የመለስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ስብሰባ ህዝቡ እንዳይቆጣ በሚል ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደረገ

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመለስ ዜናዊን ፋውንዴሽን እንሰራለን በሚል ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችና አርሶአደሮች በነፍስ ወከፍ ከ50 ጀምሮ

እንዲያዋጡ መገደዳቸው በቅርቡ ከተደረገው የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቁጣ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ በመሰጋቱ ፣ የገንዘብ መሰብሰቡ ሂደት ለጊዜው እንዲቋረጥ

መደረጉን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል።

ፋውንዴሽኑን ለማሰራት ከሚፈለገው ገንዘብ 10 እጥፍ እንደተሰበሰበ የሚነገርለት ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራ ሲሆን እስካሁን ድረስ ወጪና ገቢውን በተመለከተ

ለህዝብ ለማሳወቅ ባለመድፈሩ ከድርጅቱ አባሎች ትችቶች እየቀረቡበት ነው።

በአዲስአበባነዋሪዎችዘንድከፍተኛምሬትያስከተለውይህየገቢማሰባሰቢያበለፉትሁለትሳምንትበድርጅቱደጋፊዎችአማካኝነትየገንዘብማሰባሰቢያደረሰኝበመያዝበከተማውሁሉምቀበሌዎችና

በአንዳንድየወረዳየመንግስትመ/ቤቶችሲዘዋወሩየታየቢሆንም፣  በዚህሰሞንደግሞበደመወዝጭማሪውቅርየተሰኘውህዝብብሶትላለማባባስበሚልለጊዜውዘመቻውእንዲረግብተደርጓል፡፡

ዘመቻው የህዝቡ ምሬት “ቀንሷል” ተብሎ ሲታመን ሊቀጥል እንደሚችል መንጮች አክለው ገልጸዋል።

በቅርቡ የተደረገው የደሞዝ ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን እያባባሰው መሆኑን በእየለቱ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።