በቁጫ ወረዳ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች እየተባረሩ ነው

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል። እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ ታስረዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ...

Read More »

የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ታስሮ ወደ ደቡብ ክልል ተወሰደ

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው እንደዘገበው  መላኩ ደምሴ  ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰዷል፡፡ ጋዜጠኛው ለጥያቄ የተወሰደው ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ...

Read More »

ቻልሰ ቴለር ወደ እንግሊዝ ተዛውረው ይታሰራሉ

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ሊቢያው አምባገነን መሪ ቻርለስ ቴለር በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው ዘ ሄግ በሚገኘው አለማፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የ50 አመታት እስር ከተፈረደባቸው በሁዋላ፣ የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ እንደሚፈጽሙ ታውቋል። ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን ጦርነት ወቅት በተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ደግፈዋል በሚል ነበር ጥፋተኛ የተባሉት። የ65 አመቱ ቴለር ቀሪ ህይወታቸውን በእንግሊዝ እስር ቤት እንደሚያጠናቅቁ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

Read More »

የአፍሪካ መሪዎች በአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዙሪያ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ፊታውራሪነት የአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን አሰራር ለመቃወም አፍሪካ መንግስታት በአዲስ አበባ ለአስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸው ታውቋል። ጠ/ሚ ሀይለማርያም ሰሞኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቀርበው የወንጀል ፍርድ ቤቱን ተችተው ነበር። ይህን ተከትሎ በሚመስል ሁኔታ የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር መሪዎችን ከጥቅምት 1 እስከ 2 በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል። የኬንያው ፕሬዚዳንት ...

Read More »

4 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሥራ ዝውውር ሊያደርጉ ነው

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት እንደሚያደርግ ሪፖርተር ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር  በሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር በሆኑት  ዶ/ር ካሱ ኢላላና በፈረንሳይ ...

Read More »

መንግስት ከ9 አመታት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ11 በመቶ በታች እድገት ማስመዝገቡን ገለጸ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 በጀት ዓመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 ነጥብ 7 በመቶ ማደጉን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ በበርካታ ፈተናዎች ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት እድገት መመዝገቡን አወድሰዋል። የግብርና ዘርፍ በ2005 በጀት ዓመት የ7 ነጥብ 1 በመቶ የአገልግሎት ዘርፉ  ደግሞ የ4 ነጥብ 9 በመቶ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል። ዶክተር አብርሃም ኢኮኖሚያዊ እድገቱ የሃገሪቱን ...

Read More »

በፕሬዚዳንቱ ንግግር ዙሪያ አቶ ሀይለማርያም መልስ ይሰጣሉ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ አዲስ ፕሬዚደንት በመምረጥ የዚህን ዓመት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ፓርላማ በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ በንባብ የቀረበውን የመንግስት የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫና ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀጣይ ሳምንት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት በሚቀርቡ የድጋፍና የተቃውሞ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወያያል፡፡ ፓርላማው በትላንት ውሎው መስከረም 27 ቀን 2006 ዓም አዲሱ ፕሬዚደንት ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግርን አስመልክቶ ገዥው ፓርቲ ...

Read More »

መንግስት ለኢትዮጵያ የሚዲያ እድገት መዳከም ዋና ተጠያቂ ነው ተባለ

  መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውይይታቸውን ያደረጉ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ጋዜጠኞች ሚዲያዎቹ በመንግስት የአፈና እና የእጅ አዙር ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው ብለዋል።   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የባለሙያዎች የጥናት እና ምርምር ግኝት ስራዎች ላይ ተመርኩዞ ከባለሙያዎች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በቀረቡት ጽሁፎች እንደተገለፀው የኢትዩጵያ ሚዲያዎች አዲስ የሚቋቋሙትም ሆነ ነባር የሕትመት ሚዲያዎች የፋይናንስ ብቃታቸው ዝቅተኛ ...

Read More »

ዋልያዎች፦” የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድንን ካሸነፍን እንዲሚሰጠን ቃል የተገባልን ቦነስ ገንዘብ ያንሰናል” በማለት ቅር መሰኘታቸው ተገለጸ።

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱፐር ኤግልስን ካሸነፉ መንግስት  እንደሚሰጣቸው ቃል የገባላቸው ቦነስ በቂ እንዳልሆነና ስሜታቸውን የሚያነሣሳ እንዳልሆነ ነው  ተጫዋቾቹ የተናገሩት። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀናት በፊት የ22ቱን ተጫዋቾች ስም ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ በቡድኑ ውስጥ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆነው ጌታነህ ከበደ በጉዳት ምክንያት በቡድኑ ውስጥ አልተካተተም። በቀራቸው የደርሶ መልስ ጨዋታ ናይጀሪያን አሸንፈው ለዓለም ዋንጫ ካለፉ የሚሰጣቸው ቦነስ ምን ያህል እንደሆነ ...

Read More »

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ  የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው። ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ መድረክ እንድናወጣላቸው ተማጽነዋል። መንግስት ከአሁን ...

Read More »