Author Archives: Central

ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡ ተማሪዎች ህዝብ እንዲደርስላቸው ጠየቁ

ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ተቃውሞ ተከትሎ  በሀረር መካነሰላም እና በድሬዳዋ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ችግራቸው መፍትሄ ያገኝ ዘንድ ተማጽነዋል። ከ200 በላይ ተማሪዎች በድሬዳዋ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ፣ ከ200 በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመካነሰላም ቤተክርስቲያን ተጠልለለው የሚገኙ ሲሆን፣ ምንም መረጃ የሌላቸው ተማሪዎች ደግሞ በባዶ ሜዳ እየተንከራተቱ በመለመን ላይ ...

Read More »

ሂውማን ራይትስ ወች በተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ አወገዘ

ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወሰዱት ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ በአስቸኳይ ሊያቆሙ ይገባል ብሎአል። የመንግስት ባለስልጣናት በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን መፍታት እንደሚገባቸው ፣ ድርጊቱን የፈጸሙት የጸጥታ ሃይሎችና ባለስልጣናት አስፈላጊው ምርምራ እንዲካሄድባቸው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ጠይቋል። የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሌስሊ ሌፍኮ  የአዲስ አበባን መስፋፋት ...

Read More »

የቻይናና አፍሪካ ንግድ ወደ 400 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ሊ ኪቺያንግ ተናገሩ

ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቻይናው ጠ/ሚንስትርሊ ጂያንግ  በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ባደረጉት ንግግር አገራቸው ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ በማሳደግ ከ6 አመታት በሁዋላ የንግድ ግንኙነቱ ወደ 400 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል ብለዋል። ቻይና ባለፉት አመታት የአፍሪካ ቀዳሚዋ የንግድ ሸሪክ መሆናን ጠ /ሚኒስትሩ ገልጸዋል። አገሪቱ ለተለያዩ አፍሪካ አገራት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር መስጠቷንም ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ጠ/ሚኒስትሩ የአፍሪካ ...

Read More »

የግብጹ እጩ ፕሬዚዳንት ስልጣን ከያዙ የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ፓርቲን እንደሚያጠፉ ተናገሩ

ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አብዱል አል ፋታህ ሲሲ ከግብጽ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ስልጣን ከያዙ ሙስሊም ብራዘር ሁድስ ፓርቲን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፉት ተናግረዋል። እጩ ፕሬዚዳንቱ ሁለት ጊዜ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር ገልጸዋል። መከላከያ ሰራዊቱ የግብጽን አብዮት ቀልብሰዋል ተብሎ የሚወራው ትክክል አለመሆኑም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ለመሆን የሚወዳደሩት ሲሲ፣ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲን ከስልጣን ሲያስወግዱ ስልጣን እይዛለሁ ብለው እንዳላሰቡ ...

Read More »

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የተነሳው ግጭት አሁንም አስከፊ በሆነ መልኩ እንደቀጠለ ከአካካቢው የሚደርሱን መረጃዎች አመልክተዋል። የዩኒቨርስቲው ምክትል ዲን ዶ/ር ጨመዳ ችግሩ ከዩኒቨርስቲው አቅም በላይ መሆኑን ለተማሪዎች ተናግረዋል። ባለፈው አርብ በተማሪዎች መካከል አካባቢን መሰረት አድርጎ በተነሳ ግጭት አንድ ተማሪ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደል አንዲት ሴት ተማሪም እንዲሁ ከፍተኛ የሚባል አካላዊ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሚያዚያ 26 ባካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በስርአቱ ላይ ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል። በሰልፉ ላይ በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚሄደው የውሃ እጥረት፣ የመብራት እና የስልክ ኔት ወርክ እጥረት እንዲቀረፍ ጥሪ ቀርቧል። በቅርቡ በኦሮምያ በንጹሃን ተማሪዎች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች  ያደረሱትን ግድያ፣ ሀሳባቸውን በሚገልጹ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች ላይ የደረሰውን ...

Read More »

ሂውማን ራይትስ ወች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠየቀ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ገምጋሚ ቡድን የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ በሚገመግምበት ወቅት መንግስት በጋዜጠኖችና በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚያደርገውን አፈና እንዲያቆም እንዲጠይቅ አሳስቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምገማውን እያካሄደ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞና ጸሃፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ሃላፊ ሌስሌ ሌፍኮው ገልጸው፣ ግምገማው ውጤታ ይሆን ዘንድ የድርጀቱ ...

Read More »

የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ባለፈው ቅዳሜ በመንግሥታዊ ድርጅቶች አስተባባሪነት ሲከበር በኢትዮጽያ ስላለው የፕሬስ አፈናና ስለታሰሩ ጋዜጠኞች ጉዳይ ምንም ሳይወያይ ተበተነ፡፡

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየዓመቱ ሜይ 3 ቀን የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጽያ ለአምስተኛ ጊዜ ባለፈው ቅዳሜ በግዮን ሆቴል የተከበረ ሲሆን የስብሰባው አዘጋጅ ሆነው የተገኙት የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት እና የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡ ቀኑ የፕሬስ ነጻነት የሚታሰብበትና ጋዜጠኞች በስራዎቻቸው ዙሪያ ስለገጠማቸው ችግሮች የሚወያዩበት ቢሆንም በመንግስታዊ ድርጅቶቹ ተጠልፎ ስለፕሬስ ካውንስል ምስረታ ጉዳይ ሪፖርት ሲቀርብበት መዋሉ አሳዛኝ መሆኑን ስብሰባውን ...

Read More »

በላዛሪስትታስረውየሚገኙየሰማያዊፓርቲአባላትመደብደባቸው ታወቀ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊፓርቲሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ጠርቶት ለነበረው ሰላማዊሰልፍቅስቀሳላይእያሉፖሊስይዟቸውላዛሪስፖሊስጣቢያየሚገኙትየሰማያዊፓርቲአባላትመደብደባቸው ታውቋል። በተለይ ‹‹አንተንየሚጠብቅፖሊስየለንምተብሎ›› ፈተናእንዳይፈተንየተደረገውዮናስከድርከፍተኛድብደባየደረሰበትሲሆንበአሁኑወቅትዮናስ  መንቀሳቀስእንደማይችልአብረውትታስረውየሚገኙትየሰማያዊፓርቲአባላትመግለጻቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በእስርላይየሚገኙሌሎችየሰማያዊፓርቲአባላትምድብደባእንደረሰባቸውየታወቀሲሆንደህንነቶችናየእስርቤቱኃላፊዎችተጨማሪድብደባእንደሚደርስባቸውእያስፈራሩዋቸውመሆኑንለነገረኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ የሰማያዊፓርቲየህዝብግንኙነትኃላፊአቶብርሃኑተክለያሬድታሳሪዎቹንለመጠየቅናሁኔታውንለማጣራትወደእስርቤትበሄደበትወቅትምእስርቤቱውስጥየሚሰራአንድፖሊስ ‹‹እኔነኝያስደበደብኩት፡፡ምንምአታመጡም፡፡ከፈለጋችሁበደንብእዩኝናክሰሱኝ፡፡አሁንከእኔጋርመነጋገርአትችሉምከግቢውጡ›› ብሎእየገፈተረእንዳስወጣቸውገልጾአል፡፡ በላዛሪስትታስረውየሚገኙትየሰማያዊፓርቲአባላትላለፉትሁለትቀናትበረሃብአድማላይመሆናቸውናበዚህምምክንያትመዳከማቸውየታወቀሲሆንፖሊስናደህንነትበዚህሁኔታላይሆነውእንኳከፍተኛድብደባእያደረሱባቸውመሆኑእንዳሳዘነውአቶብርሃኑጨምሮገልጸአል፡፡ወጣት እስረኞቹ “በመጀመሪያ መታሰራችንህገወጥሆኖእያለ 5 ሺ 500 ብርከፍላችሁውጡመባላችን አግባብ አይደለም በማለት በእስር ለመቆየት መወሰናቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Read More »

በኖርዌይኦዳከተማ የሚኖሩኢትዮጵያውያን “የምእራባውያንእርዳታበኢትዮጵያየንፁሐንዜጎችማፈኛተደርጎመዋሉንለማሳየት“ ያዘጋጁት ውይይትበተሳካሁኔታተጠናቀቀ።

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኖርዌይየፓርላማአባላትን፣ፖለቲከኞችንእንዲሁምየተለያዩየማህበረሰብክፍሎችን ባሳተፈው በዚህ ዝግጅት ፣   ገዥውስርዓትበሐገርናበሕዝብላይያደረሰውንአፈናናግድያ ፤  የዜጎችመፈናቀልንናየሰብአዊመብትጥሰቶችን  የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ  ፊልሞች ቀርበዋል። የምዕራባውያንለጋሽአገሮችድጎማ አገዛዙ ለሚያደርገው አፈና አስተዋጽኦ ማድረጉን በአቶከሊፋባርቱራእንዲሁምበወጣትሎሚታባህሩ የቀረበው ዝግጅት ያሳያል። ከተጋባዥእንግዶችመካከል ሮድ ፓርቲን በመወከል ሚ/ርቴሪያኮልቦትን፣ ሆይሬ ፓርቲን በመወከል ኒልሰን ፒተርየተገኙ ሲሆንጉዳዮንከአጋሮቻቸውጋርበመሆንለፓርላማለውይይትለማቅረብየበኩላቸውንእንደሚጥሩ ገልፀዋል። ከዚህቀደም ተመሳሳይ ዝግጅትበሰሜንኖርዌይሎዲንገንከተማተካሂዷል። በሌላ ዜና ደግሞበዲሞክራሲያዊለውጥበኢትዮጵያስታቫንገርቅርንጫፍ  የፖለቲካናየሕሊናእስረኞችንለማሰብቅዳሜሜይ 3 ቀንየተካሔደውዝግጅትበተሳካሁኔታመጠናቀቁን አበበ ደመቀ ከኖርዌይ የላከው ዘገባ ያመለክታል።

Read More »