ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት)መስራች አባል የሆኑትን በአቶ መለስ ጊዜ ከከፍተኛ የድርጅቱ ቦታዎች ተገፍተው የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በመጪው መስከረም 20 በጀርመን-ቡንደስታግ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ተመለከተ። በነባሮቹ የድርጅቱ አባላት ዘንድ <አቦይ>ተብለው የሚጠሩት አዛውንቱ አቶ ስብሀት ነጋ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በድርጅቱ ውስጥ ወደ ቀድሞ ተሰሚነታቸውና አድራጊ ፈጣሪነታቸው እየተመለሱ እንደሆነ ...
Read More »የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ጉባኤ በቨርጂኒያ ተካሄደ
ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች ጉባኤ በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ተካሄደ። ትናንት እሁድ፤ መስከረም 4 ቀን በተካሄደው ጉባኤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከተለያዩ የአሜሪካን ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን፤ ለኮንግረስና ለሲቲ ካውንስል የሚወዳደሩ እጩዎች ቀርበው ንግግር አድርገዋል። ኮንግረስማን ሞራን ግሪፊዝ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር እንደሚረዱ ገልጸው፤ ከኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል። የአሌክሳንድሪያው ከንቲባ ዊሊያም ዲ ኢዩልም ...
Read More »ጅጅጋ፤ ሀረርና ድሬዳዋ ካለፉት ስድስተ ቀናት ወዲህ ጨለማ ውስጥ ናቸው
ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ምስራቅ ከተማዎች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው የታወቀ ሲሆን፤ የደብረዘይት ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት 7 ቀናት የውሀ አገልግሎት እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ከድሬዳዋ ጅጅጋና ሀረር ከተሞች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሀረር፤ ድሬዳዋና ጅጅጋ ከተሞች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት አልነበራቸውም። የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አመት ለጅቡቲ 20 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ መሸጥ መጀመሩን መናገሩ የሚታወስ ...
Read More »በኢትዮጵያ ውስት የሸሪአ ሕግ መጫን ጨርሶ የማይታሰብ ነው ተባለ
ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሸሪያ ሕግ እንዲታወጅ የኢትትዮጲያ ሙስሊሞች አለመጠየቃቸውን፤ በኢትዮጲያ ያለው ነባራዊ ሁኔታም ይህንን ጨርሶ እንደማይፈቅድ፤ አንድ የእስልምና ሐይማኖት ምሁር ገለጹ። በሸሪያ ሕግ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን የሰሩትና የፈርስት ሒጅራ ፋውንዴሽን ኢማም የሆኑት ሼህ ካሊድ መሐመድ ኡመራ ለኢሳት እንደተናገሩት ሸሪያ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሙስሊሙ ላይ ብቻ እንደሆነም አመልክተዋል። እስልምና መቻቻልን እንደሚሰብክ አጥብቀው የተናገሩት ሼህ ካሊድ መሐመድ ኡመር፤ ...
Read More »ቤታቸው የፈረሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተለምዶ አሮጌው ቄራ በሚባለው አካባቢ ላለፉት 20 እና 30 አመታት የቀበሌ እና የወረዳ ህጋዊ እውቅና ኖሮአቸው በመጠለያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 51 አባዎራዎች እና እመዎራዎች ባለፈው ቅዳሜ ያለምንም ምትክ ቤታቸውን አፍርሰው የቤት ቁሳቁሳችንን ሁሉ ወረሱብን በማለት በአራዳ ክፍለከተማ አስተዳዳሪ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ፖሊስ ሰልፉን በትኖ ...
Read More »ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ
ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሥነምግባር ችግር ከተባረሩ በኋላ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትዕዛዝ ያለጨረታ የደቡብ ክልል መገኛኛ ብዙሃን የቴክኒክ ሥራን ተረክበው በአቋራጭ ከባለሃብት ጎራ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ፣ ዛሚ በተሰኘው ራዲዮ ጣቢያቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአጃቢ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ሲሟገቱ ውለዋል፡፡ ሰሞኑን የወጡ ጋዜጦች ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን ለአቶ ኃይለማርያም አላስረከቡም በሚል ያወጡትን ተከታታይ ዘገባዎች ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከ 31 ዓመት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋኝጫ ውድድር አለፈ
ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት የብሔራዊ ቡድኑን ውጤት የፖለቲካ መነገጃ ለማድረግ መሞከሩ ብዙዎችን ቅር አሰኝቷል። በቅጽል ስሙ<ዋሊያ>ተብሎ የሚጠራው የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ትናንት በ አዲስ አበባ ስታዲየም ባደረገው የመልስ ጨዋታ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ነው ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማለፉን ያረጋገጠው። ከወራት በፊት ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታ አንድ ላይ ሲመደቡ፤ በሁለቱም አገሮች ዘንድ የደስታ ስሜት ...
Read More »ህወሀት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ቦታ ሊወስድ መዘጋጀቱ ታወቀ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና የአቶ ደመቀ መኮንን ጠቅላይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መሾም፣ በኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ውስጥ በተለይም በኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ተቀባይነት ማጣቱ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የሀይለማርያም መንግስት ኦህዴድን የሚያስከፋ በተወሰነ መጠን የህወሀትን ተቃውሞ ሊያረግብ የሚችል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ታውቋል። በመንግስት የስልጣን ተዋረድ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀጥሎ የተሻለ ቦታ ተደርጎ የሚታየውን ...
Read More »የኢትዮጵያ የውጪ ዕዳ 200 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተመለከተ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢትዮጵያ የገንዘብና የ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው 134 ቢሊዮን ብር የነበረው የ አገሪቱ የውጪ ዕዳ እጅግ በሚያስደነግጥ መልኩ ባለፈው ሰኔ ወር ወደ 200 ቢሊዮን ብር አሻቅቧል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዶክመንንት ከዚህም በተጨማሪ የመንግስት የ አገር ውስጥ ብድርና ዕዳ 60 ቢሊዮን ብር መድረሱን ያመለክታል። ይህ ዕዳ ፤ኢትዮጵያ በቅርቡ ለባቡር ሀዲድ መስመር ግንባታ ...
Read More »ቻይና አፍሪካውያን ዲሞክራሲን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት እንደምታግዝ አስታወቀች
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ የሆኑት ሚስተር ሉ ሻየ ይህን የተናገሩት በአፍሪካ እና በቻይና ምሁራን መካከል በኢትዮጵያ በደብረዘይት ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ላይ ነው። ባለስልጣኑ እንዳሉት ቻይና አፍሪካዊያን ዲሞክራሲን ብቻ ሳይሆን፣ የህግ ተቋማትን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ታግዛለች። አገራቸው በመልካም አስተዳዳር ላይ ያላትን ልምድ ለአፍሪካ አገሮች ለማካፈል ዝግጁ መሆኑዋንም ገልጠዋል። ...
Read More »