መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ የተለመደውን የተቀነባበረ ፊልም ለህዝብ አቀረበ

ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም አቶ አንዳርጋቸውን በድጋሜ በማቅረብ፣ አቶ አንዳርጋቸው

ከባድ ሚስጢር እንዳወጡ አድርጎ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው በረሃ በነበረበት ወቅት ለአመታት ሲተኛበት የነበረውን ሰሌን ምንጣፍና ይለብሰው የነበረውን ብርድ ልብስ ኢሳት ፎቶውን ያገኘ

ሲሆን፣ በረሃ ላይ የሚገኙ የግንቦት7 ታጋዮች እንደገለጹት ብርድ ልበሱን አንዳርጋቸው ከመቀበሉ በፊት ሌሎች 3 ሰዎች ሲጠቀሙበት ነበር።

አንዳርጋቸው ሲሄድ መኝታውን እራሱ አስሮ እንዳስቀመጠው የሚናገሩት ታጋዮች፣ ታሪክን ጠብቆ ለማስቀረት እንደታሰረ እንደሚቆይ ገልጸዋል።