ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ማህበሩ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የባለራእይ ወጣቶች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ” ግንቦት27 ፣ 2005 ኣም ከጧቱ ሶስት ሰአት ላይ ሜክሲኮ በሚገኘው ፍርድ ቤት ለ3ኛ ጊዜ ቢቀርብም፣ ጉዳዩ ሳይታይ ቀጠሮ ተጠይቆበት እንደገና ወደ እስር ቤት ተመልሷል። ማህበሩ አያይዞም ከግንቦት 27 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ወጣት ብርሀኑ በቤተሰቡም ሆነ በጓደኞቹ ...
Read More »የዜና እርማት
ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተመልካቾቻችን እና አድማጮቻችን፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በስዊዘርላንድ-ጄኔቫ ስለተካሄደው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ባስተላለፍነው ዜና ላይ፤ ተቃውሞ ባሰሙት ኢትዮጵያውያን ሳቢያ ዝግጅቱ እንደከሸፈ መዘገባችን ይታወሳል። ይሁንና ዜናው ስህተት እንዳለበት የደረሰንን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረግነው ማጣራት መሰረት የኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞ እስከ ምሽቱ 6፡00፣ ዝግጅቱ ደግሞ ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ እንደተካሄደ ተገንዝበናል። በመሆኑም በስዊዘርላንድ-ጄኔቭ የተካሄደውን የዓባይ ቦንድ ሽያጭ ...
Read More »ከተቃውሞ ሰልፉ በሁዋላ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አመራሮች እየተገመገሙ ነው
ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በማግስቱ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አመራሮችን እንዲሁም በፕሮፓጋንዳ መስክ ላይ የተሰማሩትን በመጥራት ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። አብዛኞቹ አመራሮች ሂስና ግለሂሳቸውን እንዲያወርዱ የተጠየቁ ሲሆን፣ የድርጅቱ አባሎች በጸረ ህዝቦች ፕሮፓጋንዳ በመወናበድ እና ለግንባሩ ርእዮተ አለም ትኩረት ባለመስጠት ድርጅቱን ከውስጥ እያዳከሙት ...
Read More »በአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ የሚመራ የአርቲስቶች እና ጋዜጠኞች ቡድን የሶማሊ ክልልን ጎብኝቶ ምስክርነት ሊሰጥ ነው
ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደሬሽን ምክር ቤት በአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ የሚመራ የአርቲስቶች ቡድንን እና ጋዜጠኞችን በማሰባሰብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የጎብኝት መረሀ ግብር በጅጅጋ እና በሌሎች የሶማሊ ዞኖች አዘጋጅቷል። አርቲስቶቹና ጋዜጠኞች ከትናንት ሰኞ ጀምሮ ወደ ጂጂጋ ይጓዛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ጉብኝታቸውም ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ታውቋል። የጉዞው ዋና አላማ በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ ቦታዎችን በመጎብኘት ልማቱ ...
Read More »የግብጽ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ላይ ሲመክሩ የሚያሳይ ቪዲዮ የፋ ወጣ
ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግብጹ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን በመሰብሰብ በመሰራት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ወይይቱ ለተቃዋሚዎች ሳይነገር በቀጥታ በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ በመደረጉ ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን ሲገልጹ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ደግሞ ይቅርታ ጠይቋል። አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው በውይይቱ ላይ የተለያዩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች አስገራሚ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ሙርሲ በቅርቡ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ...
Read More »ኢህአግ በሁመራ አካባቢ ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ
ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከመከላከያ ሰራዊት 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ ጠመንጃ፣ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በተሳካ ሁኔታ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ ደስታውን እየገለጸ ነው
ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት በተሳካ ሁኔታ ያካሄደውን ሰልፍ በተመለከተ የተለያዩ ወገኖች ለኢሳት እየደወሉ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ፓርቲው ተቃውሞውን ከማዘጋጀት ጀምሮ አጠር እና ምጥን ያለ ዝግጅት በማቅረቡ ደስታቸውን የገለጸት አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ተቃውሞው ብልጭታ እንድናይ አድርጎናል ብሎአል አንድ ሌላ ሴት ደግሞ በትናንትናው ሰልፍ “ትንሽ ትንሽ” ዲሞክራሲ እየመጣ ይመስለኛል ብለዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ መንግስት የሰጠውን ማስፈራሪያ አመራሮች እና የህግ ባለሙያዎች ውድቅ አደረጉት
ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት25 ከፍተኛ ህዝብ የተገኘበትን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ የኢህአዴግ የጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሬዲዮ ፋና ሲናገሩ ” የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ” ብለዋል። ፓርቲው ያዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተፈለገ አላማ አውሎታል ያሉት አቶ ሬድዋን ፣ በሰልፉ በአብዛኛው ...
Read More »በሰስዊዘርላድ-ጄኔቭ ኢህአዴግ የጠራው የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ “ከ ዓባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ!” የሚል መፈክር ባነገቡ ኢትዮጵያውያን ብርቱ ተቃውሞ ከሸፈ
ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህዴግ -በጄኔቭ ለ ዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ለማካሄድ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ በምስጢር ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ለደጋፊዎቹ ብቻ የዝግጅቱን ዕለት፣ቦታ እና ሰዓት አስመልክቶ ጥሪ ያቀርባል። ይሁንና ኢህአዴግ መቼ እና የት ዝግጅቱን ሊያደርግ እንዳሰበ የውስጥ መረጃ የደረሳቸው በጄኔቭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጎን ለጎን የተቃውሞ ዝግጅት ሲያስተባብሩ ይከርማሉ። ከተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ መንግስት ሰበቦችን እየፈለገ ነው
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ በተለያዩ ክፍለከተሞች ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል። የተለያዩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት መስተዳድሩ በሰልፉ ላይ ብዙ ህዝብ እንዳይገኝ ለማድረግ ከቤት ጋር የተያያዙ አጀንዳዎችን በማንሳት ህዝቡ ወደ ተቃውሞ ሰልፉ እንዳይሄድ ለማድረግ እየጣረ ነው። “ኢህአዴግ ድህነትን ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ እየተጠቀመበት መሆኑን፣ በከተማው ያሉ የቤት እና ...
Read More »