በመርጦ ለማርያም 44 የካቢኔ አባላት በህዝቡ ታገዱ

በመርጦ ለማርያም 44 የካቢኔ አባላት በህዝቡ ታገዱ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) የከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሞ ማካሄዳቸውን ተከትሎ ከክልል ተወክለው የመጡ ባላስልጣናት ያነጋገሩዋቸው ቢሆንም፣ ነዋሪዎቹ ሁሉም የካቢኔው አባላት ከስልጣን እንዲወርዱላቸው ጠይቀዋል። ጥያቄውን ተከትሎ አስተዳዳሪው የማትፈልጉን ከሆነ ሁላችንም ስልጣናችንን እንለቃለን ያሉ ሲሆን፣ የተወሰኑ የአካቢኔ አባላትን ለማቆየት የተደረገው ሙከራ ተቃውሞ እንዳጋጠመውና ህዝቡ ሁሉም አመራሮች ካልወረዱና በሌሎች ሰዎች ካልተተኩ እንደማይቀበል አስታውቋል።