በአፋር ክልል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአፋር ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት በክልሉ ያለው ችግር መባባስ ህዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን እንዳይገፋ አድርጎታል።  በዞን አንድ እና ዞን 3 በተባሉት አካባቢዎች መንግስት ነዋሪዎችን በጉልበት እያፈናቀለ መቀጠሉን  በዞን ሁለት ደግሞ የማእድን ዘረፋው የችግሩ ምንጭ መሆኑን  የአፋር ህዝብ ጋድሌ ሰራዊት ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት ገልጠዋል::

ኮሎኔል ሙሀመድ እንዳሉት ለስኳር ፋብሪካ በሚል አካባቢው እንዲራቆት እየተደረገ በመሆኑ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማ ነው::

የአፋር ክልል መንግስት ለህዝቡ ምንም ሊፈይድ እንዳልቻለ ኮሎኔሉ ይናገራሉ::

በዛሬው እለት ተፈጠረ ስለተባለው ግጭት ለማረጋጋጥ ወደ አካባቢው በተደጋጋሚ ብንደውልም የስልክ መስመር ለማግኘት አልተቻለም። መንግስትም በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide