አቶ አንዱዓለም አራጌ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጸመበት

 የካቲት 9 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ስም በእስር ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው  አቶ አንዱአለም አራጌ ቃሊቲ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በተቀመጠበት የካቲት 7 ቀን 2004ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ተደብድቧል፡፡

ከድብደባ በሁዋላ ፊቱ ላይ ጠባሳ የሚታይ ሲሆን ጭንቅላቱ አካባቢም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ አቶ አንዱአለም ለወንድሙ አቶ አብርሀም አራጌ በብስጭት እንደነገሩት በማረሚያ ቤቱ የተቀነባበረና የታቀደ ጥቃት እየተፈፀመበት እንደሆነ ጠቁሞ ለማስረጃ የሰበሰበው ወረቀትም ሆን ተብሎ ክፍሉ ውስጥ አብሮ እንዲታሰር በተደረገ ግለሰብ ተወስዷል፡፡

አቶ አንዱአለም ‹‹በድርጊቱ ብበሳጭም የግለሰቡ ተልኮ ስለገባኝ ዝም ከማለት ውጭ ምንም አላልኩም፡፡›› ያለ ሲሆን  ‹‹በተቀመጠበት ሳያስበው በቦክስና በእርግጫ በግለሰቡ መደብደቡ፣  ህይወቱን ያተረፉትም የኦህኮው ዋና ጸሀፊ አቶ በቀለ ገርባ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ለማረሚያ ቤቱ አቤት ብልም መፍትሄ ሊሰጠኝ የሚልችል ሰው አላገኙም የሚለው አንዱአለም፣ ፡ በዚህ አይነት ለህይወቴም እንደሚያሰጋኝ  እና በዚች ሀገር ላይ አየተፈፀመ ያለውን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ›› ብሎአል።

ዶ/ር ነጋሶ አቶ አንዱአለም መደብደቡን ማረጋገጣቸውን፣  ለኢሳት ተናግረዋል:: የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ  በነገው እለት ተሰብስቦ መግለጫ እንደሚያወጣ ዶ/ሩ ገልጠዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide