ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትምህርት ሚኒስቴር ” የከፍተኛ ትምህርት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጃት ማንዋል፣ ለምርጫ 2007 የተሻሻለ” በሚል ርእስ ያዘጋጀውና ለኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የቀረበው ሰነድ እንደሚለው በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው በምርጫው ለኢህአዴግ በሚያዘጋጁት የተማሪዎች የድጋፍ ሃይል መጠን ነው። ሰነዱ የትምህርት ልማት ሰራዊትን በዩኒቨርስቲዎች ለማስፋፋት የተደረገው ስራ ብዙም ውጤት እንዳላስገኘ ጠቅሶ፣ ለዚህም ...
Read More »የአዲስ አበባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ተባብሷል
ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ በርካታ አካባቢዎች የ24 ሰዓታት የውሃ አቅርቦት ማግኘት ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች ሥራቸውን በመተው ውሃ ለማግኘት ከሰፈር ሰፈር እንዲንከራተቱና ለተጨማሪ ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስአበባ በየትኛውም አካባቢ የመጠጥ ውሃ ችግር ተባብሶ መቀጠሉን የጠቆሙት ነዋሪዎች አስተዳደሩ በየጊዜው ተስፋ ከመስጠት ባለፈ በተጨባች ችግሮቹን መፍታት አልቻለም ብለዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ...
Read More »የቡድን 20 አገራት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን የሚቆጣጠሩበት አሰራር እንዲቀይሱ ተጠየቀ
ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግሎባል ፋይንሻል ኢንተግሪቲ ባወጣው ዘገባ በዚህ ሳምንት የቡድን 20 አገራት በአውስትራሊያ በሚያደርጉት ስብሰባ በህገወጥ መንገድ ገንዘብ በሚያዘዋውሩ ኩባንያዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል። ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው ድርጅት በዋጣው ዘገባ፣ ኩባንያዎች ሽያጮቻቸውን፣ ታክሶቻቸውን፣ ትርፋቸውና ኪሳራቻውን ግልጽ እንዲያደርጉ መመሪያ ሊወጣላቸው ይገባል ብሎአል። ታዳጊ አገሮች በእነዚህ ኩባንያዎች የተነሳ በእየአመቱ 1 ትርሊዮን ዶላር እንደሚያጡ ድርጀቱ ገልጿል። ታክስ ...
Read More »ኢህአዴግ በምርጫው ማግስት በዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞ እንዳይነሳ የመከላከያ ሰነድ አወጣ
ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል የልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል ለምርጫ 2007” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሰነድ በጥቅምት ወር በአዋሳ እንዲቀርብ ተብሎ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ የሰነዱ ጥራት የወረደና በሰነዱ የተካተቱት ነጥቦች ከልማት ሰራዊቱ ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ መጠቀሙን አያረጋግጥም በሚል በኢህአዴግ ጽ/ቤት በመተቸቱ እንዲሻሻል ከተደረገ በሁዋላ እንደገና ህዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም የኢህአዴግ አመራሮች ...
Read More »በሐገሪቱ የተስፋፋው ስራ ዓጥነት ለታቃዋሚ ለአሸባሪ እና ለሁከት ሃይሎች ግብአት ሆኗል ሲሉ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ተናገሩ
ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ እንደተናገሩት በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ፤ ሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ስራ አጥ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እየተቀላቀሉ ነው። የወረዳው ወጣቶችን ያወያዩት ሃላፊው ወጣት አርሶ አደሩ ተምሮ ስራ ካላገኘ ፤ ወይ የሚያርሰው መሬት ከሌለው ከትግል ውጭ ሌላ ...
Read More »በጸጥታ ሃይሎች የታፈኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸው ተዘገበ
ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍሎች የታፈኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አግባው ሰጠኝ ፣ የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ ትናንት ወደ ማዕከላዊ መወሰዳቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ሌሎች የተቃዋሚ አመራሮች ወደ ማእከላዊ ይወሰዱ አይወሰዱ ጋዜጣው አላብራራም። ባለፈው ሳምንት በትግራይ ...
Read More »በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የሟች ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ ገንዘብ ተቀብለው ገዳዮች ከእስር እንዲወጡ ማድረጋቸው ተዘገበ
ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገልፍ ኒውስ ባወጣው ዘገባ 4 ወንዶች አንዲት ኢትዮጵያዊትን አአስገድደው መኪና ላይ ከጫኑዋት በሁዋላ በየተራ ደጋግመው በመድፈርና በመኪናቸው ገጭተው በመግደል በላዩ ላይ ድንጋይ በማስቀመጥ ለማምለጥ ሞክረዋል። ግለሰቦቹ ተይዘው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በሁዋላ የጄራጂ ፍርድ ቤት በግለሰቦቹ ላይ የሞት ፍርድ ለማስተላለፍ በሂደት ላይ ነበር። ይሁን እንጅ ዳኛ አብዱላህ የሱፍ አል ሻሚሲ ፣ ላለፉት 5 ...
Read More »ፓርቲዎች ለሃይማኖት ተቋማት ጥሪ አቀረቡ
ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ››በሚል መርህ ትብብር የመሰረቱት 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀደም ብለው ባሳወቁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መሰረት የጀመሪያውን ጥሪ ለሃይማኖት ተቋማት አድርገዋል። ፓርቲዎቹ አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትበትም ጊዜ ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ የኃይማኖት ተቋማትና ምዕመናን ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተው፣ ዛሬ ላይ እነዚህ የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶች እየተናዱ በመሄዳቸው ...
Read More »በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በተለይ በዚህ ሳምንት ተባብሶ መቀጠሉ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን እያበሳጨ ነው፡፡
ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹በተለይ ባሳለፍነው አንድ ሳምንት ጊዜያት ውስጥ መቆራረጡ በወሳኝ ሰዓታት ጭምር ማለትም በምሽት እና በጠዋቱ ጊዜያት ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ነዋሪዎች በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራና ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለስልጣናት «የኃይል እጥረት የለም፣ እንዲያውም ተርፎን ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት እያደረግን ነው» በሚሉበት በዚህ ወቅት በተለይ የአፍሪካ ርዕሰ መዲና መሆንዋ በሚነገርላት አዲስአበባ ከተማ በቀን በአማካይ እስከ ሶስት ...
Read More »በግብር እዳ የሚማረሩ ነጋዴዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከገቢያቸው ጋር በማይመጣጠን የግብር እዳ እየተሰቃዩ ነው። የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች አድሎአዊ በሆነ መልኩ በሚጥሉት ግብር ነጋዴዎች ድርጅታቸውን እየዘጉ ነው። በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ አሰፋ ሁነኛው፣ ኢሳየ ቸኮል፣ የንጉስ ዋለና መሰሉ የሚባሉት ነጋዲዎች በጋራ ለቤት መስሪያ በባንክ ከስያዙት ገንዘብ ላይ ያለፍላጎተቻው በቀላጤ ብቻ ለግብር በሚል ገንዘባቸው ...
Read More »