.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደል ቅዱስ ሲኖዶስ በማውገዙ ሙስሊሞች ምስጋናቸውን ገለጹ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በስደት የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደል በማውገዙ አድናቆታቸውን እና ምስጋናቸውን ገለጹ። በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ 33 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህገ-መንግስቱ በፈቀደላቸው መሰረት እምነታቸውን በነፃነት እንዳይከተሉ መንግስት ጣልቃ በመግባት እየፈጠረባቸው  ካለው ጫና  በ ...

Read More »

ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የመዘጊያ ዕለታቸው አንድ ወር ከ 15 ቀደም ብለው እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላለፈ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መምህራን ለ ኢሳት እንደገለጹት፤በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ መንፈቅ ትምህርት ክፍለ ጊዜን ከያዙት መርሃ- ግብር ቀደም ብለው እንዲያጠናቅቁና ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ ኢህአዴግ መመሪያ አውርዷል። የኢህአዴግን ድንገተኛ ውሳኔ በመቃወም ከወረዳ እና ከዞን ትምህርት ቢሮዎች ጋር ለመነጋገር የሞከሩ ትምህርት ቤቶች ተቀባይነት አላገኙም ያሉን አንድ ...

Read More »

አይኤም ኤፍ የኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ግሽበቱን እንዲቀነስ ጫና እንደሚያደርግ ተዘገበ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ እንደጠቆመው፤ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄደው የአይኤም ኤፍ የልኡካን ቡድን፣ መንግስት አሁን የሚታየውን ኸፍተኛ የገንዘብ ግሽበት ለመቆጣጠር ይችል ዘንድ ግፊት ያደርጋል። የገንዘብ ተቋሙ እንዳለው ባንኮች የተቀማጭ ወለድን እንዲያሳድጉ ማድረግ አንዱ አማራጭ፣ በመሆኑ ይህንን ለማስፈጸም  ልኡካኑ ከመንግስት ጋር ይነጋገራሉ። ኢትዮጵያ ላለፉት አመታት ያገኘችው እድገት በገንዘብ ግሽበት የተነሳ ወደ ሁዋላ የመመለስ ...

Read More »

አልሸባብ “አፍጎየ” የምትባለውን ስትራቴጂክ ከተማ ለቆ ወጣ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አልሸባብ ፤ሰሞኑን ከሽግግር መንግስቱና ከአፍሪካ ህብረት በደረሰበት ጥቃት ከሞቃዲሹ በቅርብ ርቀት የምትገኘዋን አፍጎየ ከተማን ለቆ ለመውጣት መገደዱን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁቡ ጊዜ በከተማ ይኖሩ የነበሩ ሶማሊያውያን አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ የአልሸባብ ሰራዊት ከተማውን ለቆ የወጣው ያለምንም ጦርነት ነው፣ ይሁን እንጅ የአፍሪካ ህብረት ጦር ወደ መሀል ከተማዋ ደፍሮ ለመዝለቅ አልቻለም። የወታደራዊ ተንታኞች ...

Read More »

የአሜሪካ ደምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ፒተር ሀይንላይን ታሰረ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ፒተር ሀይንላይን የታሰረው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአወልያ ያደረጉትን ተቃውሞ ለመዘገብ በሄደበት ጊዜ ነው ። ፒተር ከአዲስ አበባ በሚያስተላልፋቸው ነጻ ዘገባዎቹ በመላው የአሜሪካ ድምጽ አድማጮች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት አለው። በያዝነው ሳምንት መግቢያ ላይ ጋዜጠኛ ፒተር የሙስሊሞችን ተቃውሞ በመዳሰስ የሰራው ዘገባ ለእስራቱ አፋጣኝ ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ...

Read More »

በአዲስ አበባ አትክልት ተራ ፤ፖሊሶች ከነጋዴዎች እና ከነዋሪዎች ጋር ተጋጩ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት ፣ መጋቢት 16፣ 2004ዓም በአትክልት ተራ ፖሊሶች አንድ አትክልት ሻጭን መደብደባቸውን ተከትሎ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ በማሰማቸው  ፖሊሶች ወደ ሀይል እርምጃ አምርተዋል። በተከራይ እና አከራይ  መካከል የተነሳን ውዝግብ ሳቢያ  በጉሊት ሽያጭ የሚተዳደር ሰኢድ ኡመካ የተባለ ወጣት በፖሊሶች በመደብደቡ፤ የአፍሪካ አንድነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን በጩኸት አሰምተዋል። ጩኸቱ ወደተካረረ ፍጥጫ አምርቶ ግጭት ማስከተሉን ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መቀጠሉን ገለጠ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የ2012 አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በዝርዝር አቅርቧል። በአረቡ አለም የታየውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የመለስ መንግስት አምና በመጋቢት እና በሚያዚያ ወራት 250 የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ እና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላት መታሰራቸውን፣ በሰኔ ወር ደግሞ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙመ ዘሪሁን ...

Read More »

ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብ የዕርዳታ ድርጅቶ ች ጥሪ አቀረቡ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብና በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በልግ ዝናብ ተስተጓጉሎ በሰብሎች ላይ ጉዳት በማስከተሉ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብ የዕርዳታ ድርጅቶ ች ጥሪ አቀረቡ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች አስተባባሪ ማይክ ማግዶናግ በልግ አብቃይ የሆኑት አካባቢዎች በተለይም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጠቃቱን ለኢሪን ገልጸዋል። የሰሜን ምሥራቅ አማራ፣ የኦሮሚያ እና ...

Read More »

ታዋቂው የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነት ያገለግሉ ነበሩ:: በደረሰባቸው ድንገተኛ ህመም ለጥቂት ጊዜ  በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ ባለትዳርና  የ4 ልጆ ች አባት እንዲሁም የሁለት ልጆች አያት ነበሩ:: በጋዜጠኛ ንጉሤ ጋማ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ ይዘን እንቀርባለን። ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ለአቶ መለስ ዜናዊ የተያዘው መርሀ ግብር እንዲሰረዝ ተደረገ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበር አባላት ባደረጉት ተጽእኖ ለአቶ መለስ ዜናዊ የተያዘው መርሀ ግብር እንዲሰረዝ ተደረገ አቶ መለስ ፣ ታቦ ምቤኪ አፍሪካን ሌደርሽፕ ኢንስቲቲዩት የተባለ ተቋም  ፣ በሚያዘጋጀው  ጉባኤ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች እና ምሁራን በሚገኙበት ዛሬ ሜይ 24፣ 2012 ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጾ ነበር። ዝግጅቱን ...

Read More »