(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 22/2010) በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ያለመከሰሰ መብታቸው የተነሳባቸው 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። በቁጥጥር ስር የዋሉት 6ቱ ሰዎች በአብዲ ኢሌ አስተዳደር ውስጥ ቁልፍ የሚባሉ ቦታዎችን ይዘው የነበሩ መሆናቸውም ታውቋል። ምክር ቤቱ የቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌን ጨምሮ የክልሉን 7 ከፍተኛ አመራሮች ያለመከሰስ መብት ያነሳው ባለፈው እሁድ ነበር። በሶማሌ ክልል ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት ይቁም፣የዜጎች አላግባብ መጨቆን ሊያበቃ ይገባል፣በክልሉ ...
Read More »አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ የታገዱት ከዘረፋና ብክነት ጋር በተያያዘ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 22/2010) አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት በጥረት ድርጅት ውስጥ በተፈጸመ የገንዘብ ዘረፋና ብክነት ጋር በተያያዘ መሆኑን ብአዴን ገለጸ። የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን የማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት አቶ በረከት ስምዖን በተለያዩ ሚዲያዎች ብአዴንን በተመለከተ የሚያቀርቡት ውንጀላ መስረተ ቢስ ነው ብለዋል። ብአዴን የፖለቲካ ውሳኔ መስጠቱን የገለጹት አቶ ...
Read More »በምስራቅ ኦሮምያ አካባቢ በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላትና በኦሮምያ ፖሊስ መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ
በምስራቅ ኦሮምያ አካባቢ በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላትና በኦሮምያ ፖሊስ መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) በምስራቅ ኦሮምያ ባቢሌ ወረዳ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ወደ ገጠር በመግባት በህዝቡ ላይ ጥቃት በመክፈት ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኦሮምያ ፖሊስ በወሰደው የመከላከል እርምጃ 7 ወታደሮች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የልዩ ሃይል አባላቱ 2 የኦሮምያ ፖሊሶችን መምታታቸው ...
Read More »በመርጦ ለማርያም 44 የካቢኔ አባላት በህዝቡ ታገዱ
በመርጦ ለማርያም 44 የካቢኔ አባላት በህዝቡ ታገዱ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) የከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሞ ማካሄዳቸውን ተከትሎ ከክልል ተወክለው የመጡ ባላስልጣናት ያነጋገሩዋቸው ቢሆንም፣ ነዋሪዎቹ ሁሉም የካቢኔው አባላት ከስልጣን እንዲወርዱላቸው ጠይቀዋል። ጥያቄውን ተከትሎ አስተዳዳሪው የማትፈልጉን ከሆነ ሁላችንም ስልጣናችንን እንለቃለን ያሉ ሲሆን፣ የተወሰኑ የአካቢኔ አባላትን ለማቆየት የተደረገው ሙከራ ተቃውሞ እንዳጋጠመውና ህዝቡ ሁሉም አመራሮች ካልወረዱና በሌሎች ሰዎች ካልተተኩ እንደማይቀበል ...
Read More »በቤንች ማጂ ዞን በማጂ ወረዳ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሆስፒታል ስራ ባለመጀመሩ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው
በቤንች ማጂ ዞን በማጂ ወረዳ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሆስፒታል ስራ ባለመጀመሩ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የዞኑ ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን መምሪያ እና ግንባታውን ያከናወነው ድርጅት ርክክብ ባለመፈፀማቸው ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት አልቻለም። የጤና ባለሙያዎች የተመደቡ ቢሆንም፣ አገልግሎት መስጠት አልቻሉም። ለተከታታይ ህክምና ታማሚዎች ህክምና እየተሰጠ ያለው ከ 40 አመት በላይ እድሜ ባለው ...
Read More »መንግስት ቪ8 እየተባሉ የሚጠሩ መኪኖችን ከተማ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አገደ
መንግስት ቪ8 እየተባሉ የሚጠሩ መኪኖችን ከተማ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አገደ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመንግስት ባለስልጣናት ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ዋጋ ያላቸውን እጅግ ውድ መኪኖች የሚያሽከረክሩ ሲሆን፣ መኪኖቹ ለመስክ ስራ ካልሆነ ከተማ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ እገዳ መጣሉን የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቶ ይገዙ ዳባ ለመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ለመንግስት ባለስልጣናት ...
Read More »ሴናተር ጆን ማኬይ በቀብር ስነስርአታቸው ላይ ትራምፕ እንዳይገኙ ተናዘዙ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) ባለፈው ቅዳሜ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የአሪዞናው ሴናተር ጆን ማኬይ በቀብር ስነስርአታቸው ላይ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳይገኙ መናዘዛቸው ተሰማ። ጆን ማኬይ በቀብር ስነስርአታቸው ላይ እንዲገኙ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማና ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እንዲገኙላቸው በክብር ጋብዘዋል። ነገር ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀብር ስነስርአቴ ላይ እንዲገኙ አልፈግም ሲሉ ማኬይ እቺን ምድር ከመሰናበታቸው በፊት መናዘዛቸውን ሲ ኤን ኤን በዘገባው አስፍሯል። ...
Read More »የዛላ አንበሳ ድንበር በዜጎች ስምምነት ተከፈተ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) ለበርካታ አመታት ሲያወዛግብ የቆየው የዛላ አንበሳ ድንበር በዜጎች ስምምነት መከፈቱ ተሰማ። ይህንን ተከትሎም የሃይማኖት አባቶችን፣የሃገር ሽማግሌዎችን፣ሴቶችንና ወጣቶችን ያካተተ ቡድን በኤርትራዋ የንግድ ከተማ ሰናፌ ወደ ምትገኘው ሰርሃ ከተማ መጓዙ ተሰምቷል። 40 አባላትን አካቷል የተባለው ቡድን ከዛላአንበሳ አለፍ ብላ ወደ ምትገኘው ሰርሃ ከተማ ሲገባም በኤርትራ ወታደሮች አቀባበል ተደርጎለታልነው የተባለው ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዘለቀው የጸብ ግድግዳ ፈርሶ ሰላምና አንድነት ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጳጉሜ አራት አዲስ አበባ ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮችንና አባላትን ለመቀበል በአዲስ አበባ የተዋቀረው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ። በመላው ዓለም ያሉት የንቅናቄው አመራርና አባላት ጳጉሜን አራት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ለማወቅ ተችሏል። ትላንት በአዲስ አበባ የስብሰባ ማዕከል በተካሄደው የአቀባበል ኮሚቴው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መገኘታቸው ታውቋል። ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴን ጨምሮ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች የንቅናቄውን አመራሮች ፎቶግራፍ የሚገኝበት ቲሸርት በመልበስ ...
Read More »አቶ በረከት ስምዖን የመንቀሳቀስ መብቴ ተገድቧል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) የቀድሞ የብአዴን ከፍተኛ አመራርና የኢህአዴግ ቁልፍ ሰው አቶ በረከት ስምዖን የመንቀሳቀስ መብቴ ተገድቧል ሲሉ ገለጹ። ታዲያስ አዲስ ከተሰኘ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ አሁን ባለው ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ ገደብ ተጥሎብኛል ብለዋል። አቶ በረከት የመንቀሳቀስ መብታቸውን የገደበው የመንግስት አካል ይሁን ሌላ በግልጽ ያስቀመጡት ነገር የለም። የብአዴን የአሁኑን አመራር ክፉኛ የወቀሱት አቶ በረከት ስምዖን የተበላሹ አመራሮች ናቸው ...
Read More »