መንግስት ቪ8 እየተባሉ የሚጠሩ መኪኖችን ከተማ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አገደ

መንግስት ቪ8 እየተባሉ የሚጠሩ መኪኖችን ከተማ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አገደ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመንግስት ባለስልጣናት ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ዋጋ ያላቸውን እጅግ ውድ መኪኖች የሚያሽከረክሩ ሲሆን፣ መኪኖቹ ለመስክ ስራ ካልሆነ ከተማ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ እገዳ መጣሉን የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቶ ይገዙ ዳባ ለመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
ለመንግስት ባለስልጣናት የሚገዙት መኪኖች በሶስት የሞተር ደረጃዎች ተመድበው ከስምንት መቶ ሰባ ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጡ ይሆናሉ። የእገዳው መነሻ በሐምሌ 2009 ዓ.ም በሚኒስሮች ምክር ቤት የጸደቀውን አዋጅ ነው።
እርምጃው አገሪቱ ለዘመናዊ መኪኖች ግዢ እና ለነዳጅ ፍጆታ የሚወጣውን ወጪ የሚቀንስ ይሆናል።