ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ወገኖቻቸው ድጋፍ ለማግኘት የተንቀሳቀሱ 35 ወጣቶች ታሰሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ/ም ) 35 የጨርቆስና እና አካባቢው ወጣቶች ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውንና ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በሰንዳፋ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ተናግራል። ወጣቶቹ ከአካባቢያቸው በሰበሰቡት ገንዘብ የገዟቸውን ምግብ እና ቁሳቁሶች አስረክበው ሲመለሱ ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ፖሊስ ምግብ እና ቁሳቁስ ...
Read More »የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳን በድጋሜ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳን በድጋሜ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ ( ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ/ም ) የቀድሞው ኦህዴድ የአሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ለሶስት ቀናት በጅማ ከተማ ባካሄደው 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔው የቀድሞው የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን እና አቶ ለማ መገርሳን በነበሩበት እንዲቀጥሉ በሙሉ ...
Read More »በሕጻናት ሞት ኢትዮጵያ ከግንባር ቀደም አምስት ሃገራት አንዷ መሆኗ ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011)በሕጻናት ሞት ኢትዮጵያ በአለም ላይ ከግንባር ቀደም አምስት ሃገራት አንዷ መሆኗን ተገለጸ። የተባበሩት መንግስታት ተቋም እንዳስታወቀው ባለፈው የምዕራባውያኑ አመት 2017 133ሺ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ሞተዋል። የተባበሩት መንግስታት ኢንተር ኤጀንሲ ቡድን ከአለም ጤና ድርጅት፣ከተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የሕጻናት ድንገተኛ ፈንድና ከአለም ባንክ የሰበሰባቸውን መረጃዎች መሰረት በማድረግ ባጠናቀረው ዘገባ በ2017 አመተ ምህረት የሞቱት 133ሺ ሕጻናት እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ነው። ከነዚህ ...
Read More »አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከነገ በስቲያ አዲስ አበባ ይገባል
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011) በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከነገ በስቲያ አዲስ አበባ ይገባል። በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ የነበረውን አፈና በተለይም በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ግድያ በማውገዝ በአለም አደባባይ የተቃውሞ ድምጹን ላሰማው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከፍተኛ የአቀባበል መርሃ ግብር እንደተዘጋጀለትም ተመልክቷል። በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ተወዳድሮ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ያገኘው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ፣ቢሊየኖች በቀጥታ በቴሌቪዥንና በአካል ...
Read More »የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በመላ ሃገሪቱ የሕግ የበላይነት ይከበር አለ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/በመላ ሃገሪቱ የሕግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ከሕግ አግባብ ውጭ ከአማራ ክልል የተወሰዱ መሬቶች እንዲመለሱ፣እንዲሁም ይህንን የመብት ጥያቄ ባነሱ ወገኖች ላይ የሚደርሰው እስር፣እንግልትና ማፈናቀል ይቁም ሲልም ጥሪ አቅርቧል። በመተከል፣በጅጅጋ፣በቡራዩና አካባቢው እንዲሁም በጉራጌ ዞን ማረቆና ወለኔ ለተከሰተው ግጭትና እልቂት መንግስት ህግና ስርአት የማስከበር ግዴታውን ባለመወጣቱ የተከሰተ ነው ሲልም የአማራ ...
Read More »ኢትዮጵያ የተደቀኑባት ፈተናዎች የገዘፉ መሆናቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011) ኢትዮጵያ የተደቀኑባት ፈተናዎች የገዘፉ መሆናቸውን አቶ ሌንጮ ለታ ገለጹ። የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ የፖለቲካ ሃይሎችም ከችግሩ ስፋት አንጻር በሃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል። አዲሶቹ የኢሕአዴግ መሪዎች ከ27ቱ አመት ኢሕአዴግ በተለየ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አመልክተዋል። የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/በቅርቡ በቀጣይ ጉዞው ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም አስታውቀዋል። ለዊሊያም ዴቪሰን በኢትዮ-ኢንሳይት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት አቶ ...
Read More »ኦዴፓ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ዶክተር አብይ አሕመድንና አቶ ለማ መገርሳን የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ። 9 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና 55 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ተመርጠዋል። ነባሮቹን 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በይፋ ያሰናበተውና ሌሎችንም በተመሳሳይ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ያስወገደው የቀድሞው ኦሕዴድ የአሁኑ ኦዴፓ ከመረጣቸው 55 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት 39ኙ አዲስ መሆናቸው ተመልክቷል። ላለፉት 28 አመታት ...
Read More »እስራኤል 1ሺ ቤተ እስራኤላውያንን ወደ ሃገሯ ልታስገባ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) የእስራኤል መንግስት 1ሺ ቤተ እስራኤላውያንን ወደ ሃገሯ ለማስገባት መወሰኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ ገለጹ። ወደ እስራኤል ለመግባት በኢትዮጵያ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት 8ሺ ያህል ቤተእስራኤላውያን መሆናቸውን መረጃዎች አመልክተዋል። ነገር ግን የእስራኤል መንግስት የፈቀደው ለአንድ ሺ ሰዎች ብቻ መሆኑ በመብት ተሟጋቾች ዘንድ ተቃውሞን አስከትሏል። “ዘ ሪፐብሊክ”የተባለው ዲጂታል ሚዲያ እንደዘገበው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ 1ሺ ቤተ እስራኤላውያን እንዲገቡ መወሰኑን ...
Read More »በቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩት ግለሰቦች ክስ እንዲመሰረትባቸው ትዕዛዝ ሰጠ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በሚቀጥሉት 7ቀናት ክስ እንዲመሰረትባቸው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። ግለሰቦቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ትዕይንተ ህዝብ ላይ ቦምብ በማፈንዳት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠትና ድርጊቱን በማቀነባበር እጃቸው አለበት የተባሉ ናቸው። አቃቤ ሕግ ምርመራዬን አልጨረስኩም በማለት ተከሳሾቹን በማዕከላዊ ምርመራ ውስጥ ማቆየቱ ይታወቃል። ሰኔ 16/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጀመሩትን የለውጥ ...
Read More »ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) አዲስ አበባ ላይ ትላንት በቁጥጥር ስር የዋሉት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ታወቀ። ፍርድቤት ዛሬ ይቀርባሉ ተብሎ እንደነበርም መረጃዎች አመልክተዋል። በአዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አስተባባሪዎች አንዱ የነበረው ብርሃኑ ተክለያሬድ በ9 የፌደራል ፖሊስ አባላትና በሶስት ደህንነቶች ትላንት በቁጥጥር ስር የዋለው አንድ ሆቴል ውስጥ መሆኑም ተመልክቷል።
Read More »