ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በከተማው የታየው ከፍተኛ የውሃ እጥረት በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንድ የከተማው ነዋሪ ውሃ በቦቴ ጭነው አንድ ጀሪካን ውሃ በ10 ብር እየሸጡ ሲሆን፣ አብዛኛው ነዋሪ ደግሞ ወንዝ ውሃ በመጠቀም ችግሩን ለማለፍ እየሞከረ ነው። ” ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፣ ስለ ንጹህ ውሃ ሳይሆን ውሃ አግኝቶ ጥምን ስለመቁረጥ ...
Read More »አፍሪካ እየተመነደገች ነው ሲሉ ፕ/ት አቦማ ተናገሩ
ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ40 በላይ አፍሪካ መሪዎችን በአንድ ጊዜ ጋብዘው በማነጋገር ላይ ያሉት የአሜሪካው መሪ ፕ/ት ባራክ ኦባማ አፍሪካ እያደገችና ጠንካራ አህጉር እየሆነች መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሳይሆን አፍሪካ በአለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን መጀመሩዋን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። የአፍሪካ ስኬት ከወጣት ህዝቦቿ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል። አሜሪካ በአፍሪካ የጸጥታ ስራ ለመስራትና ለኢንቨስትመንት 14 ቢሊዮን ዶላር መመደቡዋን ...
Read More »የብሪታንያ መንግስት የኢትዮጵያን ጉዳይ አስፈጻሚ አስጠርቶ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በጽህፈት ቤቱ አነጋገረ።
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ከተያዙ በሁዋላ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ያለፉት 44 ቀናትን በደብረዘይት አየር ሃይል እስር ቤት ውስጥ ካሳለፉ በሁዋላ የብሪታንያ መንግስት የኢትዮጵያን ጉዳይ አስፈጻሚ አስጠርቶ በጽህፈት ቤቱ አነጋግሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሲሞንድስ አቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር አገልግሎት በአፋጣኝ እንዳያገኙ መደረጉ እንዳሳሰባቸው ለኢትዮጵያው ዲፕሎማት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም ...
Read More »የመለስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ስብሰባ ህዝቡ እንዳይቆጣ በሚል ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደረገ
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመለስ ዜናዊን ፋውንዴሽን እንሰራለን በሚል ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችና አርሶአደሮች በነፍስ ወከፍ ከ50 ጀምሮ እንዲያዋጡ መገደዳቸው በቅርቡ ከተደረገው የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቁጣ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ በመሰጋቱ ፣ የገንዘብ መሰብሰቡ ሂደት ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል። ፋውንዴሽኑን ለማሰራት ከሚፈለገው ገንዘብ 10 እጥፍ እንደተሰበሰበ የሚነገርለት ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራ ሲሆን እስካሁን ድረስ ወጪና ...
Read More »የአዲስአበባመስተዳድር ፖሊሶችን ማሰልጠኑ ቀጥሎአል
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ፖሊስኮሚሽንባለፉትወራትለተካታታይ 3 ወራትያክልለሁሉምመካከለኛናከፍተኛፖሊስመኮንኖች ለደህንነትስራእገዛበሚልስልጠናከሰጠ በሁዋላ፣ ከሃምሌ 26 ቀን 2006 ዓ.ምጀምሮደግሞበአዲስአበባምኒልክትምህርትቤትግቢአዳራሽውስጥበስሩለሚገኙትሁሉም የፖሊስአባሎችስልጠናእየሰጠእንደሚገኝ ታውቋል። ስልጠናውለሁሉምፖሊሶች በተለያየዙርእንደሚሰጥይጠበቃል፡፡የስልጠናው ዋና አላማ መጪውን ምርጫ ተከትሎ የፖሊሱን ሚና ማሳወቅ፣ የፖሊሶችን የፖለቲካ አቋም መገምገምና የደህንነት አጠባበቅ ስልጠና መስጠት ነው ። በስልጠናው ላይ አንዳንድ ፖሊሶች የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚና የመብት ጥሰቶችን እያነሱ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።
Read More »ጋዜጠኞች ክሳቸውን እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን መስማታቸውን ተናገሩ
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓቃቤሕግ «ሕገመንግሥታዊሥርዓቱንበአመጽለመናድ…» በሚልክስመሰረትኩባቸውያላቸውአምስት መጽሔቶችእና አንድጋዜጣእስካሁንየክስቻርጅእንዳልደረሳቸውናጋዜጠኞቹ መከሰሳቸውንእንደማንኛውምሰውየሰሙት በቴሌቪዥንመሆኑንእየተናገሩነው፡፡ የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ እንደሚከሰሱ ያወቁት ከመገናኛ ብዙሃን መሆኑ አስገርሟቸዋል። የክስ ቻርጁን ለጋዜጠኞች ልኮ ከማሳወቅ ይልቅ ይህን አይነት አካሄድ ለመጠቀም ለምን እንደተመረጠ ግልጽ አልሆነም።
Read More »የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ሊስብ አልቻለም
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ግብዣ በዋይት ሃውስ እንዲሰበሰቡ ቢደረገም፣ አለማቀፍ እውቅና ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ብዙም ለጉባኤም ትኩረት አለመስጠታቸውን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። አንድ ከአፍሪካ ውጭ ያለ መሪ አሜሪካን ሲጎበኝ የሚሰጠውን የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ያክል 50 የአፍሪካ መሪዎች ተደምረው ሊያገኙ አልቻሉም። ቢቢሲ ከአንድ መለስተኛ ዘገባ በስተቀር ሌሎች ዘገባዎችን ያላስተናገደ ሲሆን፣ ሲኤን ኤን ...
Read More »የኢድ አልፈጥር በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበሮዋለ።
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-1 ሺህ 435ኛው የኢድ አልፈጥር በመላው የእስልምና ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም የነበረው ክብረበአል በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ድምጻችን ይሰማ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይካሄድ ባዘዘው መሰረት፣ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀርቷል። የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ሰሞኑን በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሙስሊም ዜጎች በእስር ቤት ...
Read More »መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ የተለመደውን የተቀነባበረ ፊልም ለህዝብ አቀረበ
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም አቶ አንዳርጋቸውን በድጋሜ በማቅረብ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከባድ ሚስጢር እንዳወጡ አድርጎ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው በረሃ በነበረበት ወቅት ለአመታት ሲተኛበት የነበረውን ሰሌን ምንጣፍና ይለብሰው የነበረውን ብርድ ልብስ ኢሳት ፎቶውን ያገኘ ሲሆን፣ በረሃ ላይ የሚገኙ የግንቦት7 ታጋዮች እንደገለጹት ብርድ ልበሱን አንዳርጋቸው ከመቀበሉ በፊት ሌሎች 3 ሰዎች ሲጠቀሙበት ...
Read More »ወጣቶች “በጸረ ሰላም ሃይሎች” ላይ እርምጃ እንዲወስዱብአዴን ጠየቀ
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በከተሞች የሚገኙ አውራጅና ጫኝ፤ሊስትሮ፤ሱቅ በደረቴ፤ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶችን፤ በተለያዩ አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶችን እና በአደረጃጀት ያልታቀፉ ሌሎች ወጣቶችን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀው ሰነድ ፣ “የጥፋት ፖለቲከኞች እንቅስቃሴ በመላ የከተማችን ሰላም ወዳድ ወጣቶች የተደራጀና የነቃ ተሳትፎ እንዲከሽፍ ካልተደረገ በመላ ቀልቡ ወደ ልማቱ የገባው ህዝባችን በተለይ ደግሞ ተጠቃሚ እየሆነ የመጣው ወጣቱ ...
Read More »