የዜና እርማት

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ተመልካቾቻችን እና አድማጮቻችን፣

ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በስዊዘርላንድ-ጄኔቫ ስለተካሄደው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ባስተላለፍነው ዜና ላይ፤ ተቃውሞ ባሰሙት ኢትዮጵያውያን ሳቢያ ዝግጅቱ እንደከሸፈ  መዘገባችን ይታወሳል። ይሁንና ዜናው ስህተት እንዳለበት የደረሰንን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረግነው ማጣራት መሰረት የኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞ እስከ ምሽቱ 6፡00፣  ዝግጅቱ ደግሞ ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ  እንደተካሄደ ተገንዝበናል። በመሆኑም  በስዊዘርላንድ-ጄኔቭ የተካሄደውን የዓባይ ቦንድ ሽያጭ አስመልክቶ  ባስተላለፍነው ዘገባ ለተፈጠረው ስህተት አድማጮቻችንን እና ተመልካቾቻችንን ከፍ ያለ ይቅርታ እንጠይቃለን!