የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ሃላፊነት አለበት ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ

የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ሃላፊነት አለበት ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) ጠ/ሚኒስትር አብይ ይህን የተናገሩት በሊቀመንበርነት የሚመሩትን የኦህዴድን 9ኛ ድርጅታዊ ጉበኤ ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር ነው። ኦሮሞ “ የዚህን አገር አንድነት የማስጠበቅ ሃላፊነት አለበት” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስና ለውጡን ለመቀልበስ የሚሞክሩ ሃይሎችንም አስጠንቅቀዋል። ከጠላቶቻችን ጋር ሆናችሁ የኦሮሞን ትግል ወደ ሁዋላ ለመመለስ ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት7 የአቀባባል ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካከል 2ቱ ታሰሩ

የአርበኞች ግንቦት7 የአቀባባል ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካከል 2ቱ ታሰሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድና ወጣት መኮንን ለገሰ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ መኖሪያ ቤታቸው እንዲፈተሽ ተደርጓል። ፖሊሶች የጦር መሳሪያና ገንዘብ እንዳለ ተጠቁመው መምጣታቸውን ለቤተሰቦች ቢናገሩም፣ ምንም ነገር እንዳላገኙ ታውቋል። መንግስት ከሰመሞ ግጭት ጋር በተያያዘ ጠርጥሮ እንደያዛቸው ፖሊሶች ተናግረዋል። ፖሊስ ከአዲስ አበባና አዋሳኝ ከተሞች ...

Read More »

ኤርትራና ጅቡቲ በጋራ ጉዳያቸው ላይ መከሩ

 (ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) በድንበር ውዝግብ ለዓመታት በባላንጣነት የቆዩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያዝ አፈወርቂና የጅቡቲው መሪ ኢስማኤል ኡማር ጊሌህ ተገናኝተው በጋራ ጉዳያቸው ላይ መከሩ። ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ውስጥ የተገናኙት ሁለቱ መሪዎች አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለመጀመርና ጉርብትናቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር ገለጹ። ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው እንደረገጹት ሁለቱ መሪዎች ስምምነቱን የፈረሙት በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ነው። ሁለቱም መሪዎች ይህ አዲስ ምዕራፍ ...

Read More »

አቶ ለማ መገርሳ የኢሳት የዓመቱ ምርጥ ሰው ተሸላሚ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) ኢሳት በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት አቶ ለማ መገርሳ የ2010 አሸናፊ ሆኑ። በህዝብ ድምጽ የሚካሄደውንና በአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስም የተሰየመውን የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ማሸነፋቸው የተገለጸው ዕሁድ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ነው። መስከረም 6/2011 በተካሄደው በዚህ በኢሳት የአዲስ ዓመት ዝግጅት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል። የኢሳትን የ8 ዓመታት ጉዞ ...

Read More »

አቶ ኦባንግ ሜቶ አቀባበል ተደረገላቸው

 (ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011)የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በጋምቤላ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። አቶ ኦባንግ ሜቶ ከ16 ዓመታት በኋላ ወደ ጋምቤላ ሲያመሩ የከተማዋ ነዋሪዎችና የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት አደባባይ በመውጣት እንደተቀበሏቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ ኦባንግ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የልዑካን ቡድን አባላትን በመምራት ወደ ኢትዮጵያ ያመሩት ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውም ታውቋል። በኢትዮጵያ ሰላማዊ ...

Read More »

የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) መንግስት ያለበትን የህግ የበላይነትና የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ለመወጣት ማንኛውንም ህጋዊ፣ የማያዳግምና ተገቢ ርምጃ ለመውሰድ በሙሉ ዝግጅትና አቋም ላይ ነው ሲል የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ የጥፋት ሃይሎች የመንግስትን ሆደ ሰፊነት ከአቅመ ቢስነት በመቁጠር የወጣቱን ስሜት በማነሳሳት የሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየተበራከቱ በመምጣታቸው መንግስት ሰላምና መረጋጋትን የማስከበር ...

Read More »

በቡራዩ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከግለሰብ ጸብ ጋር የተገናኘ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) በቡራዩ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት በአንዲት የ6 ዓመት ሕጻን ላይ ከተፈጸመ አሰቃቂ ግድያ ጋር ተያይዞ ችግሩ ቢባባስም ጉዳዩ ከግለሰብ ጸብ ጋር ብቻ የተያያዘ እንዳልነበር አቶ ለማ መገርሳ ገለጹ። የብሔር ግጭት ለመፍጠር ታርጋ በሌላቸው ተሽከርካሪዎች አሰላ ድረስ የነበሩ የትንኮሳ ሙከራዎችም በሕዝብ ጥረት መክሸፋቸውን አስረድተዋል። በቡራዩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማስመልከት ትናንት ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት አቶ ለማ ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያን መበተን አይቻልም አሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/201) የወንድምን ደም ማፍሰስ፣ ህጻናትን ማሰቃየት ትችላላችሁ ኢትዮጵያን መበተን ግን መቼም አይሳካችሁም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቡራዩ ሰሞኑን የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን ከጎበኙ በኋላ እንደተናገሩት የወንድሞቻችሁን ደም በመጠጣት የምትረኩ ሃይሎች ኢትዮጵያን ማፍረስ ግን ህልም ነው ሲሉ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተፎካካሪና አክቲቪስት ነን ባዮች በማስተዋል እንድትንቀሳቀሱ እጠይቃለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። መንግስት ለተጎጂዎች ድጋፍ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚከሰቱት ግጭቶች በአንድ ማዕከል እንደሚቀነባበሩ የድህንነት መስሪያ ቤት አስታወቀ

በኢትዮጵያ የሚከሰቱት ግጭቶች በአንድ ማዕከል እንደሚቀነባበሩ የድህንነት መስሪያ ቤት አስታወቀ ( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) የብሄራዊ ድህንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያም ሆነ በሶማሊ ክልል የተፈጠሩት ግጭቶች አላማቸው አንድ ነው ብሎአል። በአዲስ አበባ ዙሪያ የተከሰተው ግጭት በሶማሊ ክልልና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጠሩት ግጭቶች ተቀጽላ ነው። የግጭቶች ዋና አላማ የለውጡን እንቅስቃሴ መግታትና በመስከረም ወር የሚካሄደውን የኢህአዴግ ...

Read More »

የመስቃን ቤተ ጉራጌዎችንና የማረቆ ብሄረሰብ አባላትን ለማጋጨት በተደረገ ጥረት የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ

የመስቃን ቤተ ጉራጌዎችንና የማረቆ ብሄረሰብ አባላትን ለማጋጨት በተደረገ ጥረት የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ ( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) መስከረም 3 ቀን 2011 ዓም የወረዳ የካቢኔ አባላት ምርጫን ተከትሎ በምርጫው የተከፉ ወገኖች የማረቆን ብሄረሰብና የመስቃን ጉራጌ ብሄረሰቦችን አነሳስተው በፈጠሩት ግጭት ከሁለቱም ወገን ከ30 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ግጭቱን ለማብረድ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ የገባ ሲሆን፣ የጦር ...

Read More »