ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለባይ ግድብ መዋጪ ለማሰባሰብ በኖርዌይ ኦስሎ የተጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቷ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲቋረጥ ተደርጓል። በተመሳሳይ ሁኔታም በካልፎሪኒያ ሳንዲያጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ተብሎ የተጠራው ስብሰባ በአካባቢው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰብሰባው እንዲቋረጥ ተደርጓል። በሌላ በኩል ደግሞ በኔዘርላንድስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን የማፈናቀል ዘመቻ አውግዘዋል። ። የኢትዮጵያውያን ማህበር በሆላንድ ትናንት በአምስተርዳም ...
Read More »የታዋቂው ፖለቲከኛ እና ጸሀፊ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ ታፍኖ መወሰዱ ታወቀ
ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ነባር አባል፣ በአሁኑ ጊዜ የአረና ትግራይ ከፍተኛ የአመራር አባል እና ጸሀፊ የአቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ የሆነው አክህፎም አስገደ የታሰረው ባለፈው አርብ ነው። ሚያዚያ 16 ቀን 2005 ዓም ቀዳማዊ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራ እስር ቤት መታሰሩን እሁድ ሚያዚያ 20 ደግሞ በመቀሌ ውስጥ በሚገኝ ህጋዊ እውቅና በሌለው ድብቅ እስር ...
Read More »በመተማ ወረዳ አርሶ አደሮች ከመፈናቀላቸውም፡በላይ ድረንበር ጥሰዋል ተብለው ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ
ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጐንደር ዞን በመተማ ወረዳ ከዮሐንስ ከተማ በስተሰሜን <<ደለሎ>> ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ለረዥም ዓመታት መሬት ወስደው በሕጋዊ መንገድ ግብር ሲከፍሉ፡የቆዩ አርሶ አደሮች፣ አካባቢውን ጥለው እንዲሄዱ በወረዳው ውሳኔ መተላለፉን የሪፖርተር ዘገበ፡፡ ጋዜጣው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ድንበር አልፈዋል በሚል ሦስት አርሶ አደሮችም በሱዳን ታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ክልል ...
Read More »የህወሀት ጄኔራሎች በአለም ላይ ውድ የሆነውን የታንታለም ማእድንን በህገወጥ መንገድ እየዘረፉ ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ነው
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኬንቲቻ ቦረና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተባለ መንግስታዊ ድርጅት ከአመታት በፊት በጉጂ ዞን በሻኪሶና አናሶራ ወረዳዎች 2ሺ 500 ቶን የሚጠጋ ንጹህ የታንታለም ማእድን ማግኘቱ የመገናኛ ብዙህንን ትኩረት ስቦ ነበር። ኩባንያው ምንም አይነት የማጣሪያ ስራ ሳይሰራ ይህን ውድና ስትራቴጂክ ማእድን በርካሽ ዋጋ መሸጡ አገሪቱን እንደሚጎዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ...
Read More »በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ መንግስት የሚፈጽመውን የማፈናቀል እርምጃ አወገዘ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጭ የሚገኘው እና በ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የኢሕአዴግ መንግሥት አገራችንን ኢትዮጵያን በጠመንጃ ኃይል ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንሥቶ የኢትዮጵያ አንድነት ከባድ አደጋ ውስጥ ጥሎታል” ብሎአል። ኢህአዴግ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን መልኩን በመቀያየር በቦረናና በአርባ ጉጉ፥ በጋምቤላና በኦጋዴን፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በቤኒሻንጉል በሚኖሩት ወገኖቻችን ...
Read More »በዚህ አመት 30 ሺ ኢትዮጵያን የመን መግባታቸው ታወቀ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር እንዳስታወቀው በያዝነው አመት ብቻ 30 ሺ ስደተኞች ባህር አቋርጠው የመን የገቡ ሲሆን፣ ባለፉት 7 አመታት ወደ የመን ከገቡት ግማሸ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ወደ የመን የገቡ ሶማሊዎች ወዲያውኑ የስደተኝነት መታወቂያ የሚያገኙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያኖች ግን ይህን ወረቀት በቀላሉ አያገኙም። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሌሎች የአረብ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከሚገኙ 26 የትራፊክ መብራቶች አገልግሎት የሚሰጠው አንዱ ብቻ ነው
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከሚገኙ 26 የትራፊክ መብራቶች ከአንዱ በስተቀር ሌሎቹ አለመሥራታቸው ፤ የትራፊክ መጨናነቅና የአደጋ መንስኤ መሆኑ ተዘገበ። እንደ አድማስ ዘገባ የመብራቶቹ አለመሥራት ከዚህም ባሻገር በትራፊክ ፖሊሶች ላይ ከአቅም በላይ የሆነ የስራ ጫና ፈጥሯል፡፡ == አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠሩት የከተማዋ የትራፊክ መብራቶች ሲበላሹ ጥገና ስለማይደረግላቸው ለበለጠ ብልሽት እየተዳረጉ ከጥቅም ውጪ እንደሆኑ ...
Read More »ከደሀው ህዝብ በግብር ስም የሚሰበሰው ገንዘብ ለልማት እንዲውል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ ጠየቁ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከአመት በፊት የጀመሩትን ተቃውሞ በመቀጠል በአርብ የጁማ ጸሎት ላይ መንግስት ከደሀው ህዝብ በግብርና በተለያዩ መዋጮች ስም የሰበሰበውን ከ313 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ አህባሽ የተባለውን ሀይማኖት ለማስፋፋት ማዋሉን አጥብቀው በመቃወም ገንዘቡ ለልማት እንዲውል ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የታሰሩት ይፈቱ፣ በአገራችን ሰላም አጣን፣ ኢቲቪ አሸባሪ፣ መንግስት ...
Read More »የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ በሙስና መጨማለቁን አንድ ጥናት አመለከተ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የመንገደኞች የይለፍ ማረጋገጫ አሰጣጥ እና የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨማለቀ መሆኑን ከፌዴራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የተገኘ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ በመምሪያው በይለፍ ማረጋገጫ አሰራር ስርዓት ላይ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ተብለው በጥናቱ ከቀረቡት ሁኔታዎች ውስጥ የመረጃ አያያዝና ...
Read More »የመለስ ፋውንዴሽን ሰድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ግቢ ውስጥ ሊሰራ ነው
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀደም ብሎ ለወ/ሮ አዜብና ቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቤት ግንባታ ተመርጦ የነበረው የስድስት ኪሎው የስብሰባ ማእከል ግቢ፣ አሁን ለመለስ ፋውንዴሽን ህንጻ ማሰሪያ ሊውል መሆኑን ምንጮች ገለጹ። ወ/ሮ አዜብ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ባለፈው ሀሙስ ስፍራውን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችም ከህንጻ ግንባታው ጋር በተያያዘ ሊፈርሱ ይችላሉ፡፡ በከፍተኛ ጥበቃ በስፍራው ላይ የተገኙት ወ/ሮ ...
Read More »