የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 15/2011)የኢትዮጵያ መንግስት በገባው ቃል መሰረት ሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ። የሃገሪቱን ወህኒ ቤቶች ከሕግ አግባብ ውጭ ከታሰሩ ሰዎች ነጻ በማድረግ የጀመረውን ርምጃ መቀልበስ አይኖርበትም ሲልም አሳስቧል። ከሰሞኑ ግጭት ጋር በተያያዘ ሰልፍ በመውጣታቸው የታሰሩ በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቅርቧል። “የጅምላ አፈሳና እና እስራት በሰብዓዊ መብት አከባበር የታየውን ርምጃ ስጋት ውስጥ ጥሎታል” በሚል ርዕስ ...

Read More »

የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተወሰዱ

(ኢሳት ዲሲ– መስከረም 15/2011) ባለፈውሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ። ትላንት ልጆቻቸውን ለመጠይቅ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገኙት በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መጠየቅ ሳይችሉ እዚያው አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ለኢሳት እንደተናገሩትየማሰልጠኛው ጠባቂዎች ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ስለሆኑ ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል :: ይሁን እና ምን አይነት ስልጠና ላይ እንዳሉ የገለፁላቸው ነገር የለም:: ለልጆቻቸው የቋጠሩትን ስንቅም በአካባቢው ላገኟቸው የኔ ቢጤዎች መፅውተው ተመልሰዋል:: በአዲስ አበባ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ ወጣቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታፈሱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ ::  

Read More »

የመስቀል ደመራ በአል ነገ ይከበራል

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የመስቀል ደመራ በአልን በነገው እለት በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአሉ በፍቅርና በሰላም እንዲከበር ጥሪ አቅርባለች። በአሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ከበአሉ ጋር ብተያያዘ የእስልምና እምነት ተከታዮች ነገ የሚከበረውን የመስቀል ደመራ ማስከበሪያ ቦታ በማጽዳት ለክርስቲያን ወንድምና እህት ወገኖቻቸው ያላቸውን ክብር አሳይተዋል። ምዕመኑ የመስቀል በዓልን ሲያከበር የመስቀል መገለጫ በሆነው ...

Read More »

የተለያዩ የኦሮሞ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ኢሳትን “በጸረ-ኦሮሞነት” ከሰሱ

የተለያዩ የኦሮሞ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ኢሳትን “በጸረ-ኦሮሞነት” ከሰሱ ( ኢሳት ዜና መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ፣ የተባበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣ የኦሮምያ ነጻነት አንድነት ግንባር እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በጋራ ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ወይም ኢሳት ተብሎ የሚጠራው ጸረ-ኦሮሞ የሚዲያ ተቋም በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሃሰት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከጀመረ የሰነባበተ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ...

Read More »

የዛሬ ሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታውቁ::

የዛሬ ሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታውቁ:: ( ኢሳት ዜና መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ/ም ) ትላንት ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገኙት በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መጠየቅ ሳይችሉ እዚያው አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ለኢሳት እንደተናገሩት የማሰልጠኛው ጠባቂዎች ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ስለሆኑ ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል :: ይሁን ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የ28 ሰዎች ተገድለዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ። መስከረም 7/2011 በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን 5 ሰዎች ጨምሮ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 7/2011 28 ሰዎች መገደላቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነር ናቸው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከግድያውና ሁከቱ ጋር ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ከእርስ በርስ ሽኩቻ እንዲወጡ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011)ኢትዮጵያውያን ከእርስ በርስ ሽኩቻ ወተው በአንድነት በመሆን ለሃገራቸው ሰላም እንዲንቀሳቀሱ ብጹእ ዶክተር አቡነ ኤዎስጣጢዮስ ጠየቁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጹእ ዶክተር አቡነ ኤዎስጣጢዎስ ከ10 አመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዛቸው በፊት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያውያን ለሃገራቸው ሰላምና አንድነት በጋራ እንዲቆሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ብጹእ አቡነ ኤዎስጣጢዎስ በ1997 የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በመንግስት የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን አባል በነበሩበት ...

Read More »

በብአዴን ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011) በቅርቡ በባህርዳር ይካሄዳል ከተባለው የብአዴን ጉባኤ በፊት በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በድርጅቱ ስራአስፈጻሚ አባላት መካከል ከፍተኛ አለመተማመንና አለመግባባት መፈጠሩን ከአካባቢው ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በብአዴን ውስጥ ያለው ሃይል ሂደቱን ላለማስቀልበስ ጠንክሮ እየሰራ ቢሆንም የተወሰኑ የድርጅቱ አመራሮች ጉባኤውን ለማደናቀፍ እየሰሩ ናቸው ተብሏል። የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ስራ አስፈጻሚ አካላት በውጥረት ውስጥ ሆነው በባህርዳር ...

Read More »

በጋምቤላ 5 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011) በጋምቤላ ከተማ 5 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ። ባለፉት ሁለት ቀናት በከተማው ህዝብ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው የሃይል እርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሀገሪቱ ለውጥ ቢኖርም በጋምቤላ ግን ለውጡን ለማየት አልቻልንም በሚል የተጀመረው ተቃውሞ ተጨማሪ የሰው ህይወት ሊያጠፋ እንደሚችል ነዋሪዎች ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በክልሉ አስተዳደራዊ ለውጥ እንዲመጣ እንቅስቃሴ በማድረግ ...

Read More »

በጋምቤላ ወታደሮች 4 ሰዎችን ገድለው ከ17 ያላነሱትን አቆሰሉ

በጋምቤላ ወታደሮች 4 ሰዎችን ገድለው ከ17 ያላነሱትን አቆሰሉ ( ኢሳት ዜና መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት በንዌርና አኝዋክ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በወሰደው እርምጃ 4 ሰዎች ሲገደሉ 17 ያክል ደግሞ ቆስለዋል። የክልሉ ወጣቶች የክልሉ መስተዳደር ስልጣን እንዲለቁ መጠየቃቸው ያላስደሰታቸው የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ከተቃዋሚዎች ጋር መጋጨታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው አኝዋክ ሰርቫይቫል አቶ ኝካው ኦቻላ የአኝዋክ ሰርቫይቫል ...

Read More »