ላይ ነው

የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስዊድን አባል የሆነችበት አንድ የአዉሮፓ ህብረት የልኡካን ቡድን በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዉ ባለፈዉ መስከረም እስራት የተፈረደባቸዉን ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞችን የአቶ መለስ መንግሰት እንዲለቅ ጠንካራ ዉይይት በማካሄድ ላይ እንዳለ ተገለፀ። “ባለፉት ጥቂት ቀናት ከኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ጋር ስንነጋገር ነበር፡ ሁለቱ ጋዜጠኞች ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ተስፋ አለን” በማለት ከጉዳዩ አሳሳቢነት የተነሳ ማንነታቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ የአዉሮፓ ...

Read More »

በትግራይ መለስን እንደ ቁምነገረኛ የሚቆጥረውና ንግግሩን የሚሰማ ሰው እየቀነሰ መምጣቱ ተነገረ

የካቲት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ መለስ ዜናዊን እንደ ቁምነገረኛ የሚቆጥረውና ንግግሩን የሚሰማ ሰው እየቀነሰ መምጣቱን አቶ አስራት አብረሀ ተናገሩ በተለያዩ ጽሁፋቸው የሚታወቁት የአረና ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ አስራት አብረሀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ  ፣ “ድሮ የመለስን ንግግር ለመስማት የትግራይ ሰው ይጓጓ ነበር፣ መለስ ንግግር ካደረገ በሁዋላም አድናቆቱን ይገልጥ ነበር፣ በቅርቡ መለስ በፓርላማ ያደረገውን ንግግር ብዙ የመቀሌ ...

Read More »

ባለፉት 20 ዓመታት ለደረሰው ጥፋት ዋነኛው ተጠያቂ መለስ ናቸው ተባለ

የካቲት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መለስ ሰሞኑን በፓርላማ ያቀረቡት ሪፖርት፤ መንግስታቸው መዳከሙን የሚያመለክት ነው ያሉት ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ባለፉት 20 ዓመታት ለደረሰው ጥፋት ዋነኛው ተጠያቂም ራሳቸው ናቸው ሲሉ ተናገሩ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ላይ ጠንካራ ትችት የሰነዘሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ የመድረኩ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣የ አንድነቱ አቶ አስራት ጣሴ እና  የ የኢዴፓው አቶ ሙሼ ሰሙ ናቸው።  አቶ መለስ ዜናዊ ሰሞኑን  የበጀት ...

Read More »

የአረብ ሳት ስርጭቶች የሚታወኩት ከኢትዮጵያ በሚለቀቅ ሞገድ ነው ተባለ

የካቲት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሊባኖስ የኮምንኬሽን ሚኒስትር የሆኑት ኒኮላስ ሽናዊ  የአርብሳት ከፍተኛ ባለስልጣኖችን ጠቅሰው ለዘ ደይሊ ስታር ለተባለው የሊባኖስ ጋዜጣ እንደተናገሩት በአረብሳት የሚተላለፉት ስርጭቶች እየታወኩ ያሉት የኢትዮጵያ መንግስት ስርጭቱን ለማፈን በሚያደርገው ሙከራ መሆኑን የአረብሳት ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ መንግስት የጻፉትን ደብዳቤ አይተው አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት አረብሳትን ለማፈን እንዳስገደደው ሚኒሰትሩ ገልጠዋል። የሊቢያ እና የግብጽ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ...

Read More »