ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) አዲስ አበባ ላይ ትላንት በቁጥጥር ስር የዋሉት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ታወቀ።

ፍርድቤት ዛሬ ይቀርባሉ ተብሎ እንደነበርም መረጃዎች አመልክተዋል።

በአዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አስተባባሪዎች አንዱ የነበረው ብርሃኑ ተክለያሬድ በ9 የፌደራል ፖሊስ አባላትና በሶስት ደህንነቶች ትላንት በቁጥጥር ስር የዋለው አንድ ሆቴል ውስጥ መሆኑም ተመልክቷል።