ሂውማን ራይትስ ወች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠየቀ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ገምጋሚ ቡድን የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ በሚገመግምበት ወቅት መንግስት በጋዜጠኖችና በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚያደርገውን አፈና እንዲያቆም እንዲጠይቅ አሳስቧል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምገማውን እያካሄደ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞና ጸሃፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ሃላፊ ሌስሌ ሌፍኮው ገልጸው፣ ግምገማው ውጤታ ይሆን ዘንድ የድርጀቱ ገምጋሚ ቡድን በኢትዮጵያ የሚታየውን አፈና በግልጽ ሊያወግዝ ይገባል ብለዋል።