በዚህ አመት 30 ሺ ኢትዮጵያን የመን መግባታቸው ታወቀ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር እንዳስታወቀው በያዝነው አመት ብቻ 30 ሺ ስደተኞች ባህር አቋርጠው የመን የገቡ ሲሆን፣ ባለፉት 7 አመታት ወደ የመን ከገቡት ግማሸ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ወደ የመን የገቡ ሶማሊዎች ወዲያውኑ የስደተኝነት መታወቂያ የሚያገኙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያኖች ግን ይህን ወረቀት በቀላሉ አያገኙም። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሌሎች የአረብ አገራት በመሄድ ስራ ለመስራት የሚፈልጉ ናቸው።

የየመን ወታደሮች በቅርቡ ታግተው የቆዩ 500 ኢትዮጵያውያንን ማስለቀቃቸው  ይታወሳል። ኢትዮጵያውያኑ በአረብ አገራት በሚቆዩበት ጊዜ አስከፊ በአሰሪዎቻቸው አስከፊ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደሚፈጸምባቸው ይታወቃል።