ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሃሮማያ /ዓለማያ/ ዩኒቨርስቲ በቴክኖሎጂ ፋኩሊቲ ውስጥ የሚገኘው “የወተር ኢንጂነሪንግ” ዲፓርትመንት የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ባነሱት አካዳሚክ ጥያቄ ሳቢያ ፌዴራል ፖሊስ ወደ ዶርማቸው ገብቶ ስለደበደባቸው በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል፡፡ መብታቸውን የጠየቁ ተማሪዎች ለሁለት ቀናት የመመገቢያ ካርዳቸውን ተነጥቀው ምግብ እንዳያገኙ መደረጋቸውንና ዩኒቨርስቲው ሙሉ በሙሉ በፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ ሥር እንደሚገኝ ተማሪዎች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ” በሀገሪቱ ያሉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
መንግስት ዋልድባ ገዳምን ለማፈራረስ የጀመረውን ዘመቻ በመቃወም ሰልፍ ተደረገ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሜልበርን መድሃኔዓለም ደብር አስተባባሪነት በተጠራው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ከተሰባሰበ በኋላ ወደ ፓርላማው ህንጻ አምርቷል። በፓርላማው ጽ/ቤት በመገኘትም መንግስት አለም አቀፍ እውቅና ያለውን የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም ኢትዮጵያዊ ወገን የሚያደርገውን ጥረት የአውስትራሊያ መንግስት እንዲያግዝ የሚጠይቁ ልዩ ልዩ መፍክሮችን ሲያሰማ አርፍዷል። በሰልፉ ...
Read More »የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያውን ከደቡብ አፍሪካው “ባፋና ባፋና” ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዬ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያውን ከደቡብ አፍሪካው “ባፋና ባፋና” ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዬ:: የሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከ 1000 ብር እስከ 2000 ብር ተሸለሙ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ በመጫዎት ያገኘው ውጤት ብዙሀኑን የስፖርት ቤተሰብ አስደስቷል። በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ክፍለ-ጊዜ ‘ባፋና ባፋናዎች’ አልፎ አልፎ ያደረጓቸው ...
Read More »የሰሜን ጎንደር የመኢኣድ ምክር ቤት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ታሰሩ
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታድሎ ተፈራ የታሰሩት ትናንት ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ ፖሊሶች ወደ ቤታቸው በመሄድ እና ከፍተኛ ፍተሻ በማካሄድ አፍነው ወስደውታል። የበለሳ ተወላጅ የሆነው አቶ ታደሎ ተፈራ ጎንደር ከተማ ውስጥ ከአክስቱ ጋር ይኖር ነበር። አክስቱ ወ/ሮ ዘርጊባቸው ሀይሉ ለኢሳት እንደገለጡት ግለሰቡን በርካታ ፖሊሶች ስራ ይሰራበት ከነበረው ደልጊ ከተማ ...
Read More »በአፋር ክልል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፋር ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት በክልሉ ያለው ችግር መባባስ ህዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን እንዳይገፋ አድርጎታል። በዞን አንድ እና ዞን 3 በተባሉት አካባቢዎች መንግስት ነዋሪዎችን በጉልበት እያፈናቀለ መቀጠሉን በዞን ሁለት ደግሞ የማእድን ዘረፋው የችግሩ ምንጭ መሆኑን የአፋር ህዝብ ጋድሌ ሰራዊት ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት ገልጠዋል:: ኮሎኔል ሙሀመድ እንዳሉት ለስኳር ፋብሪካ በሚል አካባቢው ...
Read More »የመሬት ቅርምት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ጋዜጣ ዘገበ
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስዊዘርላንድ የሚታተም ታገስ አንዛይገር የተባለ ጋዜጣ ፣ በመሬት እና ባካባቢው ከሚኖሩ ዜጎች ፍላጎት እና ስምምነት ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ኢንቨስትመንት በባለሃብቶች እና ባካባቢው በሚኖሩ ዜጎች መካከል በሚፈጠር አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያመራ እና በሃገሪቷ ውስጥም አለመረጋጋት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቋል። ጋዜጣው የአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የእርሻ መሬት 10% ወይም 3.6 ሚሊዮን ...
Read More »ኢትዮጵያዊቷ በኩዌት ጎዳናዎች ራቁቷን ደም በደም ሆና ታየች
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደሟን እያዘራች ራቁቷን በኩዌት ጎዳናዎች ላይ ስትሮጥ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት በፖሊስ ተይዛ -በሳይካትሪስት ምርመራና ህክምና እንዲደረግላት ወደ ሆስፒታል መግባቷን አረብ ታይምስ ዘገበ። አረብ ታይምስ ፦ “አል ራይ” የተባለውን የአገሪቱን ሳምንታዊ ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በጎዳና ላይ ሲጓዙ የነበሩ እግረኞች አፍሪካዊ መልክ ያላት ሴት ራቁቷን ሆና ደም እየፈሰሳት በጎዳና ላይ ስትሮጥ ማየታቸውን ለኩዌት የአገር ...
Read More »ሆስኒ ሙባረክ በዕድሜ ልክ እሥራት እንዲቀጡ ተወሰነ
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ 84 ዓመቱ ሙባረክ ለፍርድ ቤቱ በከፍተኛ የጤና ችግር ላይ እንደሆኑ በማመልከት አስተያዬት ይደረግላቸው ዘንድ ጠይቀው እንደነበር የግብጽ መንግስታዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ሆስኒ ሙባርክን ለዕድሜ ልክ እሥራት ያበቃቸው፤ ባለፈው ዓመት የተካሄደውንና እርሳቸውን ከመንበራቸው የፈነቀላቸውን የግብጽ አብዮት ለማክሸፍ በማሰብ ባስወሰዱት የሀይል እርምጃ በርካታ ተቃዋሚዎች በመገደላቸው ነው። ሙባረክ፤በዓረቡ ዓለም አብዮት ከተወገዱት መካከል ፦ ለፍርድ የቀረቡ ...
Read More »በከምሴ የሚገኙ ሙስሊሞች ዛሬም ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ተፋጠው ሶላትን አሳለፉ
ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሙስሊሞቹ በከተማው የገቢዎች ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በደዌይ መስመር አካባቢ በሚገኘው መስጊድ እንደተሰባሰቡ የፌደራል ፖሊስ አባላትም አብረው በመግባት ሙስሊሞቹ ሶላታቸውን እንደጨረሱ እንዲበተኑ አድርገዋል። ፖሊሶች ከሶላት በፊት ሌላ ነገር ማድረግ አትችሉም ተብለው እንዲበተኑ ቢደረገም፣ ፍጥጫው እንዳለ መሆኑን ምንጮች ገልጠዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ሙስሊሞችን ለማግባባት ጥረት ሲያደርጉ፣ የተወሰኑ ወጣቶችንም ለማስፈራራት ሙከራ ...
Read More »በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሁለት የተቃዋሚ ፓርተዎች አባላትን አፍነው ወሰዱ
ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደባርቅ ወኪል ባስተላለፈው መረጃ መሰረት በትናንትናው እለት ቀድሞ የመኢአድ አባል የነበረውና በምርጫ 97 ቅንጅትን፣ በምርጫ 2002 ደግሞ አንድነት ፓርቲን በመወከል ሲንቀሳቀስ የነበረውን አቶ ስለሺ ጥጋቤን አፍነው ወስደውታል። ግለሰቡ ከተያዘ በሁዋላ ቤቱ ለ2 ሰአታት ሲበረበር እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል። የአቶ ስለሺ ጥጋቤ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጡት፣ ፖሊሶች እና የደህንነት ሰዎች ግለሰቡን አፍነው ወደ አዲስ ...
Read More »