ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል” የተሰኘ ዓለማቀፍ ድርጅት በታችኛው የኦሞ ሸለቆ በመንግስት ከመሬታቸው የተፈናቀሉ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ለረሀብ ተጋልጠዋል አለ። በታችኛው የኦሞ ሸለቆ በመንግስት አስገዳጅነት ከመሬታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች አርሰውም አድነውም ለመብላት ባለመቻላቸው በረሀብ ላይ መሆናቸው ተገለጠ:: በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ሞታቸውን እየተጠባበቁ ነው ተብሎል:: ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አለም ከረሀብ ...
Read More »አቶ ግርማ ሰይፉ ለኢትዮጵያ መንግስት የእንወያይ ጥሪ አቀረቡ
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብቸኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፤ መንግስት ከመድረክ ጋር እንዲወያይ ጥሪ አቀረቡ። በኢትዮጲያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ፤ መድረክ ከመንግስት ጋር በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ይችል ዘንድ ጥሪ አቀረቡ። የመድረክ ብቸኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፤ መንግስት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ለመወያየት ፈቃደኛነቱን እያሳየ፤ ከሰላማዊ ...
Read More »የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀቱ መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በሀዲድ አምራችነት የሚሳተፍበት የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም ከአውሮፓ ኀብረት የ114 ኪሎሜትር የባቡር ሐዲድ በአዲስ መልክ ለመገንባት ለኢትዮጽያ መንግስት የተሰጠው ገንዘብ በትትክክል ሥራ ላይ አለመዋሉን ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት የተገኘ መረጃ አመልክቷል፡፡ ገንዘቡ በዕርዳታ መልክ ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት መሰጠቱን ያስታወሱት ምንጮቹ ከ114 ኪሎሜትር ውስጥ ...
Read More »ከኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ጋር ተያይዞ በድሬዳዋ የዋጋ ግሸበት በአስደንጋጭ ፍጥነት እየጨመረ
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምሥራቁ የኢትዮጵያ ክፍል መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ከባድ ተሸካሚ መስመር መዘረፍ በኃላ መብራት ባጣችው በድሬዳዋ ከተማ የሸቀጦች ዋጋ በአስፈሪ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች አረጋገጡ፡፡ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከምሸቱ አንድ ሰዓት አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ያስታወሱት ነዋሪዎቹ ከዚያ በኃላ በከተማዋ የመጠጥ ውሃ መጥፋቱን ተናግረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የአንድ ...
Read More »በቋራ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ስራ እያቆሙ ነው
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በቋራ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የመስከረም ወር ደሞዝ በወቅቱ ስላልደረሰላቸው ትናንትና ዛሬ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ተቃውሞአቸውንም ለመንግስት ባለስልጣናት አቅርበዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ መምህር ለኢሳት እንደገለጡት ፣ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች መምህራን ከሀምሌ ወር ጀምሮ ደሞዝ ያልተከፈላቸው በመሆኑ፣ “ካልበላን አንሰራም” በሚል ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋትና ተማሪዎችን ለመበተን ተገደዋል። የመንግስት ባለስልጣናት መምህራን ስራ ...
Read More »አል-አሙዲ በጨረታ ላሸነፉባቸው ድርጅቶች ክፍያ አልፈጸሙም
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለአፍሪካ ዋንጫ ላለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 5 ሚሊዮን ብር ለመሸለም ቃል የገቡት ሼክ አል አሙዲ ፤ከሸሪኮቻቸው ጋር በመሆን በጨረታ ላሸነፉዋቸው ድርጅቶች የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ክፍያ ሊፈጽሙ አለመቻላቸው ተዘገበ። ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ አራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለመግዛት የጨረታ አሸናፊነታቸው የተገለጸላቸው የሼክ መሐመድ አል አሙዲና ሸሪኮቻቸው ኩባንያዎች የቅድሚያ ክፍያ ጊዜ ቢራዘምላቸውም፣ በተፈቀደላቸው ...
Read More »መንግስት በቀጣዩ ፓትሪያሪክ ምርጫ ዙሪያ ላይ እጁን እያስገባ ነው ተባለ
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“የቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዳይ ከእርቅ እና ከአንድነት በኋላ እንጂ በችኮላ መሆን እንደሌለበት አጽንዖት እየተሰጠው ባለው በአሁኑ ወቅት; የየራሳቸውን ወገን “ፓትርያርክ” አድርገው ለማስሾም ፍላጎት ያላቸው የተለያዩ ቡድኖች፣ በይፋ ብቅ ማለት መጀመራቸውን በዝርዝር የዘገበው ደጀ-ሰላም ነው። እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ቀጣዩን የፓትርያርክ ምርጫ አስመልክቶ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ በስፋት እጁን ያስገባው መንግስት ነው። የሙስሊሙ ህብረተሰብ ...
Read More »አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጡ
ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጩ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ አዲስ ነገር አለመጠበቃቸውን ሲናገሩ፣ እውቁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ደግሞ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር “ከእነስታይላቸው ” አቶ መለስን መስለዋል ብለዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፓርላማ አባላቱ ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች መልሶችን የሰጡት፣ የቀድሞው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ፎቶ ግራፍ ፊት ለፊታቸው ተሰቅሎ በሚታይበት ሁኔታ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ...
Read More »የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ኢቲቪን ፦”የቆሻሻ ፕሮፓጋንዳ ፋብሪካ” ሲል ገለጸው
ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ሰሎሞን መንግስት በውሸት ፕሮፓጋንዳ በመማረሩ ሥራውን በፈቃዱ መልቀቁን አስታወቀ። ጋዜጠኛ ሰሎሞን መንግስት ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዝኛው ፕሮግራም ክፍል ባልደረባ በመሆን የተለያዩ ዘገባዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በእንግሊዝኛው ፕሮግራም የተሻለ አቅም ካላቸው ጋዜጠኞች መካከል አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ጋዜጠኛ ሰሎሞን ፤በድርጅቱ የ ኢዲቶሪያል ነፃነት አለመኖሩና ጋዜጠኞች ዘወትር ፕሮፓጋንዳ እንዲሠሩ ...
Read More »በድሬዳዋ፣ ሀርርና ጅጅጋ የተፈጠረው የኤሌክትሪክ መቋረጥ በምሰሶዎች ላይ በተፈጠረ ስርቆት ነው ተባለ
ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት እንዳስታወቀው ወለንጨቲ አካባቢ በኤሌትሪክ ምሶሶ ላይ በተፈጸመው ዝርፊያ 5 ምሶሶዎች ወድቀዋል። በዚህም የተነሳ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በ ድሬዳዋ፣ ሀረርና ጅጅጋና በሌሎችም ትልልቅ ከተሞችና የገጠር መንደሮች ኤሌትሪክ ተቋርጦባቸዋል። በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ስራዎች እንዲቋረጡም ከማስገደዱ በተጨማሪ በኤሌትሪክ የሚሰሩ የውሀ ፓንፖች ስራቸውን በማቋረጣቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መቸገራቸውን መንግስት አምኗል። በወለንጨቲ የተፈፀመው የኤሌትሪክ ምሰሶ ስርቆት ከ35 ሚሊዮን ብር ...
Read More »