ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ መሪ ማርቲን ሹልትዝ ፣ የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆሴ ማኑኤል የጎበኙት ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ባሮሶ እና የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ቫን ሩምፒ፣ ኢትዮጵያ በእሰር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሀዝቡ ነጻነት እንዲከበር፣ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሻሻል፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ...
Read More »መንግስት አዲሱን የፕሬስ ካውንስል በበላይነት ለመምራት እየሰራ ነው
ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ እያካሄደ ካለው ሪፎርም ስራ ጋር በተያያዘ ለመወያየት ስብሰባ ቢጠራም፣ መንግስት በቀጥታ በማይመለከተው የፕሬስ ካውንስል ምስረታ አጀንዳ ላይ ሲመክር ውሎአል። ባለፈው ዕረቡ በሒልተን ሆቴል በተጠራው ስብሰባ ላይ የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት በሚል የሚታወቀውን የፕሬስ ካውንሰል በሚመሰረትበት ጉዳይ ላይ የመንግስትና የግል የሚዲያ ባለቤቶችና ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበትና ...
Read More »ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የተመለሱ የአማራ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ታወቀ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሀይል ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና ቻግኒ ከተሞች ሰፍረው የነበሩ ከ8 ሺ ያላነሱ የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን ባሳደሩት ጫና ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ ቢደረግም፣ በአካባቢው ያጋጠማቸው ያልጠበቁትና በህይወት የመቆየታቸውን ነገር አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። መሬት ያላቸው ተወላጆች ተመላሽ ተፈናቃዮችን ስራ ለመቅጠር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሰርተው ለማደር ተቸግረዋል። የዞን እና ...
Read More »የዘንድሮው ምርጫ ለኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ለተቃዋሚዎችም መልእክት ያስተላለፈ ነበር ተባለ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ህዝቡ በዘንድሮው የአካባቢና የወረዳ ምርጫ ህዝቡ ኢህአዴግን ለመቃወም እንደተጠቀመበት ከተለያዩ አካባቢዎች ያሰባሰብናቸው መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን፣ መልእከቶቹ ግን ለኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎችም የህዝቡን ጥያቄ እንዲሰሙ የሚያመለክቱ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እና አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። በደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት የዞኑ ሰብሳቢ የሆኑት መምህር አለማየሁ መኮንን ለኢሳት እንደገለጡት በዞናቸው የተካሄደው ...
Read More »ሲአን አባሎቹ እንደታሰሩበት አስታወቀ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ለሲዳማ ህዝብ አስተዳደራዊ መብቶች የሚታገለው ሲአን ለኢሳት እንደገለጸው ከዘንድሮው ምርጫ ራሱን ካገለለ በሁዋላ በገዢው ፓርቲ የሚደርስበት ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሎአል። ድርጅቱ እንደገለጸው በትናንትናው እለት አራት አባሎቹ በቡርሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው በእስራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል። አቶ ወገሳ ጭቆ በአራት ወራት እስራትና 500 ብር ፣ አቶ ለገሰ ለቀሙ በስድስት ወራት እስራትና 500 ብር፣ አቶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከመንግስት የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ ወታደራዊ የበላይነትን አግኝቷል። አርበኞች ግንባር በሚያዚያ 8፣ 2005 ዓ.ም በመንግስት የፈጥኖ ደራሽ ሀይል ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የመንግስት ወታደሮችን በመግደል 25 ማቁሰሉን፣ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9፣ 2005 ...
Read More »የኔሰው ገብሬ ራሱን ባጠፋባት ዋካ ከተማ ያለው ችግር ተባብሶ ቀጥሎአል
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ለኢሳት የተላከው መረጃ እንደሚያመለክተው ከወረዳ ጥያቄና ከመልካም አስተዳደርና ፍትህ ጋር በተያያዘ በዳውሮ ዞን በዋካ ከተማ ከሁለት አመት በፊት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ተከትሎ መንግስት ለዋካ እና ለተርጫ የወረዳ ከተማ ማእከልነት በመስጠት ችግሩን ለማብረድ ቢሞክርም፣ ህዝቡን ለአመጽ አነሳስተዋል የተባሉትን ግለሰቦች በማሰሩ ሌላ ችግር እየፈጠረ መምጣቱ ታውቋል። መንግስት በአቶ ዱባለ ገበየሁ፤ አባተ ኡቃ ፤ ...
Read More »ከፍንጂ ማምከኛ ድርጅት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት ተዘረፈ
ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ሶስት የፈንጅ አምካኝ ድርጅቶች መካከል በአገልግሎት ዘመኑም ሆነ በተግባሩ በግንባር ቀደምነት ስሙ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ፈንጅ አምካኝ ድርጅት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንደፈርስ መደረጉን ተከትሎ፣ ከተለያዩ የውጭ አገራት በእርዳታ ከተሰጠው በመቶ ሚሊዮኖች ከሚቆጠር ገንዘብ በተጨማሪ፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቹ በወታደራዊ መኮንኖች እንዲዘረፍ መደረጉን የውስጥ ምንጮች ገለጹ። አብዛኞቹ የድርጅቱ ከባድ መኪናዎች እና ሌሎች ንብረቶች ...
Read More »በአፋር እና በኢሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተገደሉ
ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአራት ቀናት በፊት በገዋኔ እና ቡሊወላይቶ ወረዳዎች በሚባሉት አካባቢዎች የታጠቁ የኢሳ ጎሳዎች በሰነዘሩት ጥቃት የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ከአራት ቀናት በፊት ኢሳዎች በአፋሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት ሁለት ሰዎች በጊል ተመትተው ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ወደ ናዝሬት ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተሰጣቸው ነው። ከትናንት በስቲያ በተመሳሳይ መንገድ በደረሰ ጥቃትም እንዲሁ አንድ የአፋር ...
Read More »የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው
ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደተናገሩት የዩኒቨርስቲው ሀላፊዎች ከዚህ በፊት ተሞክሮ ውጤት ያላስገኘውን ቢፒአር በድጋሚ እንዲጀመር በማድረጋቸው ሰራተኛውን እያሰቃዩት ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ሰራተኞች የትምህርት ደረጃቸውንና የሚፈልጉትን የስራ መስክ እንዲገልጹ ቢደረግም፣ በመጨረሻ ላይ ግን አብዛኞቹ ሰራተኞች ለቦታው አትመጥኑም ተብሎ ተነግሯቸዋል። እንደ ምንጮች ከሆነ ከ20 አመት ላናነሰ ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች የትምህርት ደረጃቸውን በማሻሻል ለተመደቡበት ...
Read More »